የመንግስትን እቅድ በግልጽ ቋንቋ ለህዝብ ለማድረስ ባለ አንድ ገጽ የእቅድ ሰሌዳ (ዳሽ ቦርድ) ይፋ ተደረገ።

 

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ኢትዮጵያ አዲሲቷ የተስፋ አድማስ የተሰኘ  ባለ አንድ ገጽ እቅዱ ይፋ ተደርጓል ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ስር የተቋቋመው የፕሬስ ሴክሬታሪ በይፋ ስራ መጀመሩን በማስመልከት በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንደተገለፀው  በአዲስ መልክ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተደራጀው መረጃ አቀባይ መስሪያ ቤት የቀድሞውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ተግባራት የሚሰራ ነው፡፡
የሚዲያ ግልፀኝነትን ለመፍጠርና ብቃት ባለው መልኩ መረጃዎችን በፍጥነት ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መደራጀቱም ታውቋል።
በዚህም መንግስት እስከ 2012 ዓ.ም ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራቸውን እቅዶች በማስትዋወቅ የተፈፃሚነታቸውን ሂደት ለመገናኛ ብዙሃንና ለህዝብ ቅርብ ለማድረግ እንደሚሰራ አዲስ በተቋቋመው የፕሬስ ሴክሬታሪ ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው በተሾሙት ወ/ሮ ቢልለኔ ስዩም ተገልፇል ።

የአንድ ገጽ እቅዱ ምን አይነት ይዘት በዚህ ምስል ላይ መመልከት ይችላሉ ።