Take a fresh look at your lifestyle.

“ዜጎችን ራቁታቸውን በመጣል በጉንዳን እንዲበሉ አድርገዋል ” ( የፖሊስ የምርመራ መዝገብ )

384

 

በቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ሀላፊ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል በነበሩት የአቶ ያሬድ ዘሪሁንን ጉዳይ ለማየት የተሰየመው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ችሎት ጉዳዩን ለማየት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ
በትናንትው እለት ወደ ኬንያ ለመሸሽ ሲሞክሩ በፌደራል ፖሊስና በኦሮሚያ ፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር የዋሉት
ተቶ ያሬድ ዘሪሁን ዛሬ ለሁለተኛ ቀን ፍርድ ቤት ቀርበዋል ።
በዚሁ ወቅት ፖሊስ በተከሳሹ ላይ ባቀረበው የክስ ማመልከቻ አቶ ያሬድ ዘሪሁን አሁን በቁጥጥር ስር ካልዋለው የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገለግሎት የቀድሞ ኃላፊ ጋር በመተባበርና ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመቀበል በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል ፡፡ በዚሁም መሰረት
በዜጎች ላይ አፈና በማካሄድ ፡ ብልታቸው ላይ ውሃ በማንጠልጠል ራቁታቸውን ቆሻሻ ውስጥ በመጣል ጉንዳን እንዲበሉ አድርገዋል በተፈፀመባቸው ድብደባም ለብዙዎች ህይወት እንዲያልፍ አድርገዋል

ሆን ብለው ያዘጋጇቸውን ሰወች ወደ ኤርትራ ሰርገው ህገወጥ መሳሪያ እንዲያስገቡ በማቀነባበር ህዝብ እንዲሸበር ይህም በተጠርጣሪዎች ላይ እንዲሳበብ በማድረግ ወንጀል እንደሚፈልጋቸው ለፍርድ ቤቱ ገልፆ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድቤቱን ጠይቋል ፡፡
ሆኖም ተከሳሹ ከህግ አማካሪያቸው ጋር መገናኘት እንደሚፈልጉ በመግለፅ ለሚቀጥለው ማክሰኞ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲሉ ፍርድ ቤቱን በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ለመጭው ማክሰኞ ቀጠሮ ሰጧል ።

Comments are closed.