Take a fresh look at your lifestyle.

የጦር መሳሪያ በመነካካት ላይ የነበሩ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ ፡፡

205

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ አደባባይ ጽዮን ቀበሌ ዕውቀትና ልምድ ሳይኖራቸው ‹ኤፍ ዋን›› የተሰኘ ቦንብ የነካኩ አራት ሰዎች መሞታቸው እና 2 ሰዎች መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡

የደባርቅ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ጥቅምት 24 ቀን 2011ዓ.ም በአደባባይ ጽዮን ቀበሌ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ በሕገ-ወጥ የተቀመጠን ኤፍ ዋን ቦንብ በመነካካታቸው ፈንድቶ ነው ጉዳቱ የደረሰው፡፡

አደጋው በደረሰበት ቤት በድግስ ምክንያት የተሰባሰቡ ሰዎች ቦንቡ መሥራት አለመሥራቱን ለማወቅ በመነካካታቸው አራቱ ሰዎች ወዲያውኑ ሞተዋል፤ ሁለቱ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል፡፡

ምንጭ፡-AMMA  የደባርቅ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት

Comments are closed.