‘‘ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ’’ ሜጄር ጀነራል ክንፈ ለዕለቱ ዳኛ ከተናገሩት።
ሜጄር ጀነራል ክንፈ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
ሜጀር ጀነራል ክንፈ ከጡረታ የማገኘው ገንዘብ 4000 ብር ስለሆነና አቅም ስለሌለኝ የዘመድ እጅ እንዳላይ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ ሲሉ ለዳኞች አስታውቀዋል። ይህን ለማረጋገጥም ቃለ መሃላ ፈፅመዋል ።
ሜጀር ጀነራሉን ጨምሮ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የተጠርጣሪዎች ቁጥር 8 ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ስድስቱ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው። ሁለቱ ደግሞ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡ ናቸው።
ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ፍጹም የሺጥላ እና የሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም ኢሳያስ ዳኘው ይገኙበታል። በተመሳሳይ መልኩ አቶ ኢሳያስ ዳኘውም ገንዘብ ከፍለው ጠበቃ ማቆም እንደማይችሉ በመጥቀስ፤ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ጠይቀዋል።