political – news https://konjoethiopia.com Ethiopian news Tue, 05 Feb 2019 19:58:31 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.1.7 አቶ ዛዲግ አብርሃ ለህወሓት ያስገቡት ሙሉ ደብዳቤ https://konjoethiopia.com/2019/02/05/%e1%8a%a0%e1%89%b6-%e1%8b%9b%e1%8b%b2%e1%8c%8d-%e1%8a%a0%e1%89%a5%e1%88%ad%e1%88%83-%e1%88%88%e1%88%85%e1%8b%88%e1%88%93%e1%89%b5-%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%8c%88%e1%89%a1%e1%89%b5-%e1%8b%b0%e1%89%a5/ Tue, 05 Feb 2019 19:14:00 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1274 ለህወሃት ልዩ ዞን ፅ/ቤት አዲስ አበባ ላለፉት አመታት በህውሃት ድርጅት ስር ተደራጅቼ እንቅስቃሴ ሳደርግ እንደቆየሁ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም በፖለቲካው መስክ የመሳተፍ ፍላጎቱ ያልነበረኝ ቢሆንም በታሪክ አጋጣሚ የአገራችንን ፖለቲካ የመቀላቀል እድሉን አግኝቻለሁ፡፡ በተፈጠረው አጋጣሚም ስለሃገሬ የፖለቲካ ምንነት እና በፖለቲካ ገበያው ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦችንና ተቋማትን በቅርበት የማውቅና የመሳተፍ እድሉ ገጥሞኛል፡፡ በዛው ልክ ደግሞ በህወሀት […]]]>

ለህወሃት ልዩ ዞን ፅ/ቤት አዲስ አበባ

ላለፉት አመታት በህውሃት ድርጅት ስር ተደራጅቼ እንቅስቃሴ ሳደርግ እንደቆየሁ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም በፖለቲካው መስክ የመሳተፍ ፍላጎቱ ያልነበረኝ ቢሆንም በታሪክ አጋጣሚ የአገራችንን ፖለቲካ የመቀላቀል እድሉን አግኝቻለሁ፡፡ በተፈጠረው አጋጣሚም ስለሃገሬ የፖለቲካ ምንነት እና በፖለቲካ ገበያው ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦችንና ተቋማትን በቅርበት የማውቅና የመሳተፍ እድሉ ገጥሞኛል፡፡ በዛው ልክ ደግሞ በህወሀት ውስጥ አደርግ በነበረው ትሳትፎ በር የመዝጋት የመጠራጠርና እንደ ባዳ የመታየት ስሜት ከላይ እስከ ታች ድረስ አጋጥሞኛል፡፡ ገና ከጅምሩ ትግሉ ድርብ ድርብርብ ነበር ፡፡ በአንድ በኩል የመጣሁበት አካባቢ በክልሉ ፓለቲካ ውስጥ በዳርነት የሚመደብ ነውና አጠቃላይ ጉዞው እጅግ አቸጋሪ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቱ ወጣቶችን የመጠራጠርና ያለማመን ከፍተኛ ችግር የተንሰራፋበት ነውና እኔም እንደማንኛውም ወጣት ጉዞየ በሳንካ የተሞላ እንዲሆን አድርጎብኛል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአንድ ሙቀጫ መውቀጥ ጥሩ አይደለምና በህይወቴ ነገሮችን በተለየ መልኩ እንዳይ ያደረጉኝ እንዲሁም ትምህርት የሰጡኝ ጥቂት ሰዎች ነበሩና በነሱ ድጋፍና ምክር በችግርም ውስጥ ቢሆን እስካሁን ድረስ ለመዝለቅ ችያለሁ፡፡

በእርግጥም! በየሃገሬ ፖለቲካ ረጅም ርቀት ተጉዤ አስተቃጽኦ ላደርግበት የምችልና የሚገባ መሆኑን የማታ ማታ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ይሁንና ገና ከማለዳው ጀምሮ በህውሃት ውስጥ የነበረኝ የፖለቲካ ተሳትፎ አልጋ በአልጋ አልነበረም፡፡ በአጭሩ በሴራና በአሜኬላ የተሞላ ነበር ብሎ መናገር ማጋነን አይሆንም፡፡ ሆኖም ችግር ሲመጣ መሸሽና ማፈግፈግ ሳይሆን ፊት ለፊት ተጋፍጦና ተፋልሞ ማሸነፍ እንደሚገባ ላስተማረኝ ለውድ አያቴ ለሃዋደ ሻረው አቢቱ አበራ እና በአጠቃላይ ለራያ ማህበረሰብ ምስጋና ይግባውና ምርጫዬ “እግሬ አውጭኝ” ብሎ መሸሽ ሳይሆን አሜኬላውን መንቀልና ሴራውን ደግሞ ማፈራረስ ነበር፡፡

በአንፃራዊነት ከእድሜየና ከቆይታየ እንፃር ሲታይ በእርግጥ እድገቴ ፈጣን ነበር ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ ነገር ግን እድገቱ የመጣው በእኔ የስራ ፍላጎት እምነት ያላቸው የሌሎች ደርጅቶች የግንባሩ አመራሮች እየገፉና እየጠየቁ እንጅ በህወሀት በኩል እንደዛ አይነት ፍላጎት ስለነበረ አይደለም፡፡ እንዲያውም ቅናት ያደረባቸው አንዳንድ የህወሀት አመራሮች እድሉን ለማሰናከል ሲተጉ ተስተውላል ፡፡ አንዳንድ ግብዝ የዚህው ድርጅት አመራሮች ተመልሰው የማይገኙ በትላልቅ የአሜሪካ ትምህርት ቤቶች የመማር የነፃ የትምህርት እድልን ሳይቀር ትቼ አገሬን ለማገልገል በመወሰኔ በስልጣን ፍላጎት ከሰውኛል፡፡ በየቢሮው እየዞሩ የስልጣን ያለህ እያሉ የሚውሉት እነዚህ ግለሰቦች ከስልጣን ሲነሱ ደግሞ እንደ ልጅ እያለቀሱ የሚማፀኑ ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ የሚያስገርመው ነገር ደግሞ እያንዳንዱን እንጥፍጣፊ ስልጣን ለግል ጥቅምና ዝና ያላንዳች ርህራሄ የሚያውሉትና ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የስንቱን ምስኪን ህይወት የቀጠፉት እነዚህ ጨካኞች በግሌ ያገኘሁትን የነፃ የትምህርት እድልን መሰዋእት ያደረኩትን እኔን በስልጣን ፍላጎት ይከሳሉ፡፡

ይህን የመልቀቂያ ደብዳቤ እንዳዘጋጅና ከህወሀት ራሴን በፈቃዴ እንዳሰናብት በርካታ ገፊ ምክንያቶቼን እንደሚከተለው በዝርዝር የገለጽኩ ሲሆን የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች ሊረዱት የሚገባ ትልቅ ቁም ነገር ቢኖር ድርጅቱን በይፋ ለቅቄ ከመውጣቴ በፊት እንዲስተካከል የምችለውን ሁሉ ጥረት ማድረጌን ነው።

እስካሁን መልቀቂያ ሳላቀርብ የቆየሁበት ዋና ምክንያት ከዛሬ ነገ ወደ ማስተዋልና ካለፈው ተምረው በስተታቸውም ተጸጽተው ነገሮችን ያስተካክሉ ይሆናል በማለት ለዚህም ጊዜ መስጠቱ መልካም ነው ብዬ በማሰብ ነበር። ነገር ግን ይህንን እንደማያደርጉና ምንም የሚለወጥ ስብዕና እንደሌላቸው የስካሁኑ አካሄዳቸው ግልጽ ስላደረገልኝ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ደርሻለሁ።
በነዚህ ዓመታት በግሌ የምከተለውን አቋም እና የነበረኝን የትግል አካሄድ ትክክለኛነት እና ፍትሃዊነትን ተረድተው “አይዞህ” ብለው የሞራል ብርታት የሰጡኝ ከፍ ሲልም ከጎኔ ቆመው የታገሉ ጥቂቶች አልነበሩም፡፡ ነገር ግን ወደ ላይ በወጣሁ ቅጥር የተበጀልኝ ሴራ ይበልጥ እየተውሰበሰበ መጣ፡፡ በተለይም የጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዴሊቨሪ ሚኒስትር ሆኜ በተሾምኩ ማግስት ጀምሮ ጥቃቱ ተቋማዊ መልክ እየያዘና ትልልቅ ቱባ የህወሃት ባለስልጣናትም ጭምር የሚሳተፉበት ወደመሆን ተሸጋገረ፡፡ የፖለቲካ እስረኞችን ሙሉ በሙሉ ለመፍታትና የሰቆቃ ማእከል ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ማእከላዊ ተዘግቶ ወደ ሙዝየምነት እንዲቀየር ተወሰኖ ለመላው ህዝባችን ይፋ እንዲሆን ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በግለሰብ ደረጃ ይህ ነው የማይባል ጥቃትና ዛቻ እንዲሁም ማስፈራሪያ ደርሶብኛል፡፡

የአገሪቱ ቁንጮ የህወሐት ባለስልጣናት የተሳተፉበት ይኸው ጥቃት “ለምን የፖለቲካ እስረኛ አለ ብለህ ይፋ አወጣህ፤ ውሳኔው በቀጥታ twitter እና Facebook ለአለም በማሰራጨት የጠቅላይ ሚንስትርሩን ውሳኔ የማስቀየር እድላችንን ዝግ እንዲሆን አድርጋሀል ፤ በአጠቃላይ ከጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ፤ ከምክትል ጠቅላይ ምንስትር ከአቶ ደመቀ መኮንን፤ ከኦህዴድ አመራሮችና ከፈረንጆች ጋር ወግነህ የስርአት ለውጥ ለማምጣት የምትንቀሳቀስ የቀለም አብዮተኛ ነህ፤ ከዚህ በኋላ ከአንተ ጋር የምንነጋገረው በጥይት ነው!” በማለት ውሳኔው ከተላለፈባት ከዚያች ምሽት ጀምሮ ከፍተኛ ዛቻና የስነ-ልቦና ጫና ከትላልቅ የህወሐት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ በተለያዩ ወቅቶች ደርሶብኛል፡፡ እዚህ ላይ ግልፅ የሆነልኝ ነገር የድርጅቱ አመራሮች ምን ያክል እንደተበላሹና በታሰሩ ዜጎች መፈታት ምን ያክል እደሚያማቸው ነው፡፡ ጫናው ሲያይልና ይፋ የተደረገበት ምክንያት ግቡን ሲመታ በፌስቡክ ገፅ የተፃፈንውን ነገር ትንሽ ቆየት ብለንና በነጋታው ደግሞ በተለይም የውጭ ሚዲያ ወኪሎች የቀድሞውን ዘገባ እንዲያስተካክሉ አድርገናል፡፡ነገር ግን መረጃው አስቀድሞ በበቂ መጠን ስለተሰራጨ ግቡን ሊመታ ችላል፡፡
ከዛ በኋላም ቢሆን በነበሩት ተደጋጋሚ የህወሐት ስብሰባዎች ተመሳሳይ ስሞታና ዛቻ ደርሶብኛል፡፡ በእርግጥ አገራችንን ወደ ትልቅ እስር ቤት እየቀየራት የነበረው የጥቂት አምባገነኖች እርምጃ መቆም እንዳለበትና የነሱ ሰለባ የሆኑት የህሊና እስረኞች ከገባባቸው ነጻ መውጣት እንዳለባቸው ካመንኩኝ ውየ አድሬያለሁ፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ የታገልኩት የሰብአዊ መብት ለማክበር ነው፤ እስረኞች በህግ ጥላ ስር ሊመቱ አይገባም እያለ በአደባባይ ላይ ያለአንዳች ሃፍረት የሚለፍፍ ስርአት ራሱን ፉርሽ በሚያደርግ ሁኔታ ደብዳቢ እና ተጋራፊ ሆኖ መገኘቱ አንድ በቅርብ በማውቀው ወዳጄ ላይ ተከስቶ ካገኘሁት ጊዜ ጀምሮ የህሊና እረፍት ሊሰጠኝ ባለመቻሉ ይህ ሁኔታ መለወጥ እንዳለበት ካመንኩኝ ሰናባብቻለሁ፡፡
እናም መልካም እድልና ምቹ ሁኔታ ሲፈጠር መጠቀም ይገባ የነበረ በመሆኑ የህሊና እስረኞችን ለመታደግና ማዕከላዊን ወደ ሙዝየም ለመቀየር በተደረገው ጥረት ግንባር ቀደም ሚና ከተጫወቱ መሪዎች ጋር ሆኜ የድርሻዬን ተወጥቻለሁ፡፡ በዚህ ውሳኔ ሂደት ውስጥ የበኩሌን የጠብታ ታክል ድርሻ ተወጥቼ ከሆነ በህይወቴ የምኮራበት ትልቅ ተግባር እንጂ በምንም መልኩ አላፍርበትም፡፡ ሆኖም የአምባገነንነት እርካቡ እየተናደበት እንደነበር የገባው ህወሐት ውስጥ የመሸገው ቡድን በርግጎና በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ተነሳስቶ ለዚህ ውሳኔ ድርሻ ነበራቸው በሚላቸው ሃይሎች ያነጣጠረ እርምጃ መውሰድ መቼ ይቀርና!!

በተለይም ደግሞ አክራሪው ቡድን በህወሐት ውስጥ መሽጎ እንደሚገኝ የውስጥ አርበኛ ወስዶኝ ነበረና አንገቴን እንድደፋና ሸሽቼ እንድጠፋ ለማድረግ የተቀነባበረ የስም ማጥፋትና የጥቃት ውርጅብኝ ተካሂዶብኛል፡፡ ይህ ሁሉ ሁኔታ እየተካሄደ በነበረበት ሁኔታ እንኳን ምርጫየ ትግል እንጅ መፈርጠጥ አልነበረም፡፡
“ሳይደግስ አይጣላም!” እንዲሉ አበው . . . ከዛ በኋላ በፍጥነት በተቀያየረው ሃገራዊ ሁኔታ ትኩረታቸውን ስቦት እና አዛብቶት እንጅ የታሰበልኝን እና የተደገሰልኝማ ነገር አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነም ቢሆን ምርጫዬ መሸሽና አንገት መድፋት ሳይሆን አንገትን ቀና አድርጎ መታገል ነበር፡፡ ምክንያቱም ጥቃቱ በእኔ በግለሰብ ደረጃ ላይ ያነጣጠረ የነበረ በመሆኑ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የራያ ህዝብ ያለ ምርጫውና ያለውዴታው ገና ከማለዳው “ሆ. . .!” ብሎ የተቃመው አከላለል ከተወሰነበት ጊዜ ጀምሮ መግደልና ማሳደድን መቀጠላቸው ህዝቡም በተደራጀ መልኩም ባይሆን ትግሉ አላቆመም ነበር፡፡ የራያ ህዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ካደረጉት መሰረታዊ ምክንያቶች/ጉዳዮች አንዱ ትግሉ በተደራጀ መንገድ አለመከናወኑ መሆኑን አውቆ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተደራጀ መንገድ ወደ ትግል ገብቷል፡፡ ወንድሜ ከሆነውና በጠንካራ ማህበረሰባዊና ስነልቦናዊ ገመድ ከተሳሰርኩት የአማራ ህዝብ ጋር አብሬ ልኑር ብሎም እየተዋደቀ ይገኛል፡፡

ይህ ሲሆን ታዲያ የኢትዮጵያ የናሽናል ጥያቄ (የብሄረሰቦች ጥያቄ) ብዝሃነትን የማስተናገድ ችሎታ እጦት ነውና “ኢትዮጵያ ብዝሃነትን ልታከብር ይገባታል!” ብሎ በፕሮግራሙ ላይ በነጭና በጥቁር በደማቁ የጻፈው እንዲሁም በዛ ላይ ተመስርቶም ላለፉት 45 አመታት የፖለቲካ ሞብላይዜሽን ያደረገው ህወሐት ምላሽ ጥይት፤ ግድያ፤ ማፈናቀልና እንግልት ሆኗል፡፡

ነገሩ “ሆድ ሲያውቅ ደሮ ማታ ነው!” እና ድርጅቱ ለፕሮግራሙና ለዚያም ሲባል መስዋእት ለሆኑት ታጋዮቹ ክብር እንደሌለው በአደባባይ አስመስክሯል፡፡ የማንነት ጥያቄን ያነሱ እምቦቃቅላ ህጻናትን እስከ አፍንጫው በታጠቀው የክልሉ ልዩ ሃይል አናት አናታቸው እየተመቱ በእንጭጩ ተቀጭተዋል፡፡

በአጠቃላይ የራያ ህዝብ የተደራጀ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የስንቱ ህይወት እንደተቀጠፈ፤ ለእስር እንደተዳረገና እንደተፈናቀለ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ አካባቢው በዚህ ምክንያት ለከፋ ማህበራዊ መስቅልቅልና ቀውስ እንዲሁም ለጸጥታ ቀውስና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ተዳርጓል፡፡ በራያ ህዝብ ላይ ይህን የመሰለ ግፍና መከራ እየፈጸመ ካለ ድርጅት ጋር አብሬ እንድቀጥል ህሊናዬ አልፈቀደልኝም፡፡

በእርግጥ ገና ከገባሁ በጥቂት አመታት ውስጥ ልቤ ሸፍቶ በመንፈስ የራቅኩት ድርጅት ዛሬ ቀኑ ደርሶ በወጉ የአባልነት ግንኝነታችን ያበቃ ዘንድ የራያው ጉዳይ አንዱ ምክንያት ሆኗል፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ የለውጥ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በእርግጥ የአገራችን ችግር መሰረታዊ ለውጥ የሚሻና ውስብስብ ቢሆንም ችግሩን የሚመጥን መሰረታዊ የለውጥ ፕሮግራም ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ መናገር ይቻላል፡፡

ህወሐት በጥቂት ጠባብ ጸረ ለውጥ ቡድን ተጠልፎ ከሃገራዊ ለውጥ ጎን መቆም ሳይሆን ፀረ- አቋምን ምርጫው አድርጎ ለውጡ የትግራይን ህዝብ ጨምሮ መላው የአገሪቱ ህዝብ የሚጠቅም ቢሆንም ቅሉ፤ የውስን ሰዎች ጥቅም የሚያስቀር ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ድርጅቱ ሊታገልለት የሚገባውን የትግራይ ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ሳይሆን የጥቂት የህወሐት ባለስልጣናት ጥቅም ለማስከበር ሲል ለውጡን ተቃርኖ ብቻ ሳይሆን አፍራሽ በሆነ የሰላ ጥግ ላይ ቆሟል፡፡

በመሰረቱ ዲሞክራሲም ሆነ እኩልነት የትግራይ ህዝብ ለዘመናት የታገለላቸው እና ውድ ልጆቹን የገበረላቸው የህልውና ጥያቄዎች እንጂ ባለጋራዎቹ አይደሉም፡፡ አዲሱ የለውጥ ፕሮግራምም ተንጋዶ የበቀለውንና የማቃናትና አሜኬላውን የመንቀል እንጅ ከትግራይ ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ተቃርኖ የመጣ አይደለም፡፡ ህወሐት በዚህ ታሪካዊ ወቅት እየተወሰደ ያለውን ትክክለኛ እርምጃ የመቃወም ግዙፍ ስህተት ከድርጅቱ ጋር አብሬ እንዳልቀጥል ካደረጉኝ መሰረታዊ ምክንያቶች ሁለተኛው ነው፡፡

ከዛሬ ነገ ችግሮች ተቀርፈውና ተሻሽለው ከመስመር የወጡ አካሄዶችም ፈር ይዘው ይራመዳሉ በሚል ትዕግስትና ተስፋ ፤ ብዙ ነገሮችን በራሴ ይዤ እየታገልኩ ቆይቻለሁ:: በግሌም ሆነ በተገኘሁበት ማህበረሰብ ላይ እጅግ መራር ውርጅብኝ እየወረደ፤ ይባስ ብሎም በአገር ደረጃ ነገሮች እየተበለሻሹ እየሄዱ እንኳ ነገሮችን ለማቃናትና ለማሻሻል የበኩሌን እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ አካሂጃለሁ:: የሆነ ሆኖ ከግትር አቋማቸው ፈቀቅ የማይሉ ተቸካዮች በህዝብና በአገር ላይ የሚያደርሱት ግፍ አልበቃ ብሏቸው፤ በተገኘችው ጭላንጭል ዕድል ይህን መከራ ለማስቆም የሞከርኩትን ግለሰብ ስም ለማጥፋት በየመንደሩ ሲባዝኑ ይውላሉ::

ከጥንት ጀምሮ ለነፃነት ከኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር አብሮ የተዋደቀውን የትግራይ ህዝብ፤ ዛሬ እንደሰብዓዊ ምሽግ ተጠቅመው ሊለያዩት ቢሞክሩም ፤ ይህ የአክራሪ ወንጀለኞች የቀን ቅዠት እንደጉም መብነኑ እና መክሸፉም የማይቀር ነው! ኢትዮጵያዊነትን ከትግራይ ህዝብ ልብ ላይ መፋቅ ከቶም የማይቻልና ዛሬም ቢሆን እላዩ ላይ ተጋድመው የተጫኑትን የቀንበር እንጨቶች ሰብሮ ዳግም ለእኩልነትና ነፃነት እንደሚበቃ ቅንጣት ጥርጥር የለኝም!

በመጨረሻም ፀረ-ለውጥ እና ፀረ-ዴሞክራሲ ከሆነው ድርጅት ጋር ለመቀጠል ህሊናዬ ባለመፍቀዱ በገዛ ፍቃዴ ከድርጅት አባልነት የለቀቅኩኝ መሆኑን እያሳወቅኩ በቅርቡ ያታግለኛል ከምለው ድርጅት ጋር ተደራጅቼ የራያና መላ የአገሬ ራችን ህዝብ ጥያቄ ይበልጥ መልስ እንዲያገኝና ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተደረገ ያለውን ርብርብ አቅም በፈቀደው ሁሉ ለማገዝና ለመታገል እንደምሰራ ከወዲሁ ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡ የራያ ህዝብ በተድላና በፍቅር ከወሎ አማራና ከመላው የአማራ ህዝብ ጋር ለዘላለሙ ይኖራል ። ምክንያቶቹ በትንሹ እነዚህ ሲሆኑ በማወቅም ይሁን ባለማቅ በስካሁኑ የፓለቲካ ህይወቴ ያስቀየምኳችሁ ካላችሁ ከልብ የመነጨ ይቅርታን እጠይቃቹሃለው።

ዛዲግ አብርሀ
ድልና ነፃነት ለራያ ህዝብ !!!!!
ዴሞክራሲና ሰላም ለመላ የአገራችን ህዝብ!!!!!!
ገጽ 5

]]>
ጃዋር መሃመድ በለውጡ ሂደት ውስጥ የእሱን ሚና የገለፀበት አስገራሚ አባባል ። https://konjoethiopia.com/2019/01/09/%e1%8c%83%e1%8b%8b%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%88%83%e1%88%98%e1%8b%b5-%e1%89%a0%e1%88%88%e1%8b%8d%e1%8c%a1-%e1%88%82%e1%8b%b0%e1%89%b5-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%8a%a5%e1%88%b1%e1%8a%95/ Wed, 09 Jan 2019 15:00:45 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1252 “ዶ/ር አብይ ማለት አሁን የምንጓዝበት ባስ ሹፌር ነው። እኔ ደግሞ ከረዳቶቹ መካከል ነኝ። እንደረዳት ተሳፋሪው ችግር ሲፈጥር አረጋጋለሁ፤ ሾፌሩ እንቅልፍ እንዳይወስደው አነቃዋለሁ። ፍጥነቱን ጨምሮ ከተገቢ በላይ ከተጓዘ እንዲቀንሰው፣ ከተገቢው በታች በዝግታ ከተጓዘ ደግሞ ጨመር እንዲያረግበት አማክረዋለሁ፤ ግን ዝም ብለህ እያጨበጨብክ ብቻ ተከተለኝ ካለ absolutely wrong. ከኔም ይሁን ከወንድሞቼ የሚጠበቀው ዝም ብሎ እጅ ማጨብጨብ ሳይሆን መንገዱን […]]]>

“ዶ/ር አብይ ማለት አሁን የምንጓዝበት ባስ ሹፌር ነው።
እኔ ደግሞ ከረዳቶቹ መካከል ነኝ። እንደረዳት ተሳፋሪው ችግር ሲፈጥር አረጋጋለሁ፤ ሾፌሩ እንቅልፍ እንዳይወስደው አነቃዋለሁ። ፍጥነቱን ጨምሮ ከተገቢ በላይ ከተጓዘ እንዲቀንሰው፣ ከተገቢው በታች በዝግታ ከተጓዘ ደግሞ ጨመር እንዲያረግበት አማክረዋለሁ፤ ግን ዝም ብለህ እያጨበጨብክ ብቻ ተከተለኝ ካለ absolutely wrong.

ከኔም ይሁን ከወንድሞቼ የሚጠበቀው ዝም ብሎ እጅ ማጨብጨብ ሳይሆን መንገዱን ማየት፤ ተሳፋሪውን መመልከት፤ ጎማውን ተመልክቶ አየር ከጎደለው መሙላትና ሾፌሩ ደግሞ ሲሳሳት ሹፌሩ ያላየውን ረዳቱ በደንብ ስለሚመለከተው መምከር ነው። ባሱ እንኳን ትንሽ ችግር ቢኖርበት #ወርዶ ታኮ አስገብቶ የሚያስተካክለው ረዳቱ ነው።
ከዚህ ውጪ ዛሬ ከኛበላይ የሱ ደጋፊ የለም ብሎ ሚያጨበጭበው ሀገራችን የሆነ ችግር ውስጥ ብትገባ ከውጪየመጡት ወደመጡበት ይወጣሉ። ሀገር ውስጥ ያሉት ደግሞ እኔ_አላውቅም እንደሚሉ በሚገባ እናቃለን።

መንግስታች ትክክል ሲሰራ ልክ ነው እንላለን፤ መንግስታችን ላይ ጠላት ሲነሳ ጠላት ላይ እንነሳለን። መንግስት ሲያጠፋ ደግሞ ስህተቱን ነግረን ወደ መንገዱ እንዲመለስ እናረጋለን።
(Jawar Mohammed)

]]>
” አቶ ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ ተኩስ መግጠም አስፈላጊ አይደለም” የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ https://konjoethiopia.com/2019/01/02/%e1%8a%a0%e1%89%b6-%e1%8c%8c%e1%89%b3%e1%89%b8%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%88%b0%e1%8d%8b%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%88%98%e1%8b%ab%e1%8b%9d-%e1%89%b0%e1%8a%a9%e1%88%b5-%e1%88%98%e1%8c%8d%e1%8c%a0%e1%88%9d/ Wed, 02 Jan 2019 12:41:57 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1244 ቁጥራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ የአገሪቱ ዜጎች የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፤ የ2011 በጀት ዓመት የአምስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለ5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ተቋሙ […]]]>

ቁጥራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ የአገሪቱ ዜጎች የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፤ የ2011 በጀት ዓመት የአምስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለ5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ተቋሙ በሚመጡ ጥቆማዎች ከአንድ ቤተሰብ ብቻ ከአራት በላይ የቤተሰብ አባላት እንደተያዙ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ተቋሙም ይህን መነሻ አድርጎ የማጥራት ሥራ ቢሠራም ግለሰቦቹ ሲያዙ የፍርድ ቤት ትዕዛዝም ሆነ ያዢው ማን እንደሆነ በውል ባለመታወቁ ሥራውን በሚፈለገው ደረጃ ለማከናወን ተቸግሯል፡፡

በከባድ የአገር ሀብት ምዝበራ ወንጀልና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው ከተያዙ ግለሰቦች ውጪ አሁንም በመንግሥት የሥራ ኃላፊነትና በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ተሳታፊ  መሆናቸውን ጠቅሰው፣  ሕግን መሠረት ባደረገ መልኩ በተደራጀ ሁኔታ የተቀነባበሩ በመሆናቸው ምርመራውን አዳጋችና ተጠርጣሪዎችን ወደ ሕግ የማቅረብ ሂደቱን ፈታኝ አድርጎታል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ከአገር ውጭ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በኢንተርፖል እየመጡ ከአገር ውስጥ ግን ተሸሽገዋል የሚባሉትን ስለምን መያዝ አዳጋች ሆነ? በዚህ መንገድስ የህዝብ አመኔታ ማግኘት ይቻላል ወይ? ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አለማድረግስ የችግሩን ዕድሜ አያራዝመውም ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ከምክር ቤቱ የሕግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና አባላት ተነስተዋል፡፡              በተመሳሳይ ክልሎች በወንጀል ተጠይቆ ይፈለጋል የተባለ የለም በሚል ካለም አሳልፈው እንደሚሰጡ ሲናገሩ ይሰማል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተጠርጣሪዎችን የደበቁ እንዳሉ ይገልፃልና ይህ እንዴት ይታያል? ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተደበቁ ተጠርጣሪዎች በሌሉበት የሚታይበት አግባብ ላይ እንዲሁም የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት  ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ  ምክትል ለሕግ ቀርበው ጉዳያቸው ሲታይ ግብረአበራቸው በሚል ስማቸው ይነሳልና ያለመከሰስ መብት አላቸው ወይ?፣ ምንም እንኳ በአገሪቱ በነበረው የአመራር ሂደት ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጣ ቢሆንም ተጠርጣሪዎችን የመያዙ ጉዳይ ግን ብሔር ተኮር እንደሆነ ይነሳልና ከዚህ አንፃር በእኩል ደረጃ ተጠያቂ ማድረግ ጋር ተያይዞ ምን እየተሠራ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ከምክር ቤቱ አባላት ተነስተዋል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ  ጥያቄዎቹ ትክክለኛና ተገቢ እንደሆኑ በመግለጽ፤ መንግሥት ሕግን መሠረት አድርጎ ተጠያቂ የማድረግ ተግባሩን እያከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከተሸሸጉ ተጠርጣሪዎች ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሻቸውን ሲሰጡም አንዳንዶቹ  ቦታቸውን በመለዋወጥ፣ የተወሰኑት ደግሞ ያሉበት የማይታወቅ ሲሆን፤ ከአገር ውጭ ያሉትን ግን በመነጋገር ወደ አገር እንዲመጡ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር ተያይዞ ያለመከሰስ መብት አላቸው በሚል ለተነሳው ጥያቄ ግለሰቡ የፌዴራልም ሆነ የክልል ምክር ቤት አባል አለመሆናቸውን በመግለጽ ያለ መከሰስ መብት የሌላቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የተሸሸጉትም በክልሉ ውስጥ ቢሆንም እርሳቸውን ለመያዝ ግን በተኩስ መሆን አለበት ብሎ መንግሥት አያምንም ብለዋል፡፡ ክልሎች ወንጀለኛ ተብሎ የተጠየቁት እንደሌለና አሳልፈው እንደሚሰጡ የሚያነሱትም ትክክል አይደለም፡፡ ይልቁንም በደብዳቤ ጭምር የተጠየቀ በመሆኑ ይህን መሠል ምላሽ የሚሰጠው ‹‹አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም›› ሆኖ ነው ሲሉ ድርጊቱ ሆነ ተብሎ እየተፈፀመ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከብሔር ተኮር ተጠያቂነት ጋር ተያይዞ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፤ በከፍተኛ አመራር ቦታዎች ላይ አብላጫውን ቦታ ይዞ የነበረ ብሔር ተጠያቂ ሲደረግ ሊያዝ ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህን ለማሟያ በሚል ሌሎችን የማካተት ሥራ አይሠራም፡፡ ተጠያቂነቱ ወንጀል ተፈጽሟል አልተፈፀመም? የሚለውን እንጂ በፖለቲካ አቋምና በብሔር አለመሆኑንም ነው  የገለጹት፡፡ በመሆኑም በሁሉም ክልሎች ወንጀለኞችን የሚሸሽጉ አካላትን አጋልጦ ለሕግ እንዲቀርቡ የማድረግ ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ፣ የፖለቲካ አመራርና የምክር ቤቱም ነው ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አዲስ ዘመን ታህሳስ 24/20111

]]>
ዓረና የህወሓት ተቃዋሚ ነው ፤ ደጋፊ አይደለም ። https://konjoethiopia.com/2019/01/01/%e1%8b%93%e1%88%a8%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8b%88%e1%88%93%e1%89%b5-%e1%89%b0%e1%89%83%e1%8b%8b%e1%88%9a-%e1%8a%90%e1%8b%8d-%e1%8d%a4-%e1%8b%b0%e1%8c%8b%e1%8d%8a-%e1%8a%a0%e1%8b%ad%e1%8b%b0/ Tue, 01 Jan 2019 14:04:07 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1241 ከህወሓት ድጋፍ አንጠብቅም! ================= ዓረና የህወሓት ተቃዋሚ ነው፤ ደጋፊ አይደለም። የህወሓት ደጋፊዎችና ተላላኪዎች ህወሓትን አትንኩብን እያሉ ነው። ልክ ናቸው። ምክንያቱም ህወሓት ከተነካች ትጋለጣለች። ከተጋለጠች ከስልጣን ትወርዳለች። ከስልጣን ከወረደች ጥቅማቸው ይነካል። ጭቁን የትግራይ ህዝብ ነፃ ይወጣል፣ በእኩል ዓይን ይታያል። ሰዎች በብቃታቸው ይመዘናሉ፣ ስራ ያገኛሉ። የተዘረፈው ገንዘብ ለህዝብ ይከፋፈላል። ህዝብ ይጠቀማል። ትግራይ የህዝቧ እንጂ የህወሓት ተላላኪዎች የግል […]]]>

ከህወሓት ድጋፍ አንጠብቅም!
=================

ዓረና የህወሓት ተቃዋሚ ነው፤ ደጋፊ አይደለም። የህወሓት ደጋፊዎችና ተላላኪዎች ህወሓትን አትንኩብን እያሉ ነው። ልክ ናቸው። ምክንያቱም ህወሓት ከተነካች ትጋለጣለች። ከተጋለጠች ከስልጣን ትወርዳለች። ከስልጣን ከወረደች ጥቅማቸው ይነካል። ጭቁን የትግራይ ህዝብ ነፃ ይወጣል፣ በእኩል ዓይን ይታያል። ሰዎች በብቃታቸው ይመዘናሉ፣ ስራ ያገኛሉ። የተዘረፈው ገንዘብ ለህዝብ ይከፋፈላል። ህዝብ ይጠቀማል። ትግራይ የህዝቧ እንጂ የህወሓት ተላላኪዎች የግል ንብረት አትሆንም። እናም ይጎዳሉ (ከህዝብ ጋር እኩል ይሆናሉ) ለብቻ መብላት አይኖርም።

ስለዚህ ህወሓትን ስንተች ቢንገበገቡ አይገርምም፤ የጥቅም ጉዳይ ነውና። ዓረና የህወሓት ተቃዋሚ እንደመሆኑ መጠን የህወሓት ደጋፊዎች እንዲደግፉን አንጠብቅም። ስለዚህ ቢቃወሙን አይደንቀንም። ከቁብም አንቆጥረውም። (ህወሓት ስትነካ የሚያንገበግበው ሰው የህወሓት ደጋፊና ተጠቃሚ እንጂ ሌላ ማን ሊሆን ይችላል? ያልሆነማ የተለያዩ አማራጭ ሐሳቦች ማየት አለበት)። የህወሓት ሰዎች ሲቃወሙን ልክ ናቸው። የጥቅም ጉዳይ ነውና።

ግን አንድ ነገር ተሳስተዋል። ዓረና የህወሓት ደጋፊ እንዲሆን ይፈልጋሉ። ሊሆን አይችልም። ዓረና ከህወሓት የተለየ ዓላማ ያለው ድርጅት ነው። ህወሓቶች ለውጥ አይፈልጉም፤ ዓረና ለውጥ ለማምጣት ነው ሚታገለው። ስለዚህ የተለያየን ነን። ለውጥ ከመጣ እንደግፋለን። ለለውጥ እየታገልን ለውጥን አንቃወምምና! የኛ ጉዳይ ለውጡ ህዝብ ሚጎዳ ሳይሆን ሚጠቅም መሆን አለበት ነው።

ለውጥ ለማምጣት ትግል የጀመርነው ከ10 ዓመት በፊት ጀምሮ ነው (የወራት ዕቅድ አይደለም)። ዴሞክራሲ ሰፍኖ ህዝባዊ መንግስት እስኪመሰረት ድረስም ይቀጥላል።

አሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ ባጠቃላይ ለትግራይ ህዝብ ደግሞ በተለይ የሚጠቅም አማራጭ ሐሳብ ስናቀርብ የስድብ ዘመቻ ያካሂዳሉ። ህወሓትን አትንኩብን ይላሉ። ህወሓትን የተቃወመ የጠቅላይ ሚኒስተር ዶር ዐብይ አሕመድ ተላላኪ በማለት ለማጥላላት ይሞክራሉ (ዶር ዐቢይ ግን የዓረና አባል ሆነንዴ?!)። “ወደኛ ተቀላቀልና ሌሎችን ሁሉ በመሳደብ የተጋሩን ደሕንነትና ጥቅም እናስከብር” ይሉሃል። ሌሎችን በመሳደብ የተጋሩን ጥቅምና ደሕንነት የሚከበር ይመስላቸዋል። ህወሓት ያልደገፈ ትግራዋይ እንዳልሆነ ይሰብካሉ፤ ትግራዋይነት የሚታደለው እንደ ፓርቲ መታወቅያ በህወሓት ይመስል!

አሁን ህወሓቶችን በሚተቹ አክቲቪስቶች ላይ የስድብ መዓት በማውረድ የማጥላላት ዘመቻ እንዲከፍቱ መመርያ ተሰጥቶዋቸዋል (መደብ ወርዶላቸዋል)። የስድብ ጦርነት ከፍተዋል። ዋና አዛዥ የህወሓቱ ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ሲሆን በደሕንነት፣ በኮሙኒኬሽን ቢሮ እና በክልሉ ሚድያ ተቋማት አስተባባሪነት በተለየ በሚከፈላቸው አክቪስቶች ነን ባዮች የሚከናወን ነው፤ የማይከፈላቸው ግን በህወሓት “የተከበናል” (የፀጥታ ችግር) ፕሮፖጋንዳ የተሸወዱም አሉ። የፀጥታ ችግር ቢያጋጥም እንኳ በህወሓት መሪነት ሊፈታ እንደማይችል ያልተገነዘቡ አሉ።

ከነዚህ ቅልብተኛ አክቲቪስት ነን ባዮች አንዱ በክልሉ ቴለቪዥን ጣብያ ቀርቦ “እነዚህ ፀረ ህወሓት አክቲቪስቶች ከፌስቡክ ወደ ትዊተር አባረናቸዋል” ብሏል (በመንጋ ስድብ መሆኑ ነው)። ዓላማቸው የስድብ ዘመቻ በመክፈት ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ደጋፊ የለንም ብለው እንዲሸማቀቁ፣ ስድብ ፈርተው ህወሓትን ከመተቸት እንዲቆጠቡና ህወሓት መልሳ እንድታገግም ዕድል ለመስጠት ነው።

አሁን ስለ ህወሓት ጥሩ ነገር ብፅፍ ራሱ መሳደባቸው አያቆሙም። ምክንያቱም መደብ (መመርያ) ተሰጥቷቸዋል። ዝም ብለው ስድብ ይፅፋሉ። እንደ ፓሮት የተነገራቸውን ይደግማሉ። ከነዚህ ተከፋይ ተሳዳቢዎች በቅርቡ በትእምት ስፖንሰርነት “አንዳንድ ነገሮች” እንዲጎበኙ ተጋብዘው ነበር። ከተጋበዙት አብዛኞቹ ብዙ የፌስቡክ አካውንቶች ከፍተው እንዲሳደቡ የሚከፈላቸው ናቸው።

ዓረና ግን እንኳን በስድብ በጠመንጃም አይሸማቀቅም፤ ዓላማ ነዋ። ከህወሓትም ድጋፍ አይጠብቅም። በትግራይም ለውጥ እንፈልጋለን። ሊያስተዳድረን የሚገባ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ነው። ህወሓት የህዝብ ድጋፍ አለኝ ብሎ የሚያምን ከሆነ አማራጭ ሐሳብ ለምን ይፈራል?

ይህን የትእምት ገንዘብ ለቅልብተኛ ተሳዳቢዎች ከሚከፈል ዩኒቨርስቲ ተመርቀው ስራ ያላገኙ ግን ብዙ ማምረት የሚችሉ ወጣቶች ስራ የሚጀምሩበት ዕድል ለምን አይከፈትላቸውም? ያመርታሉኮ! መሳደብ ግን ምርት የለውም! እናም የትእምት ገንዘብ ለተሳዳቢዎች ከሚሰጥ ለአምራች ወጣቶች ቢውል ውጤታማ ይሆናል።

አትድከሙ! ከህወሓት ተላላኪዎች ድጋፍ አንጠብቅም፤ የራሳችን ለውጥ ፈላጊ ወጣት ደጋፊዎች አሉን። የህወሓት ደጋፊም አንሆንም፤ የምንደግፈው የራሳችን ድርጅት አለን። የዓረና ማሕበራዊ መሰረት (Social Base) የህወሓት አባል ወይ ደጋፊ አይደለም። ለዚህም የትግራይን ህዝብ እንጂ ህወሓቶችን ለማስደሰት አንሰራም። ከድርጅት ህዝብ ይቀድማል!

ዴሞክራሲ ያሸንፋል!

It is so!!!

]]>
“ለረዥም ጊዜ ፖለቲካ ውስጥ የመቆየት ፍላጎት የለኝም” ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ https://konjoethiopia.com/2018/12/27/%e1%88%88%e1%88%a8%e1%8b%a5%e1%88%9d-%e1%8c%8a%e1%8b%9c-%e1%8d%96%e1%88%88%e1%89%b2%e1%8a%ab-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%89%86%e1%8b%a8%e1%89%b5-%e1%8d%8d%e1%88%8b%e1%8c%8e/ Thu, 27 Dec 2018 15:29:39 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1236 የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የሆኑትና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋን በጽህፈት ቤታቸው አግኝተናቸው በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርገናል። ቢቢሲ አማርኛ፡ አንዳርጋቸው ታፍኖ መወሰዱን ባወቅክባት ቅፅበት ምን ተሰማህ? ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ፡ አንዳርጋቸው የተያዘ ጊዜ ኒው ዮርክ ነበርኩ። እንደተያዘ እዚያው የመን እያለ ነው የሰማሁት፤ በተያዘ በግማሽ ወይንም በአንድ ሰዓት አብረው ሲበሩ ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ነው […]]]>
ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ

የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የሆኑትና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋን በጽህፈት ቤታቸው አግኝተናቸው በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርገናል።

ቢቢሲ አማርኛ፡ አንዳርጋቸው ታፍኖ መወሰዱን ባወቅክባት ቅፅበት ምን ተሰማህ?

ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ፡ አንዳርጋቸው የተያዘ ጊዜ ኒው ዮርክ ነበርኩ። እንደተያዘ እዚያው የመን እያለ ነው የሰማሁት፤ በተያዘ በግማሽ ወይንም በአንድ ሰዓት አብረው ሲበሩ ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ነው የሰማሁት። እዚያ ያሉ እኛን የሚያውቁ ሰዎች እንደዚህ አይነት ነገር አለ ተከታተሉ ብለው የነገሩን ያኔ ነው።

በዚያ በኩል እንደሚሄድም አላውቅም ነበር፤ በሌላ በኩል እንደሚሄድ ነበር የማውቀው። ያው መጀመሪያ ላይ ትደነግጣለህ። የመጀመሪያ ሥራህ የሚሆነው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄድ ወይንም ችግር እንዳይደርስበት ማድረግ የሚቻለውን ለማድረግ ለተለያዩ መንግሥታት፣ አቅም ላላቸው ሰዎች፣ መንገርና አንድ ነገር እንዲያደርጉ መሞከር ነበር።

ቢቢሲ አማርኛ፡ እርሱ እስር ቤት በነበረበት ወቅት እርሱን በተመለከተ ምን አይነት ስሜቶችን አስተናገድክ?

ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ፡ ከአንዳርጋቸው ጋር ለረዥም ጊዜ ነው የምንተዋወቀው። ብዙ አውርተናል። ምን እንደሚፈልግ አውቃለሁ። እኔም ምን እንደምፈልግ ያውቃል። ሲታሰር የተወሰነ የድርጀቱን ሥራ ኃላፊነት እርሱ ስለነበር የወሰደው ኢትዮጵያ መምጣቱን ካወቅሁ ጊዜ ጀምሮ ለእኔ ግልፅ የሆነልኝ በምንም አይነት እንደማይፈቱት፣ እንደማይገድሉትም አውቅ ነበር።

ጥያቄው ያለው እንዴት ታግለን ቶሎ ይህንን ነገር እናሳጥራለን የሚል ነው። ከዛ በኋላ ብዙ ጊዜ አልፈጀብኝም ሥራዬን ሁሉ ትቼ እርሱ የጀመራቸውን ሥራዎች ወደ መቀጠል ነው የገባሁት። በእንዲህ አይነት የትግል ወቅት አንዳርጋቸው ሲታሰር ምን ይፈልጋል? ማንም ሰው ቢለኝ፤ የታገለለትን አላማ ከዳር እንድናደርስለት ነው እንጂ የሚፈልገው ሌላ ለግሉ እንዲህ አይነት ነገር ይደርስብኛል የሚል የስሜት ስብራት ውስጥ እንደማይገባ አውቅ ስለነበር፤ ያለኝን ጠቅላለ ጉልበቴን ያዋልኩት እንዴት አድርገን ይህንን ትግል በቶሎ ገፍተን እርሱንና በየቦታው የሚታሰሩትን ጓዶቻችንን ነፃ እናወጣለን ወደ ሚለው ነው።

ከዚያ ባሻገር ግን የታገልንለትን አላማ፣ ኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ የማድረግ አላማ፣ ከዳር እንዴት እናደርሳለን የሚለው ነው፤ ከዚያ ውጪ ሌላ አልነበረም። ከመጀመሪያው አንድ ቀን ሁለት ቀን ውጪ ጠንካራ የሆነ የስሜት መዋዠቅ ውስጥ መግባት አይገባም ብዬ ነው ለራሴ የነገርኩት።

አሁን ሥራው ይህንን ነገር ከዳር ማድረስ ነው። በእንዲህ አይነት ትግል ውስጥ ችግሮች ይፈጠራሉ፤ ግን እያንዳንዱ ችግር ላይ ከፍተኛ የሆነ የስሜት መዋዠቅ ካስቀመጥክ ሥራ አትሰራም። ሁሉን ነገር ዘግቼ ይህንን ነገር እንዴት ከዳር እናደረሳለን የሚለው ላይ ነው ጊዜዬን ያጠፋሁት።

ቢቢሲ አማርኛ፡ አሁን ያለው ለውጥ የሚሾፈረው በኢህአዴግ መሆኑ ምን አይነት ስሜት ነው የሚፈጥረው?

ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ- አንዱ ትልቁ ጥያቄ ኢህአዴግን የምናየው የድሮው ኢህአዴግና የአሁኑ ኢህአዴግ አንድ ነው፤ ወይንስ ቢያንስ ያንን ለውጥ ካመጡ ሰዎች በኋላ በመሰረታዊ መልኩ ለውጥ አድርጓል የሚለውን መመለስ አለብህ።

የትግል ለውጥ ስትራቴጂ ለውጥ ስናደርግ የወሰንነው ይህንን ለውጥ ለማምጣት የመጡት ሰዎችን፤ በእንዲህ አይነት የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ስትሆን አንዱ ሥራህ የመንግሥት ስልጣንን በያዘው ኃይል ውስጥ ያለውን ነገር ማጥናት ነው።

ስለዚህ በኢህአዴግ ውስጥ የሚደረጉትን ለውጦች እንከታተል ነበር፤ እና አንዱ ትልቁ ጥያቄ የነበረው እነ ዐቢይ ሲመጡ ኢህአዴግን በአዲስ መልኩ ለማስቀጠል የመጡ ሰዎች ናቸው ወይንስ እውነተኛ ለውጥ ፈልገው የመጡ ናቸው የሚለውን መመለስ ነበር። እነዚህ ሰዎች ዝም ብሎ በፊት የወያኔ ሥርዓት ይከተል የነበረውን ነገር ለማስቀጠል የሚያስቡ ሰዎች እንዳልሆኑ ስንረዳ ብዙ ጊዜ አልወሰደብንም።

ምክንያቱም በከፊል የመጡትም በህዝብ ትግል ነው። ሀያ ምናምን ዓመት ያልተቋረጠ ትግል ሲካሄድበት የነበረው ከዛም ሦስት ዓመት ደግሞ ያላቋረጠና የተጋጋለ ሰፊ የህዝብ ትግል ሲካሄድበት የነበረው ነው። ኢህአዴግ በነበረበት ሊቀጥል እንደማይችል ግልፅ የሆነበት ጊዜ ነው። በዚያን ጊዜ የመጡት እነዚህ ሰዎች ኢህአዴግን ሸውደን ሌላ አዲስ መልክ አምጥተን እናስቀጥል ብለው የሚያምኑ ሳይሆኑ በርግጥም የበፊቱ ሥርዓት ተሸንፎ የመጡ ናቸው።

ይህንን አንዴ ከወሰንክ በኋላ፣ ተጋግዘህ ያንን ሥርዓት ለማቆም ትሞክራለህ እንጂ በፊት የነበሩት ሰዎች እንዲህ ነበሩና በመሳሪያ ልቀጥል የምትለው ነገር አይደለም። እኛ በምንም አይነት፣ መቼም ቢሆን የመሳሪያ ትግልን እንደጥሩ ነገር አድርገን ገብተንበት አናውቅም። ምርጫ አጥተን የገባንበት ነው። ያን አላስፈላጊ የሚያደርግ ነገር ሲፈጠር ደቂቃም አልፈጀብንም። ተመልሰን ወደ እውተኛ ሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ ወደ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ መንገድ መሄድ የተሻለ ነው ብለን ነው የገባንበት።

በኢህአዴግ ውስጥ ወጥ ነው ማለት ባይቻልም ለውጡን ይዘው የመጡት ኃይሎች በርግጥም ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚፈልጉ መሆናቸውን እናምናለን። ያንን ሥርዓት ለማምጣት ከእነርሱ ጋር አብረን እንሰራለን፤ ከዚያ በኋላ ኢህአዴግ ካሸነፈ፤ እኛ እኮ በፊትም ኢህአዴግ ለምን አሸነፈ አይደለም፤ የሕዝብ ፍላጎት የህዝብ ፈቃድ አግኝቶ ያሸንፍ ነው የምንለው።

ማንም የህዝብ ፍቃድ አግኝቶ ያሸንፍ የህዝብ መብት ይከበር፣ ሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ። የህግ ልዕልና ይኑር። እነኚህ ናቸው ጥያቄዎቹ። ማን ስልጣን ያዘ አይደለም። ዋናው ጥያቄ በምን መልክ ስልጣን ይያዛል? የህዝብ ፈቃድ አግኝቶ ነወይ? ህዝብ በፈለገ ጊዜ ሊያወርደው የሚችል ነወይ? ከዛ በተጨማሪ ደግሞ እውነተኛ ነፃ የሆኑ ተቋማት አሉ ወይ? ፍርድ ቤቱ በነፃነት ይሰራል ወይ? ጦር ኃይሉ በርግጥም ህብረተሰቡን የሚጠብቅ ነው ወይስ የአንድ ፓርቲ መሳሪያ? የምርጫ ተቋሞቹ እርግጥም ነፃና የህዝብ ፍላጎት የሚንፀባረቅባቸው ምርጫዎች ለማድረግ ፈቃደኞች ናቸው? እነዚህ ናቸው ጥያቄዎቹ። ያንን ለማድረግ ፍላጎት ያለው አካል እስከመጣ ድረስ እኛ ምንም ችግር የለብንም።

ቢቢሲ አማርኛ፦ ሥርዓቱን ሰው ባይጥለው ኢኮኖሚ ይጥለዋል ትል ነበር። አሁን ያለውንስ መንግት?

ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ፡ ይኼ አዲሱ የለውጥ ኃይል ከነበረው የወጣ ነው ብለህ ብታስብ፣ ፕሮፓጋንዳውን ምናምኑን ትተህ የተረከበው ኢኮኖሚ ደንበኛ የዝርፊያ ሥርዓት የሽፍታ ኢኮኖሚ ሥርዓት ነበር። ዝም ብለህ ያገኘኸውን ዘርፈህ የምትሄድበት። የነበሩትን ፕሮጀክቶች ይካሄዱ የነበሩትን እንዳለ ብታይ ከዝርፊያ ጋር የተያያዙ ናቸው።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ምናምን ብለህ አንድ ጤነኛ ሰውና ስለከተማ ትራንስፖርት የሚያውቅ ሰው እንዲህ አይነት የከተማ ትራንስፖርት፣ በዚህን ያህል ወጪ አውጥቶ አይተክልም ነበር። በጣም ቀላል የሆኑ፣ በቀላሉ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግሮች የሚፈቱ፣ እንደዚህ ከተማዋን ለሁለት ከፍለህ አስቀያሚ ሳታደርገው ልትፈታ የምትችልባቸው መንገዶች ነበሩ።

ፕሮጀክቶቹ በአንድ መልኩ ወይም በሌላ ለመስረቂያ ተብለው የተዘረጉ ናቸው። ለዚህ ነው ማለቅ ያልቻሉት። ለዚህ ነው ከአስር ከሃያ እጥፍ በላይ ወጪ የሚያስወጡት። እነኚህ ሁሉ የሆኑት ደግሞ በሕዝብ ስም በሚገኝ ብድር ነው። ይህ ሁሉ ብድር ሀገሪቱ ላይ ተከምሮ ወደ ሰላሳ ቢሊየን ዶላር ብድር ያለባት ሀገር ነች።

ይህ የሆነው ያ ሁሉ ብድር ከተሰረዘ በኋላ፣ በተለይ ከምርጫ 97 በኋላ የመጣ ይህንን የዘረፋ ሥርዓት ለማቆየት የተዘረጋ ሥርዓት ነው። ይኼ ነገር መጥቶ መጥቶ በተወሰነ ደረጃ ኢኮኖሚውን ዝም ብሎ ያራግበዋል። ምክንያቱም ዝም ብሎ ገንዘብ ኢኮኖሚ ውስጥ ስላለ። በኋላ ላይ ግን ተንገራግጮ መቆሙና ችግር ውስጥ መጣሉ የማይቀር ነው። እና በዚህ ምክንያት ይህንን ሥርዓት የተረከቡት ሰዎች በጣም ከባድ የሆነ ችግር ይገጥማቸዋል። አንደኛው እዳውን መክፈሉ፤ ሁለተኛ በአጠቃላይ የንግድ ሥራን በሚመለከት ያለው ባህል ተበላሽቷል። ሁሉም በስርቆት በማጭበርበር በምናምን አገኛለሁ ብሎ የሚያስብ የኢኮኖሚ ክላስ ነው የተፈጠረው።

ሀብታም የሚባሉትን፣ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር ሚሊየነር ሆኑ የሚባሉትን፣ አይነት ግለሰቦችን ብታይ ቁጭ ብለው አስበው ምን ያዋጣል ለህብረተሰቡ የተሻለ እቃ እንዴት እናቅርብ በማለት አይደለም። ወይ መሬት ዘርፈው፣ ወይ ከባንክ ገንዘብ ተበድረው ያገኙት ነው። በዚያ አይነት መሰረት ላይ የቆመ ኢኮኖሚ ሁል ጊዜ ችግር ይገጥመዋል። ይህንን ሁሉ መቀየር በማክሮ ኢኮኖሚ ደረጃ ያሉብህን ችግሮች መፍታት ብቻ ሳይሆን የንግድ አመለካከቱን ባህሉን ራሱ መቀየር በጣም ሰፊ ሥራ የሚጠይቅ ነገር ነው።

ይህንን ለማስተካከል ግን በመጀመሪያ የፖለቲካው ሥርዓቱ መስተካከል አለበት። ከዚያም ባሻገር ግን ሰላምና መረጋጋቱ ወዲያውኑ መምጣት አለበት። ይህንን የፖለቲካ ነገር ሳታስተካክል የኢኮኖሚውን ነገር ማስተካከል ከባድ ነው። ለዚህ ነው ቅድሚያ የፖለቲካ ማስተካከያዎች መወሰድ ያለባቸው እንጂ፤ ቶሎ ብሎ የእነዚህን የኢኮኖሚ ችግሮች አንድ በአንድ መመልከት ግዴታ ነው። መንግሥትም ይኼን ይገነዘባል ብዬ አስባለሁ። የለውጥ ኃይልም ስለሆነ ከሌሎችም ሀገሮች በተወሰነ መልኩ እዳውን ለመቀነስ ትብብር ያገኛል ብዬ አስባለሁ። ምንም እንኳ ፖለቲካውን የመፍታት እርምጃ መውሰድ ቀዳሚ ቢሆንም የኢኮኖሚውንም ችግር ለመፍታት በአንድ ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።

ቢቢሲ አማርኛ-አንዳንድ የተወረሱብህን ንብረቶች ለማስመለስ ሞክረሃል?

ፕሮፌ. ብርሃኑ፡ እስካሁን አልተመለሱም። ይኼ ለውጥ ስለእኔ አይደለም። 100 ሚሊየን ህዝብ የሚበላው ያጣ ያለበት ሀገር አሁን የእኔን ንብረት መለሱ አትመለሱ በጣም ትልቅ

ፕሮፌ. ብርሃኑ፡ የደህንነት፣ ሰላም የማረጋጋት፣ ባለፈው27 ዓመት የተፈጠረው የክልል አደረጃጀት። የክልል አደረጃጀቱ ደግሞ ዝም ብሎ በዘር ላይ፣ በደም ቆጠራ ላይ መመስረቱ ብቻ አይደለም። በዚያ ላይ የተመሰረተው አከላለል የራሱ ጦር ያለው አገር ነው። አሁን እነዚህ ክልሎች የምትላቸው የራሳቸው ሀያ ሺህ፣ ሰላሳ ሺህ. . . ጦር አላቸው የሚባል ነው።

በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም። በአንድ ሀገር እንደዚህ አይነት ኃይል ሊኖር የሚገባው የመንግሥት መከላከያ ነው። ለሁሉም እኩል የሆነ፣ ሁሉንም በጋራ የሚያገለግል፣ የሁላችንንም ደህንነት የሚጠብቅ ኃይል። አሁን ግን በሁሉም ክልሎች ያሉ ኃይሎች አሉ።

እነዚህን ሁሉ እንዴት አድርጎ በአንድ ሀገራዊ የመከላከያ እዝ ስር ታደርጋቸዋለህ? በየአካባቢው ከብሔር ጋር በተያያዘ የተነሱ ግጭቶችን እንዴት ታስቆማቸዋለህ? እንደ አገር ወይ ከዚህ ችግር ወጥተን እንበለፅጋለን። ወይ እንደሃገር እንፈርሳለን። የተወሰነ ቡድን አልፎለት፣ ሌላው የማያልፍለት አገር ሊኖረን አይችልም።

ሁላችንም ተሰባስበን የምንኖርባት፣ የሁላችንም መብት የተከበረባት፣ የሁላችንም ባህል የሚከበርባት፣ የሁሉም ቋንቋ የሚከበርባት የተረጋጋች ሀገር መፍጠር በጣም ከባዱ ከእነ ዶ/ር አብይ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ይሄንን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባት ሂደት ላይ የሚገጥመን ችግር ነው።

ነገር ግን በደንብ መነጋገር ከቻልን በማስፈራራት ሳይሆን ቁጭ ብለው እየተነጋገሩ ህብረተሰቡ ያሉትን አማራጮች እየሰማ የምንነጋገርበት አይነት የፖለቲካ ምህዳር መፍጠር ከቻልን፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በምን አይነት የፖለቲካ ሂደት ፖለቲካቸውን እንደሚያስተዋውቁ በደንብ ከተስማሙና ሁሉም ለዚያ ታማኝ ከሆኑ የምንወጣው ችግር ነው። የሚያቅተን አይደለም። አሁን ብዙ ችግር ያለ ይመስላል። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች ማስተካከል ከቻልን ወደዚያ እንሄዳለን። ግን ትልቁ ተግዳሮት አሁን ያለው ግን ይኼ ነው። ፖለቲካውን ማረጋጋት፣ ፖለቲካውን ወደ ሰለጠነ ፖለቲካ መውሰድ ትልቁ ተግዳሮት ነው የሚመስለኝ።

ቢቢሲ አማርኛ፦ አሁን ያለው የሀገሪቷ ነባራዊ ሁኔታ አንተ ስትሄድ ከነበረው በበለጠ የብሔርተኝነት ስሜት ናኝቶ በኦሮሚያና በአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ተቃውሞ ሲገጥማችሁ እያየን ነው። እንዲህ ባለው ሁኔታ የድጋፍ መሰረታችን የት ነው የምትሉት?

ፕሮፌ. ብርሃኑ፦ ሁለት ነገር ማንሳት እፈልጋለሁ። አንደኛ ለእኛ የሚያሳስበን ነገር ምን ያህል የፖለቲካ ድጋፍ የት እናገኛለን የሚለው አይደለም። ትልቁ የሚያሳስበው ጥያቄ ይህችን አገር እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ማድረግ ላይ ነው። ትልቁ ጉልበታችንን የምናፈስበት ጉዳይ እሱ ነው። ሁለተኛ አንድ ነገር እውነታ ሆኗል ማለት አይቀየርም ማለት አይደለም። ኢትዮጵያ እኮ ደሃ ሀገር ነች። ይሄ እውነታ ሁሌም ደሃ አገር ያደርጋታል ማለት አይደለም።

የተለያዩ ፖሊሲዎችንም ያረቀቅነው ይህንን እውነታ ለመቀየር ነው። የኢትዮጵያም የፖለቲካ እውነታ በአብዛኛው ለ27 ዓመት ይሰማው የነበረ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ብሔር ብሔረሰቦች ስሜት ውስጥ ገብተዋል ከሆነ አንደኛ ቁጥሩ ላይ መስማማት አንችልም። ምክንያቱም በተጨባጭ የምናውቀው ነገር የለም። ምን ያህሉ ሰው በዜግነት ፖለቲካ ያምናል? ምን ያህሉስ በብሔር? የሚለው ሁኔታ ላይ በተጨባጭ የተሰራም ሆነ የተሰበሰበ ጥናት የለም።

በአብዛኛው ልኂቅ በብሔር ፖለቲካ ውስጥ እንደተዘፈቀ ግልፅ ነው። ህብረተሰቡ ገብቷል ወይ? የሚለው አጠራጣሪ ነው። ሁለተኛ ብዙ ሰው ዘንግቶታል እንጂ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ኢትዮጵያ ማህበረሰቧ የተደባለቀ ነው። ንፁህና ያልተቀላቀለ ማህበረሰብ ለማግኘት አዳጋች ነው። ሦስትና አራት ትውልድ ብንቆጥር ሁላችንም ከተለያየ ብሔር ጋር የተደባለቅን ነን። እሱ ቀርቶ በአንድ ትውልድ እንኳን አባት አንድ ብሔር እናት ሌላ ብሔር ሆና የተወለደው በትክክለኛ መንገድ ቢቆጠር ከማንኛውም ከአንድ ብሔር ነኝ ከሚለው የሚበልጥ ይመስለኛል።

ይሄ ሁሉ ከዚህ የብሔር ፖለቲካና ከመጣው ግጭት መውጣት የሚፈልግ የማህበረሰብ አካል ነው። እኛ የምንለው አንደኛ እነዚህ ሃሳቦች በነፃነት የሚገለፁበት፣ ህብረተሰቡ ከስሜት ወጥቶ ለአገራችን፣ ለህዝባችን፣ ለራሳችን የሚጠቅመን የቱ ነው ብሎ በደንብ ማሰብ በሚጀምርበት ጊዜ እነኚህ ነገሮች ይቀየራሉ። የፖለቲካ ስሜት የማይቀየር በድንጋይ ላይ የታተመ ነገር አይደለም። ሁልጊዜም ይቀያየራል።

ከአርባ አመት በፊት ሁላችንም ሶሻሊስቶች ነበርን። የሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለም በተግባር ሲታይ ምን እንደሆነ ካየ በኋላ ነው ሰው ሁሉ የሚያዋጣ አለመሆኑን ተረድቶ የተቀለበሰው።

ከ27 ዓመት በፊት ይሄ የዘር ፖለቲካ ሲመጣ፤ ብሔር ብሔረሰቦች በሰላም የሚኖሩበት ብልፅግና ያለበት ሁሉም እኩል የሚሆንበት ተብሎ ነበር። አሁን ስናየው ግን ሰላምና እኩልነት የሌለበት፣ ብሔርና ብሔረሰቦች ራሳቸውን ማስተዳደር ያልቻሉበት፣ የውሸት እንደሆነ ማህበረሰቡ ተገንዝቦታል።

አሁን እንግዲህ መጪውን ጊዜ ሰው ቁጭ ብሎ ማሰብ የሚጀምርበት ጊዜ ነው። በነፃነት ማሰብ፣ መወያየትና ሃሳቦቹን ለህብረተሰቡ ማቅረብ ከቻልን እኔ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊያን በዜግነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ይመርጣሉ ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ አያስፈራኝም!

ስለዚህ ትልቁ ነገር እኛ እንደ ፓርቲ ምን ያህል ድምፅ እናገኛለን፣ የቱጋ እናሸንፋለን የሚለው አይደለም፤ ጥሩ የፖለቲካ ምህዳር ተፈጥሮ ሁሉም ሃሳቦች በነፃ የሚንሸራሸሩበት፤ በውሸት ስሜት ህብረተሰብን ማነሳሳት የሚቀርበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንፈልጋለን።

ስሜት፣ መገፋፋትና ዘላቂ ጥቅምህን ማወቅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ቀስ ብለው ሰዎች መወያየት ሲጀምሩም ነው ለእኔ፣ ለቤተሰቤ የሚበጀኝ፤ ዘላቂ ጥቅሜ ምንድን ነው? ብለው ማሰብ የሚችሉት። በዚያ ጉዳይ ላይ የዜግነት ፖለቲካ ከምንም ነገር በላይ ለዚች ሀገር ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና መሰረት እንደሆነ ጥያቄ የለንም። ለዚሀም ነው ዛሬ ባይሆን መቼም ወደፊትም የዜግነት ፖለቲካ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የማናስገባው።

ቢቢሲ አማርኛ፡ ኤርትራውስጥ ስትንቀሳቀሱ በነበረበት ወቅት ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር የነበራችሁ ግንኙነት ምንድን ነው?

ፕሮፌ. ብርሃኑ፡ ኤርትራ በነበርንበት ጊዜ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር ጋር ተገናኝተን አናውቅም። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባላት ጋር [ማለትም] ከተራ አባላት ጋር በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ከተለያዩ ሰዎች ጋር እንገናኛለን። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የመጡ ብዙ የኦሮሞ ተወላጅ አባሎች ነበሩን፤ አሉን።

ከብሔር ውጪ የሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ክፍት የሆነ ድርጅት ስለሆነ ከየትም አማራም፣ ትግሬም፣ ኦሮሞም የሚገባበት ድርጅት ነው። ብዙም ችግር ስላልነበረ ብዙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጋዮች የነበሩ አባሎች ነበሩን። እኛም ጋር አባል ሳይሆኑ ኤርትራ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ብዙ የኦሮሞ ወገኖቻችን ጋር በጓደኝነት፣ በወዳጅነት ስንሠራ ነበር።

ከኦነግ ከወጡት ከእነ ከማል ገልቹ፣ ኮለኔል አበበ ጋር ብዙ ጉዳዮች ላይ አብረን እንወያያለን። ለሀገራችን የሚሻለው ምንድን ነው? የሚሉ ነገሮች ላይ እንወያያለን። እንደ ድርጅት ከዚህ በፊት ጀምሮና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም ከሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ጋር አብረን እንሠራ ነበር። ከኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፍሮንት ጋር በጋራ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የሚል ፈጥረን ስንንቀሳቀስ ነበር። ከነከማል ገልቹ ጋርም ተመሳሳይ ነበር።

ስለዚህ ለእኛ ኦሮሞ ሆነ፣ ትግሬ ሆነ፣ አማራ ሆነ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። እንደ ድርጅት የሀገሪቱን አንድነትና ለሁሉም ሕዝቦቿ እኩል የሆነች ሀገር እንድትሆን የሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጋር አብረን እንሰራለን። አሁንም የኦሮሞ ወገኖቻችን ድርጅታችን ውስጥ አባል ናቸው።

አሁን ካለው በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ ጋር ኤርትራ ከገባን ሳይሆን ከሰባት፣ ስምንት ዓመት በፊት እንዴት በጋራ አብሮ እንደሚሠራ ውይይት ነበረን። ከዚያ በኋላ እዛም ውስጥ ችግሮች ነበሩ። እኛ ከበፊትም የነበረን ግልጽ የሆነ አንድ አቋም ነው። ለአገር አንድነት ቅድሚያ መስጠት አለብን። እንደ ሀገር አንድ ካልሆንን በጋራ ፖለቲካ መሥራት አንችልም የሚል አቋም ነው። ከማንኛውም ድርጅት ጋር ስንሠራ የምንለው በኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት ታምናለህ? በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ታምናለህ? ነው። ከዚያ በኋላ ሌላውን ውይይት ማድረግ፤ መደራደርም እንችላለን።

ለመጨረሻ ጊዜ አቶ ዳውድን ያገኘሁት ወደ ኤርትራ ለአንድ ጉዳይ ስመለስ ኤርፖርት ውስጥ ነው። ሰላም እንባባላለን። እዚህም ተገናኝተናል። በፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች ውይይት ውስጥ ገንቢ የሆነ ውይይት እናደርጋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ይቺ አገር የጋራችን ነች። ለሁላችንም የምትሆን ሀገር መፍጠር ነው። የተሻለ ሀሳብ አለን የሚሉ ሀሳባቸውን ለማኅበረሰቡ አቅርበው በዚያ በሚደረግ ውይይት ሕዝብ የመረጠውን መቀበል ግዴታችን ነው።

ሁላችንም መረዳት ያለብን በአንድ ሀገር ውስጥ ሦስት ወይም አራት የታጠቁ ኃይሎች ሊኖሩ አይችሉም። ፖለቲካ እንደዛ ሊሆን አይችልም። በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካችንን እንሠራለን ብለን ካሰብን፤ ሁላችንም መሳሪያ አውርደን እንገባለን ነው ያልነው። ስለዚህ አውርደን በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካው ውስጥ ገብተን ለሀገራችን ይበጃል የምንለውን ለኅብረተሰቡ አቅርበን ሕዝቡ የሚወስነውን መቀበል ነው።

ቢቢሲ አማርኛ፡ ከፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ያገኟቸውስ መቼ ነው?

ፕሮፌ. ብርሀኑ፡ መጨረሻ የተገናኘነው ነሀሴ ላይ ነው። ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት ለመሰነባበት ተገናኝተን በሀገራችን በአካባቢያችን ጉዳዮች ላይ አውርተናል።

ቢቢሲ አማርኛ፡ ምን አይነት ግንኙነት ነበራችሁ?

ፕሮፌ. ብርሀኑ፡ እሳቸው ፕሬዘዳንት ናቸው። እኔ አንድ ታጋይ ነኝ። ስለዚህ ምን ግንኙነት ይኖረናል? አንዳንድ ጊዜ እንገናኛለን። በሀገርና በአካባቢ ጉዳይ እናወራለን። ግን ከእሳቸው በታች ያሉ በእኛ ሥራ ዙሪያ አብረናቸው የምንሠራ ሌሎች ሰዎች አሉ። ፕሬዘዳንቱ ፕሬዘዳንት ናቸው፤ በየጊዜው እየሄድኩ እሳቸውን የማገኝበት ሁኔታ የለም።

ቢቢሲ አማርኛ፡ለወደፊት ጡረታ ወጥተውስ ምናልባት በሲቪል ወይም በቢዝነስ ዘርፍ ሲተፉ ራስዎን ያያሉ?

ፕሮፌ. ብርሀኑ፡ በጣም አያለሁ። የጀመርነው፣ በጣም ብዙ ሰው የሞተበት፣ የተጎዳበት፣ ይቺን ሀገር ዴሞክራሲያዊ የማድረግ ነገር በደንብ መሰረት ከያዘ በኋላ ለረዥም ጊዜ ፖለቲካ ውስጥ የመቆየት ፍላጎት የለኝም። በ94 [በአውሮፓውያኑ] ስመጣም ፖለቲካ ውስጥ ልገባ አልነበረም። አስተምር ነበር። በኢኮኖሚው ዙሪያ እሳተፍ ነበር። ጋዜጦች ላይ እጽፍ ነበር። የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበር ውስጥ እሠራ ነበር። ፖለቲካ የሚባል ነገር ውስጥ ተመልሼ እገባለሁ አላልኩም።

በልጅነቴ ኢሕአፓ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ተመልሼ [ፖለቲካ ውስጥ] እገባለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። በአንድ መልኩ ወይም በሌላ ፖለቲካ ውስጥ መልሶ ያስገባኝ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለተማሪዎች ስለ አካዳሚክ ነጻነት ንግግር ካደረግን በኋላ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር ስንታሰር ነው። እንዲህ አይነት ሥርዓት ካለ፣ ነጻነት ከሌለ፣ በነጻነት መነጋገር ካልተቻለ ሌሎች የሚሠሩ ሥራዎችም የውሸት ይሆናሉ።

አካዳሚሽያን [ትምህርታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ባለሙያ] ነኝ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አስተምራለሁ ብለህ ነጻነት ከሌለህ፣ የምታስተምረውን ነገር በነጻነት ማስተማር ካልቻልክ፤ የምታስተምረው በተወሰነ ደረጃ የውሸት ነው የሚሆነው። የፖለቲካ ሥርዓቱ ለፖለቲካ ስልጣን ሳይሆን ለዕለት ተዕለት ሥራዎች እንኳ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አይደለም።

ባለፈው 27 ዓመት ውስጥ ነጋዴ ብትሆን የሚያሳብድ ነው የሚመስለኝ። ንግድ ማለት የውድድር ቦታ ከሆነ፤ የኢኮኖሚው ሥርዓት ሙሉ በሙሉ በአድልዎ ላይ የተመሰረተ ከሆነ ምንም ልትነግድ አትችልም። አንተንም ከፀባይህ አውጥተው እንደነሱ አጭበርባሪ ሆነህ የምትኖርበት ሁኔታ ነው የሚፈጠረው።

እንደ አንድ እውነተኛ ዜጋ ለመኖር የፖለቲካ ምህዳሩ ነጻነትህን የሚያከብር፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሀሳብህን በነጻነት መግለጽ መቻልህ፣ በምትሠራው ሥራ ጣልቃ የማይገባ መሆኑ አስፈላጊ ነው። ከብዙ ሰዎች ጋር የምለየው በዚህ ነው። እነሱ ይሄ ፖለቲካ ውስጥ መግባት ነው የሚመስላቸው። እኔ ፖለቲካ ውስጥ መግባት አልለውም። ይሄ መሰረታዊ የሆነ ዜግነትህን ማስከበር ነው።

ኢትዮጵያዊ ነኝ ካልኩ እንደ ኢትዮጵያዊ ይገባኛል የምለው መሰረታዊ ነጻነት አለ። ያንን ካላገኘሁ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም። ከዚህ ጠፍቼ፤ ከዚህ ሸሽቼ አሜሪካና አውሮፓ የምኖር ጊዜ ያለኝ ነጻነት ሀገሬ ውስጥ ካለው ነጻነት የበለጠ ከሆነ እውነተኛ ዜጋ አይደለሁም። ፖለቲካ ውስጥ ያስገባኝ ይሄ ነው።

እስር ቤት ከገባን በኋላ በጣም ብዙ ኦሮሞ ወገኖቻችን ታስረው ሳይ ሀገሪቱ ወደ ምን አይነት አደጋ ውስጥ እየገባች እንደሆነ ነው ያየሁት። አሁንም ለእኔ ፖለቲካ ማለት እነዚህን መሰረታዊ የሆኑ የዜግነት መብቶች ማስከበር፤ ሁሉም የሀገሩ ባለቤት የሚሆንበት ድባብ መፍጠር ነው። ይሄ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታችን ነው።

ያንን ማድረግ ካልቻልክ፤ የዜግነት መብትህን እየወረወርክ ነው። ይህንን በፍጹም ማንኛውም ዜጋ ማድረግ የለበትም ብዬ አምናለሁ። ለእኔ ፖለቲካ የሚያያዘው ከዚህ ጋር ነው። ከዚያ በኋላ ያለው ምርጫ ምናምን አድካሚውና በፍጹም የማይረባው የፖለቲካ ክፍል ነው። ዋናው ሥራ ካደረስኩ በኋላ ለጡረታም ደርሻለሁ፤ ትንሽ የማርፍበት ጊዜ ነው።

Source ፡ bbc

]]>
National Reconciliation Commission to be accountable to the Prime Minister once it is established https://konjoethiopia.com/2018/12/26/%ef%bb%bfnational-reconciliation-commission-to-be-accountable-to-the-prime-minister-once-it-is-established/ Wed, 26 Dec 2018 14:31:42 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1229 National Reconciliation Commission to be accountable to the Prime Minister once it is established December 25,2018 In its 14th regular session for the year, the Ethiopian Parliament has approved today a bill drafted to establish National Reconciliation Commission. The idea was discussed by the council of ministers sometime in mid November of this year. The commission is […]]]>

National Reconciliation Commission to be accountable to the Prime Minister once it is established

National Reconciliation Commission
Ethiopian Parliament Building


December 25,2018

In its 14th regular session for the year, the Ethiopian Parliament has approved today a bill drafted to establish National Reconciliation Commission.

The idea was discussed by the council of ministers sometime in mid November of this year.

The commission is tasked to get to the bottom of grudges, political or otherwise, and come up with a recommendation for reconciliation and implement it.

The new body is made accountable to the office of the Prime Minister which generated some intense debate among parliamentarians.

Those who argued in favor of making the commission accountable to Abiy Ahmed explained their view by pointing out that the parliament has control over it for it is the same body that will appoint members of the commission. Yet, it is the prime minister that nominates members of the commission and presents them to the parliament.

EBC also reported that the commission will get legal support, and protection, so as to make it free from any form of influence.

According to a report by government media, Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC), members of the parliament demonstrated divergence on the issue of reconcilliation itself.

There were opposing voices in Ethiopia’s 547 seat parliament as some saw the idea of establishing National Reconciliation Commission as irrelevant on grounds that “no Ethiopian entity or entities are in conflict and hence in need of no reconciliation.”

On the other hand there were those who emphasized the idea that reconciliation is even more important than justice if the approach to it is right.

Members who could belong to the latter group went to the extent of asserting that reconciliation is good even from the point of view of the situation in the parliament- perhaps a hint about the difference between champions of what is now old system under TPLF and champions of reform, and change in Ethiopia.

Finally, the Bill passed after a vote was administered on it in the house. One Member of Parliament voted “no” and one parliamentarian abstained.

Outside of the context of debate in the parliament, the idea of truth and reconciliation, for many Ethiopians, seem to be relevant in view of what has happened in Ethiopia in the past 27 years.

Others tend to stretch back in history, and these are mostly ardent patrons of ethnic politics who seem to have politically charged interpretations of history that sees Ethiopia’s past in black and white to justify a view of ethnic repression for purposes of ethnic politics, to affirm the importance of reconciliation.

However, even ethno-nationalist parties like Oromo Democratic Party, which is governing Oromo region of Ethiopia, have revised their view of history and reached at the conclusion that there was no ethnic oppression in the history of Ethiopia – a view similar to Ethiopian revolutionaries who carried out the 1974 Ethiopian revolution which toppled the imperial government of Ethiopia.

Source ፡ borkena

]]>
ህወሓት ከፌደራል ተሸንፎ ነው የመጣው፤ በጣም ችግር ላይ ነው ያለው ፡፡ ( አምዶም ገ/ስላሴ ) https://konjoethiopia.com/2018/12/26/%e1%88%85%e1%8b%88%e1%88%93%e1%89%b5-%e1%8a%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b0%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%89%b0%e1%88%b8%e1%8a%95%e1%8d%8e-%e1%8a%90%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8c%a3%e1%8b%8d%e1%8d%a4-%e1%89%a0/ Wed, 26 Dec 2018 12:01:28 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1226 • ህወሓት ከፌደራል ተሸንፎ ነው የመጣው፤ በጣም ችግር ላይ ነው ያለው፡፡ የቆየው በጠመንጃ፣ በደህንንት፣ በፖሊስ እና በገንዘብ ኃይል ሲሆን፤ የትግራይን ሕዝብ ፍላጎት የማያሟላና ለማስተዳደር የማይበቃ ድርጅት ነው፡፡ • ኤፈርትን በሃላፊነት ያገለገሉት አቶ ስብሀት ነጋ መድረኩ ላይ ስለነበሩ ባያቋርጡኝ ድርጅቱን በተመለከተ ለመናገር ነበር ያሰብኩት፡፡ ከኤፈርት ጋር በተያያዘ የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ እንደሆነ ተደርጎ ይወራል፡፡ ህወሓት ድርጅቱን ለራሱ […]]]>

• ህወሓት ከፌደራል ተሸንፎ ነው የመጣው፤ በጣም ችግር ላይ ነው ያለው፡፡ የቆየው በጠመንጃ፣ በደህንንት፣ በፖሊስ እና በገንዘብ ኃይል ሲሆን፤ የትግራይን ሕዝብ ፍላጎት የማያሟላና ለማስተዳደር የማይበቃ ድርጅት ነው፡፡

• ኤፈርትን በሃላፊነት ያገለገሉት አቶ ስብሀት ነጋ መድረኩ ላይ ስለነበሩ ባያቋርጡኝ ድርጅቱን በተመለከተ ለመናገር ነበር ያሰብኩት፡፡ ከኤፈርት ጋር በተያያዘ የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ እንደሆነ ተደርጎ ይወራል፡፡ ህወሓት ድርጅቱን ለራሱ ነው መጠቀሚያ ያደረገው፡፡

• በአማራው ክልል አዴፓ እና በህወሓት መካከል ያለው የስልጣን ሽኩቻ የሁለቱን ክልሎች ሕዝቦች ያጋጫል፤ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ብለን እንገምታለን፡፡

• የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ምንም አይነት ጥያቄ የሚነሳበትና የሚያነሳም ሕዝብ አይደለም፤ ሀገሩን ትቶ ወደየትም አይሄድም፡፡

• የትግራይ ተወላጆች በአማራ፣ በኦሮሚያና በሌሎችም ክልሎች ጥቃት እየደረሰባቸው ነውና ይሄን ጉዳይ በጽኑ ነው የምንቃወመው፡፡ ህወሓት ግን ይህን ይፈልገዋል፡፡ ምክንያቱም እኔ ከሌለሁ ያጠፉሀል የሚል ፕሮፓጋንዳ በመስራት ይጠቀምበታል፡፡

የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉአላዊነት (አረና) ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ካደረገው ቃለምልልስ የተወሰደ ሙሉ ቃለምልልሱን በነገው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይጠብቁ ።

]]>
ODP Blames OLF for Failing to Implement Recent Agreement to Pacify Oromia https://konjoethiopia.com/2018/12/25/odp-blames-olf-for-failing-to-implement-recent-agreement-to-pacify-oromia/ Tue, 25 Dec 2018 15:06:22 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1220 E Addis Ababa December 25/2018 The peace agreement reached between the Oromo Democratic Party (ODP) and Oromo Liberation Front (OLF) to pacify Oromia a month ago has expired without bearing fruit due to the unwillingness of OLF, Mogos Edeo of ODP said. According to him, a committee was put to task to prepare a joint […]]]>

E

Addis Ababa December 25/2018 The peace agreement reached between the Oromo Democratic Party (ODP) and Oromo Liberation Front (OLF) to pacify Oromia a month ago has expired without bearing fruit due to the unwillingness of OLF, Mogos Edeo of ODP said.

According to him, a committee was put to task to prepare a joint plan of action that would enable both organizations to maintain peace, fight maladministration, disarm OLF fighters, and sustain peaceful struggle among the parties on 26 November 2018.

The party representative said the two parties have earlier inked an agreement and established a committee comprising of six members drawn from both parties to monitor the implementation of the agreement.

Talking to journalists today, the final day for presenting joint report to the public about the implementation of the agreement, Mogos added that OLF failed to keep its promises and cooperate.

The representatives pointed out that the committee was established based on the suggestion from religious fathers and elders to facilitate a dialogue for constructive engagement by both parties.

OLF representatives reached by ENA said they are unable to respond to queries for the time being.

Mogos also said the government has been giving professional training for around 1,300 OLF disarmed forces.

]]>
ከሴራ ፖለቲካ ማንም አያተርፍም ! https://konjoethiopia.com/2018/12/23/%e1%8a%a8%e1%88%b4%e1%88%ab-%e1%8d%96%e1%88%88%e1%89%b2%e1%8a%ab-%e1%88%9b%e1%8a%95%e1%88%9d-%e1%8a%a0%e1%8b%ab%e1%89%b0%e1%88%ad%e1%8d%8d%e1%88%9d/ Sun, 23 Dec 2018 14:32:07 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1204 የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምኅዳር ካበላሹት በርካታ ከንቱ ነገሮች መካከል አንዱ ሴረኝነት ነው፡፡ ሴረኝነት የኢትዮጵያን መልካም አጋጣሚዎች ከማበላሸት አልፎ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈ፣ ያሰቃየ፣ ለስደት የዳረገና ተስፋ ያስቆረጠ ነው፡፡ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከ1953 ዓ.ም. መፈንቅለ መንግሥት ማግሥት ጀምሮ እስካሁን ድረስ የሴረኞች ሰለባ ነው፡፡ በአገሪቱ ፖለቲከኞች መካከል እርግማን ያለ ይመስል ከመነጋገርና ከመደራደር ይልቅ መተናነቅ፣ ዕውቅና […]]]>

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምኅዳር ካበላሹት በርካታ ከንቱ ነገሮች መካከል አንዱ ሴረኝነት ነው፡፡ ሴረኝነት የኢትዮጵያን መልካም አጋጣሚዎች ከማበላሸት አልፎ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈ፣ ያሰቃየ፣ ለስደት የዳረገና ተስፋ ያስቆረጠ ነው፡፡ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከ1953 ዓ.ም. መፈንቅለ መንግሥት ማግሥት ጀምሮ እስካሁን ድረስ የሴረኞች ሰለባ ነው፡፡ በአገሪቱ ፖለቲከኞች መካከል እርግማን ያለ ይመስል ከመነጋገርና ከመደራደር ይልቅ መተናነቅ፣ ዕውቅና ተሰጣጥቶ ከመፎካከር ይልቅ መጠላለፍና መጠፋፋት ለዓመታት የዘለቀ በሽታ ነው፡፡ ይኼንን ዓይነቱን ኋላ ቀርነትና ጨለምተኝነት በጣጥሶ ለአገር ሰላም፣ ዴሞክራሲና ዕድገት ከመጨነቅ ይልቅ አሁንም በሴራ ፖለቲካ መሻኮት ቀጥሏል፡፡ ይህ የዘመናት ሕመም በገዥው ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ከፍተኛ ውጥረት ፈጥሯል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በገዥው ኦዴፓና በቅርቡ ወደ አገር ቤት በተመለሰው ኦነግ መካከል መኳረፍ አሳይቷል፡፡ በሌሎች አካባቢዎችም ውስጥ ለውስጥ የሚብስለሰሉ ነገሮች አሉ፡፡ ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ የተረፈው ሽኩቻ በየቦታው ግጭቶች እየቀሰቀሰ የንፁኃን ደም በከንቱ ይፈሳል፡፡ ሕፃናት፣ እመጫቶች፣ ነፍሰ ጡሮች፣ አዛውንቶችና አቅመ ደካሞች ይፈናቀላሉ፡፡ በሴረኞች ምክንያት የሕዝብ ሕይወት ይመሰቃቀላል፣ አገር ትቃወሳለች፡፡

እስካሁን የተመጣበት መንገድ የሕዝብን ምሬት ከመጠን በላይ በማድረጉ ምክንያት ለሦስት ዓመታት ያህል ድብልቅልቁ በወጣ ለውጥ አገሪቱ ስትናጥ ከርማ፣ ካለፉት ዘጠኝ ወራት ወዲህ አገሪቱ አዲስ የለውጥ ጉዞ ጀምራለች፡፡ ይህ ጉዞ ግን በበርካታ ፈተናዎች ተከቦ በሕዝብ ድጋፍ እዚህ ቢደርስም፣ አሁንም እጅግ በጣም የሚያሳስቡ ችግሮች ተጋርጠዋል፡፡ አልፎ አልፎ የሚፈጸሙ ስህተቶች ቢኖሩ እንኳ ይታረማሉ በሚል መንፈስ ሕዝብ አሁንም ለውጡን ደግፎ፣ አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድትሸጋገር ዕገዛ እያደረገ ነው፡፡ ይኼንን የሕዝብ የለውጥ መንፈስ በመጋራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንባር ቀደም አመራር መስጠት ሲገባቸው፣ አሁንም ብዙዎቹ እያንቀላፉ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አንድም ጠመንጃ ሳይተኩሱ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በዘንባባ ዝንጣፊ አቀባበል ከተደረገላቸው መካከል፣ ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግሉ የማይመጥን ድርጊትና ባህሪ እያሳዩ ያሉ አሉ፡፡ ከበርካታ ዓመታት ስደት በኋላ በተፈጠረው መልካም አጋጣሚ ወደ አገር ቤት ከተመለሱ በኋላ፣ ይኼንን መልካም አጋጣሚ ለማምከን መሯሯጥ ምን የሚሉት ነው? ከሰላማዊ የፖለቲካ የጨዋታ ሕግ በማፈንገጥ ትርምስ መፍጠር ምን ዓይነት ትርፍ ያስገኛል? ችግሮችን በሰከነ መንገድ መፍታት? ወይስ የተለመደው አዙሪት ውስጥ ገብቶ መፃኢ ዕድልን ማጨለም? ይህ በፍጥነት ምላሽ የሚፈልግ ጥያቄ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ የትም የማያደርስ የሴራ ፖለቲካ ታክቶታል፡፡ ሕዝብን ከድህነት፣ ከኋላ ቀርነትና ከጨለማ ውስጥ የማያወጣ ሴረኝነት፣ አገርን አተራምሶ ቀውስ ከመፍጠር የዘለለ ፋይዳ እንደሌለው ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ትናንት አምባገነንነት አገርን ቆላልፎ መላወሻ በማሳጣቱ ምክንያት የተከፈለው መስዋዕትነት ሳያንስ፣ ጥቂቶችን ሥልጣን ላይ በአቋራጭ ጉብ ለማድረግ ንፁኃንን ዕልቂት ውስጥ ለመክተት የሚደረገው ሰይጣናዊ ድርጊት መቆም አለበት፡፡ ከግለሰቦችና ከቡድኖች በላይ የሥልጣን ሉዓላዊ ባለቤት የሆነ የተከበረና የታፈረ ሕዝብ መኖሩን መዘንጋት ነውር ነው፡፡ ከምንም ነገር በላይ አገር የምትባል የጋራ ጎጆ መኖሯን ችላ ማለት ፀያፍ ነው፡፡ ከፖለቲካ ፓርቲ በላይ ሕዝብና አገር መኖራቸውን የማይረዳ ፖለቲከኛም ሆነ የፖለቲካ አቀንቃኝ ራሱን መመርመር ይኖርበታል፡፡ የሴራና የአሻጥር ፖለቲካ የኋላቀርነት መገለጫ ነው የሚባለው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ይህ ያለንበት ዘመን ለሐሳብ አፍላቂዎች ብቻ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ፣ የዳበረ አስተሳሰብ ያላቸው በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ይፎካከራሉ፡፡ የሐሳብ ልዕልና የሌላቸው ደግሞ ሴራ እየጎነጎኑ አገር ስለሚያምሱ ፋይዳ ቢስ ናቸው፡፡

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ሕግ ማክበርን ይጠይቃል፡፡ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር አካላት ውጤታማ ሆነው እንዲሠሩ ዕገዛ ይፈልጋል፡፡ የዴሞክራሲ ተቋማት ጠንክረው ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት ሥርዓት እንዲፈጥሩ እንረዳዳ ይባልበታል፡፡ የፍትሕ ሥርዓቱ ነፃና ገለልተኛ እንዲሆን፣ ከማንም ያልወገነ የምርጫ ቦርድ እንዲመሠረት፣ ሚዲያው በነፃነትና በገለልተኝነት እንዲሠራ፣ የፀጥታ ኃይሎች የማንም ተቀጥላ ሳይሆኑ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ ወዘተ መሠረቱን በጋራ እንጣል ይላል፡፡ የሕግ የበላይነት በሚገባ ሰፍኖ ሕገወጥነት ሲመክን የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ፡፡ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት የሚወዳደሩበት ዴሞክራሲያዊ ምኅዳር ይፈጠራል፡፡ እነዚህ መልካም ነገሮች በኢትዮጵያ ምድር በተግባር እንዲታዩ የበኩልን ማዋጣት ሲገባ፣ ሰላምና መረጋጋት የሚያደፈርስ ድርጊት ውስጥ መገኘት ያስነቅፋል፡፡ በተለይ በዚህ ወቅት ችግሮች ቢያጋጥሙ እንኳ ቅድሚያ ለመነጋገርና ለመደራደር መስጠት ይገባል፡፡ ከዚህ ውጪ በማናለብኝነት ስሜት መፎከርም ሆነ እንዳሻ ለመሆን አቧራ ማስነሳት ከሕዝብ ጋር ያጣላል፡፡ ይህ ደግሞ አትራፊ አይደለም፡፡

ዘወትር እንደምንለው የአገር ህልውና ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ የአገሪቱ ችግሮች ደግሞ በጣም ብዙና ውስብስብ ናቸው፡፡ ተራማጅ ኃይል አገሪቱን ካለችበት አረንቋ ውስጥ አውጥቶ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሲለፋ፣ ለሚያጋጥሙ ችግሮች በጋራ መፍትሔ እየፈለጉ አብሮ መሥራት ሲገባ እንደ ጠላት ማደናቀፍ ያሳዝናል፡፡ ሕዝብ የአምባገነንነትና የጭቆና ኑሮ ሰለቸኝ ብሎ ትናንት በእንቢታው ነፃ ያወጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጭምር መሰናክል  ሲሆኑ፣ ወዴት እየመለሳችሁኝ ነው ብሎ ጥያቄ ማንሳቱ አይቀርም፡፡ ይኼንን ጥያቄ ደግሞ አድበስብሶ ማለፍ አይቻልም፡፡ የዘመናት ውስብስብ ችግሮች የሚፈቱት በሴራ ፖለቲካ ሳይሆን፣ ለሕዝብ ጥቅምና መብት የሚበጀውን በማመላከትና ለተግባራዊነቱም ተግቶ በመሥራት ብቻ ነው፡፡ ከዚያ ወጪ ለአቋራጭ ሥልጣን ተብሎ ለሕዝብ የማይበጅ አጀንዳ አንግቦ መዞር ለትርፍ ሳይሆን ለኪሳራ ይዳርጋል፡፡ የሴራ ፖለቲካ ጠልፎ ሲጥል እንጂ አንድም ቀን ድል ሲያጎናፅፍ እንዳልታየ ታሪክ ብርቱ ምስክር ነው፡፡ ሕዝብ የሚፈልገው ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት ነው፡፡ እነዚህን ዕውን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ትግል ብቻ ነው፡፡ ከሴራ ፖለቲካ ማንም አያተርፍም !

( ከሪፖርተር ርእሰ አንቀጽ የተወሰደ )

]]>
ሸህ ሁሴን ጅብሪል ከ100 አመት በፊት ስለ ዶ/ር አብይ አህመድ የተናገሩት ትንቢት ። https://konjoethiopia.com/2018/12/21/%e1%88%b8%e1%88%85-%e1%88%81%e1%88%b4%e1%8a%95-%e1%8c%85%e1%89%a5%e1%88%aa%e1%88%8d-%e1%8a%a8100-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8d%8a%e1%89%b5-%e1%88%b5%e1%88%88-%e1%8b%b6-%e1%88%ad/ Fri, 21 Dec 2018 15:34:24 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1198 መቼም በያ ሰሞን ያለብን አበሳ ፤ አንድ ጀግና ጎበዝ ከጅማ ሲነሳ ፤ ተሃት ትሆናለች እንደሙት ሬሳ ። መልኩ ልጅ ኢያሱን ፤ ንግግሩ ሸጋ ፤ ፈገግታው ያማረ ፤ አህላቁ የረጋ ፤ ህልቁ ይወደዋል ከቆላ እስከ ደጋ ። በምስራቅ በምእራብ ፤ በደቡብ ባገሩ ። ሁሉም የሚወደው ፤ አንደበተ ጥሩ ፤ ሰሜን ይጠላዋል ፤ አጀብ ነው ምስጢሩ ። […]]]>


መቼም በያ ሰሞን ያለብን አበሳ ፤
አንድ ጀግና ጎበዝ ከጅማ ሲነሳ ፤
ተሃት ትሆናለች እንደሙት ሬሳ ።
መልኩ ልጅ ኢያሱን ፤ ንግግሩ ሸጋ ፤
ፈገግታው ያማረ ፤ አህላቁ የረጋ ፤
ህልቁ ይወደዋል ከቆላ እስከ ደጋ ።
በምስራቅ በምእራብ ፤ በደቡብ ባገሩ ።
ሁሉም የሚወደው ፤ አንደበተ ጥሩ ፤
ሰሜን ይጠላዋል ፤ አጀብ ነው ምስጢሩ ።
ወሎ ተደስቶ ፤ ሲደልቅ መረባ ፤
ሰሜን አንገራግራ ፤ ስትል ወጣ ገባ ፤
ይመሽግባታል፤ ዝንጆሮና ሌባ ።
እንደ ልጅ ኢያሱ ፤ እንደ ወሎው ልጅ ፤
አይኑ አራት አይና ነው ላገር የሚበጅ ፤
ምቀኛ በዝቶበት ይቸገራል እንጅ ።
ምቀኛው ከማጀት፤ ከገዛ መንደሩ ፤
ትንሽ ያውኩታል አንገዛም ብለው እያንገራገሩ ፤
ባይሆን ይቀጠፋል ኡምራቸው ባጭሩ ።
ከሶስት አመት ሃላ ፤ ለአለም የሚበጅ ይጠናል ወንበሩ ።
ቀልብያው የኢያሱ ወኔው የአባ ጀቦ ፤
በጠላት ዙሪያውን በሂስድ ተከቦ ፤
መስሏቸው ገራገር ፤ ደርሰው ሲሃስዱ ፤
እንደ አቤቶ ኢያሱ ፤ አይችሉም ሊያወርዱ፤
በሴራ አይንዱትም ሺህ ቢረማመዱ ፤
አይነቀንቁትም ሴራ ቢገምዱ ፤
ከሰማይ አውርዶ ፤ ወንበሩን የሰጠው ፤ አላህ ነው ዘመዱ

Credit ፡ Mengistu Zegeye

]]>