ለኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት አዲስ አበባ ጉዳዩ ቅሬታን ስለማቅረብና እንዲፈታ ስለመጠየቅ ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቡናና ሻይ ልማት ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን በዘንድሮ አመት የሚከበረውን አለም አቀፍ የቡና ቱሪዝም ፕሮግራም ቡና መገኛ በሆነችው ካፋ ዞን እንደሚያከብሩ ገልፀው እስካሁን ሲሰራ ከመቆየቱም ባሻገር በደረ ገፃቸው ice ethiopia 18 Land of origins Ethiopia Coffe tour ካፋ ላይ ለመገናኘት መልቀቃቸው ይታወሳል ። ይህ በንዲህ እንዳለ በቅርብ ጊዜ የቡናና ሻይ ልማት ባለስልጣን ሃሳቡን ገልብጦ ጅማ ቡና መገኛ እንገናኝ ብለው መልቀቃቸው በዚሁ በመደመር ወቅት ብሄርን ከብሄር ሆን ተብሎ ታሪክ ለመቀማትና በህብረተሰብ ውስጥ ጥርጣሬ ለመፍጠር የተሰራ ሴራ መሆኑን እንገነዘባለን ።

በመሆኑም ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት የሚደረገው ጥረት ብቻም ሳይሆን በአለም የሚታወቀውን ታሪክ መሻር ከአንድ በህግ ከሚተዳደር የመንግስት ተቋም ፡ የማይጠበቅ መሆኑን ህዝባችን ይረዳል ያውቃልም ። ስለዚህ ታሪክን ማበላሸትና ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት የሚደረግ ተግባር እንዲቆምልን ተገቢው የቡና መገኛ ታሪካችን እንዲዘገብልንና ice የተሰኘው ፕሮግራም በትክክለኛ ቦታ ካፋ ዞን ማኪራ ቀበሌ ቡኒ መንደር Tour ፕሮግራም እንዲካሄድ የሚመለከተው ሁሉ የአካባቢውን ህብረተሰብ ቅሬታ ተረድቶ ተገቢው ምላሽ እንዲሰጥ እየጠየቅን ይህን ፕሮግራም አስመልክቶ በተለያየ ጊዜያት ፖስት የተደረጉ ፅሁፎችን ከዚህ ደብዳቤ ጋር አያይዘናል ።
ከሰላምታ ጋር
አስረስ አዳሮ አጦ / የመምሪያው ሃላፊ /