ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ኢትዮጵያ አዲሲቷ የተስፋ አድማስ የተሰኘ ባለ አንድ ገጽ እቅዱ ይፋ ተደርጓል ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ስር የተቋቋመው የፕሬስ ሴክሬታሪ በይፋ ስራ መጀመሩን በማስመልከት በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንደተገለፀው በአዲስ መልክ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተደራጀው መረጃ አቀባይ መስሪያ ቤት የቀድሞውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ተግባራት የሚሰራ ነው፡፡
የሚዲያ ግልፀኝነትን ለመፍጠርና ብቃት ባለው መልኩ መረጃዎችን በፍጥነት ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መደራጀቱም ታውቋል።
በዚህም መንግስት እስከ 2012 ዓ.ም ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራቸውን እቅዶች በማስትዋወቅ የተፈፃሚነታቸውን ሂደት ለመገናኛ ብዙሃንና ለህዝብ ቅርብ ለማድረግ እንደሚሰራ አዲስ በተቋቋመው የፕሬስ ሴክሬታሪ ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው በተሾሙት ወ/ሮ ቢልለኔ ስዩም ተገልፇል ።
የአንድ ገጽ እቅዱ ምን አይነት ይዘት በዚህ ምስል ላይ መመልከት ይችላሉ ።