ዑጋንዳውያን ሴቶች የአልጋ ግብር/Sex Tax ጀምረዋል ።

(ጥላሁን ግርማ )

ኡጋንዳውያን ሴቶች “የአልጋ ግብር”/Sex Tax የተባለ በአይነቱ አዲስ የሆነ የግብር አይነት ያስተዋወቁ ሲሆን ይህ የግብር ዓይነት ሴቶቹ ለልጆቻቸውና ለራሳቸው የማያቋርጥ የገንዘብ ድጋፍ ማግኛ ሆኗቸዋል ይላል የዘ-ሰን ዘገባ።

ጉዳዩ የተጀመረው አንዲት ኡጋንዳዊት ሴት የሚያገኘውን ገቢ እየደበቀ በመቸገሯ ቤተሰቦቿን ለመርዳት የጀመረችው ይህ የግብር ዓይነት ዛሬ ላይ የሴቶችን መብት እንደማስከበሪያ በመላው ኡጋንዳ ተቀባይነትን አግኝቶ ከ30 ሺህ የማያንሱ ኡጋንዳውያን ሴቶች ዱርዬ ባሎቻቸው ላይ ” የአልጋ ግብር”/Sex tax መጣላቸውን አሳውቀዋል።

በሥራዋ መምህር የሆነችው አኔት ናኖዚ ባሏ ገቢውን እየደበቀና ለልጆች ማሳደጊያ የሚሆን ገንዘብ እየከለከለ በሚሰራው ገንዘብ እየሰከረና ከሌሎች ሴቶች ጋር እየባለገ ወደ ቤት እንደሚመጣ ትረዳለች። ይሄኔ ነበር የ34 ዓመቷ ናኖዚ ለባለቤቷ ትምህርት ለመስጠት የፈለገችውና የ”ቾምስ” ጥያቄ ሲያቀርብ “የክፈለኝ” ጥያቄ ማቅረብ የጀመረችው።

መጀመሪያ ላይ አጨቃጫቂ የነበረው ይህ የናኖዚ ስትራቴጂ በመብት ተሟጋቾችና በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ድጋፍን አግኝቷል። ምንም እንኳን በሃይማኖት መሪዎችና በመንግስት ባለስልጣናት ድጋፍ ያላገኘና ዑጋንዳውያንን ለሁለት የከፈለ ሃሳብ ቢሆንም ቅሉ።

ቀምቃሚ ባሎች [የሰይጣን ጆሮ አይስማውና] ይሄንን “የአልጋ ግብር” ጉዳይ ሚስቶቻቸው ሰምተው ግብሩን ቢጥሉባቸው ምን ይውጣቸው ይሆን?

ተጨማሪ መረጃ ይሄንን ሊንክ በመጫን ያንብቡ
https://www.thesun.co.uk/news/worldnews/6693467/african-wives-make-husbands-pay-sex-tax/&ved=2ahUKEwiq-JDRm7veAhVObBoKHeYkCJsQFjAEegQIAxAB&usg=AOvVaw1vsmMGuZX-TL2QAh0LayFF