Take a fresh look at your lifestyle.

” አዲስ ፓርቲ አይደለሁም “

ኦነግ በቃል አቀባዩ በአቶ ቶሌራ ዳባ አማካኝነት እንዳስታወቀው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር  ፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ መዝገብ  በ1983 ዓ.ም በሕግ ስለተመዘገበ አሁን ድጋሚ አይመዘገብም  ሲል ያቀረበውን አቤቱታ አዲሷ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ  ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ውድቅ አድርገውታል ። አዲስ ፓርቲ አይደለሁምና ድጋሚ መመዝገብ የለብኝም ሲል መከራከሪያ ይዞ የቀረበው የኦሮሞ…

ከብዕር ይልቅ ዱላ የቀለለውን የዩንቨርሲቲ ተማሪ እና የነገዋ ኢትዮጵያ ሳስብ (በያሬድ ሃ/ማርያም )

ጋብ ብሎ የነበረው በዩንቨርሲቲዎች ውስጥ የሚታየው ተማሪዎች በጎጥ እየተደራጁ የመቧቀስ የኋላ ቀርነት አዙሪት ይህን ሳምንት ደግሞ እንደ አዲስ አገርሽቶ መታየቱ እጅግ አሳዛኝም፤ አሳሳቢም ነው። ዩንቨርሲቲዎች የምርምር፣ የእውቀት፣ የጥበብ እና የመፈላሰፊያ መንደሮች ናቸው። የዩንቨርሲቲው ማህበረሰብም አቅሙ የሚለካው በሰነቀው እውቀቱ፣ ባደረገው ምርምር እና የምርምር ውጤት ወይም…

የመንደር አምባገነነኖችን ማስታመምና ማስተናገዱ እስከመቼ ?! ( በነአምን ዘለቀ የግንቦት 7 አመራር )

 ህግና ስርአት  መከበር አለበት፡ የፌደራል መንግስታና የክልል አስተዳደሮች ስረአተ አልበኞችን ብቻ ሳይሆን በታችኛው እርከን ላይ የሚገኙ የአስተዳደርና የደንነት ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።  እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ የመኖር፡ የመንቀስቀስ፣ የመናገር፣ የመደራጀት፣ የማደረጀት፣ የመስብሰብ ፓለቲካዊና  የሲቪል መብቶች ሙሉ በሙሉ…

የአሶሳ ኒቨርስቲን ሰላም ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን የዩኒቨርስቲዉ ቦርድ አስታወቀ ።

በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀሰዉ ግጭት በተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳትና ሞት መድረሱ ይታወሳል፡፡ በዩኒቨርስቲዉ የመማር ማስተማር ሂደትም ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ አሁን ግጭቱን ተከትሎ ግቢዉን ለቀዉ የወጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዉ አንፃራዊ ሰላም በመኖሩ በመመለስ ላይ መሆናውን በቦታው የሚገኘው የአቢሲ ሪፖርተር ያለለት ወንድዬ ዘግቧል ፡፡ በዩኒቨርስቲዉ አሁን…

“ነጭ የለበሰ ‘መልአክ’ በኦሮምኛ አናገረኝ”- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ

ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለየች የሚባለው መቼ ነው? ምን ሲሆን? አቶ ሂርጳ ነገሮ ለዚህ ፍንጭ ሊሰጡን የሚችሉ ሁነኛ ሰው ናቸው፤ የቅርብ ጊዜ ምሥክር። ትውልዳቸው ከወደ ምሥራቅ ወለጋ ሲቡ ስሬ ወረዳ ነው። ዘለግ ላለ ጊዜ በጽኑ ታመው ቆይተዋል። ከ2 ዓመት በፊት ሆድ ዕቃቸው ተከፍቶ በቀዶ ጥገና ታክመዋል። የጤና ታሪካቸው በአጭሩ ይኸው ነው። ማክሰኞ ረፋድ ላይ ግን…

የጠፉ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ መንገዶች፣ ድልድዮች፣ ሕንጻዎች፣ መኪኖች፣ ማሽኖች በየክልሉ የሉም ወይ?

ሲበላ ሳቀ !!! ዳንኤል ክብረት በሀገራችን ሲፈጠር የነበረው ችግር ሁሉ በአንድ አካባቢ ሰዎች ብቻ ነው ወይ የተፈጠረው? በየአካባቢው ዛፉን ሲያስቆርጡ የነበሩ ጠማማ የመጥረቢያ እጀታዎች አልነበሩም ወይ? አለቆቻቸውን ያስደሰቱ መስሏቸው ‹በጥፊ በለው› ሲባሉ ‹በጥይት በለው› እያሉ ሲተረጉሙ የኖሩ በየአካባቢው የሉም ወይ? ክልሎቹ የፌዴራሉ መንግሥት…