በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀሰዉ ግጭት በተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳትና ሞት መድረሱ ይታወሳል፡፡
በዩኒቨርስቲዉ የመማር ማስተማር ሂደትም ተቋርጦ ቆይቷል፡፡
አሁን ግጭቱን ተከትሎ ግቢዉን ለቀዉ የወጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዉ አንፃራዊ ሰላም በመኖሩ በመመለስ ላይ መሆናውን በቦታው የሚገኘው የአቢሲ ሪፖርተር ያለለት ወንድዬ ዘግቧል ፡፡
በዩኒቨርስቲዉ አሁን ላይ የተማሪዎችን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች መከናወናቸውን የዩኒቨርስቲዉ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ረሺድ መሃመድ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርስቲዉ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል በዝግጅት ላይ እንደሚገኝና ግቢዉን ለቀዉ የወጡ ተማሪዎች ተጠቃው እንዲመለሱ አቶ ረሺድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በግጭቱ ወቅት የትምህርት ማስረጃቸዉ የወደመባቸው ተማሪዎች ሙሉ ማስረጃቸውን ሳይጉላሉ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ ተመቻችቷል ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ያሉበትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ፈትሾ የማስተካካያ እርምጃ እንደሚያደርግ አቶ ረሺድ ገልጸዋል፡፡
ኢቢሲ እንደዘገበው በዩኒቨርስቲዉ ተከስቶ ከነበረዉ ሁከትና ብጥብጥ ጀርባ ያሉ አካላት ላይ አሰፈላጊዉ ማጣራት እየተካሄደ ሲሆን በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል ።
Epa
Comments are closed.