Take a fresh look at your lifestyle.

” ሕዝባችንን መጠየቅ የምፈልገው ሰፊ ትእግስትና መረጋጋት እንዲኖረው ነው ” ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ

514

ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት

 ሕገ መንግስቱን ማሻሻል የሚቻልበት አሰራር በራሱ በሕገ መንግስቱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ የማይሻሻልበት ምክንያት የለም፡፡ ምክንያቱም ሕገመንግስት ዘላለማዊና ቋሚ አይደለም፡፡

 ሕዝባችንን መጠየቅ የምፈልገው ሰፊ ትእግስትና መረጋጋት እንዲኖረው ነው፡ ፡የፍትሕ ጉዳይ በአንድ ጀምበር መልስ የሚገኝለት አይደለም፡፡ሪፎርሙ ተጀምሯል፡፡መንግስት መልካም ሀሳብ አለው፡፡ሕዝቡ በቅን ልቦና እንዲረዳው ትእግስት እንዲያደርግ ያስፈልጋል፡፡

 ትክክለኛና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ፍትሕ እንደሚሰጥ ሌላው ወገን በፍርድ ቤት ላይ ሙሉ እምነት እንዲኖረው መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡

 የሚዲያ ሰዎች እንዲከታተሉት፣እንዲያውቁት፣ሕዝቡንም እንዲያሳውቁት የምፈልገው የሐሰተኛ ማስረጃ ሰነድን ጉዳይ ነው፡፡ በሐሰተኛ ሰነድ ሰው ንብረቱን እያጣ ነው ፡፡

 የዳኝት ነጻነትን ለማረጋገጥ ዳኞች ራሳቸው ለራሳቸው መቆም አለባቸው፡፡ ሲታዘዙ አቤት ከማለት ወጥተው የዳኝነት ነጻነትን ማስከበር አለባቸው፡፡

 

Comments are closed.