እንደሚታወቀው ሁሉ በዓለም ላይ የተለያየ ቅርፅና ይዘት ያላቸው የፌዴራሊዝም ዓይነቶች እንዳሉ ግልጽ ሲሆን፣ በሁለቱ ዋና ዋና የፌዴራሊዝም ዓይነቶች ላይ በተለያየ ጊዜና በተለያዩ ምሁራን ሰፊ ጥናት ተካሂዶባቸዋል፡፡ እነዚህ የፌዴራሊዝም ዓይነቶችም፣
- በዘር ግንድና በቋንቋ ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝም (Language and Ethnic Based Federalism) ነው፡፡
ይህ የፌዴራሊዝም ዓይነት በብዙ አገሮች ተግባራዊ ሆኖ ከጥቅሙ ይልቅ ችግሩ የሰፋ በመሆኑ የተነሳ አገሮቹ ወደማይወጡት ማጥ ውስጥ ገብተው የሚገኙ ሲሆን፣ በፌዴራል መንግሥቱ ሥር የሚገኙ አካላት አንድም ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር ወይም እርስ በርሳቸው በግጭት ውስጥ ስለሚገቡ ሰብዓዊና ቁሳዊ ሀብታቸው በግጭቱ ይወድማል፡፡ በዚህ የተነሳም ዕድገታቸው ቀጭጮ ዜጎቻቸው በድህነት አዘቅት ውስጥ የሚማቅቁ ናቸው፡፡
ይህን ዓይነት የፌዴራሊዝም ሥርዓት ከሚከተሉ አገሮች መካከልም፣ የቀደሞዋ ሶቪየት ኅብረት፣ ዩጎዝላቪያ፣ ቤልጂየምና ኢትዮጵያ ይገኙበታል፡፡
በዚህ ዓይነት የፌዴራሊዝም ሥርዓት ውስጥ የሚገኙ አገሮች የአብዮታዊ ዲሞክራሲን መርህ ስለሚከተሉ፣ ከግለሰብ መብት መከበር ይልቅ ለቡድን መብት መከበር ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ የአገራችንን ሁኔታ እንደ ምሳሌ ብንወስድ ኢሕአዴግ መርህ መሠረት የአማራውን መብት የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ብአዴን)፣ የኦሮሞን የሰብዓዊ መብት ኦሕዴድ፣ የትግራይ ተወላጆችን መብት ሕወሓት፣ ወዘተ ያስከብራል በሚል ያምናል፡፡
- እንጂ እስካሁን ድረስ ባለን ተሞክሮ መሠረት እነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች የየራሳቸውን የፖለቲካ አባላት፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መብትና ጥቅም እንጂ የሚወክሉትን የአጠቃላይ ሕዝብ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ በቂ ጥረት ሲያደርጉ አልታዩም፡፡ በእንደነዚህ ዓይነቶቹ ችግሮች ምክንያት በእነዚህ አገሮች የሚታየው ያልተረጋጋ ፖለቲካ፣ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ዕድገትና ዝቅተኛ የአንድነት ስሜት፣ በአጠቃላይ የመበታተን ዕጣ ፋንታ (Unstable Politics, Low Economic Development, Less Integrity and in General Fragmentation) ይታይባቸዋል፡፡
ሁለተኛው የፌዴራሊዝም ዓይነት ደግሞ በጂኦግራፊ፣ በኢኮኖሚና፣ በማኅበራዊ ትስስር ላይ የተመሠረተ ነው “That Based on Geography, Economic and Socilites”፡፡ ይህን ዓይነት የፌዴራሊዝም ሥርዓት ከሚከተሉ አገሮች መካከልም አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ብራዚል፣ ታላቋ ብሪታኒያ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካና ናይጄሪያ ይገኙበታል፡፡ እነዚህ አገሮች የሊበራል ዴሞክራሲን መርህ ስለሚከተሉ በመጀመርያው ረድፍ ከተጠቀሱት በተቃራኒ ከቡድን መብት ይልቅ ለግል መብትና ጥቅም ቅድሚያ ስለሚሰጡ ሰላም፣ የተረጋጋ ፖለቲካና የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያጣጥሙ ከመሆናቸው በተጨማሪ አንድና ጠንካራ አገር ያላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ ብራዚል ይህን ዓይነት የፖለቲካ መስመር በመከተሏ ምክንያት ዛሬ ከድህነት ወጥታ ለዓለም አገሮች የምግብና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማቅረብና ፈጣን የሆነ ኢኮኖሚ በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡
- ላይ ጥልቅ ጥናት የተደረገበትና ሕዝባችን የተሳተፈበት ውሳኔ የሚያስፈልገው የትኛው ፌዴራሊዝም ነው ለኢትዮጵያ የሚጠቅመው? የሚለው ነው፡፡ በአኔ አስተያየት የዜጎችባህል፣ ቋንቋ፣ ማንነትና የሰብዓዊ መብት ተከብሮ የማዕከላዊ መንግሥትም የአካባቢ መስተዳድሮችን ሥልጣን ሳይሸራርፍ እንዲያከብር ሆኖ፣ እንዲሁም የሊበራል ዴሞክራሲ መሠረቱ የእያንዳንዱ ዜጋ መብትና ድምፅ ተከብሮ የመንግሥት ሥልጣን ብቸኛው ባለቤት ሕዝብ መሆኑን መቀበል ነው፡፡ በዚህም መሠረት የዜጎች ማለትም የግለሰቦች የመጻፍ፣ የመናገር፣ የመደራጀት፣ መሪውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመምረጥና የመመረጥ፣ የእምነት ነፃነት፣ ንብረት የማፍራት ነፃነትና የሌሎችንም የሲቪክና የፖለቲካ ነፃነት ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ ዋስትና መስጠት ነው፡፡
- የምልበት ምክንያትም ዛሬ የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም የዜጎችን ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመሥራት መብትን ገድቧል፡፡ በፌዴራል መንግሥቱና በአንዳንድ ክልሎች መካከል እንዲሁም በየክልሎች መካከል የእርስ በርስ ግጭትን በመፍጠር የዜጎች ሕይወትና የአገሪቱ ንብረት እንዲወድም አድርጓል፡፡ እንዲሁም አገሪቱ የተረጋጋች እንዳትሆን ከፍተኛ ምክንያት ሆኖባታል፡፡ ለምሳሌ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሊያ፣ በኮንሶና በአሪ፣ በጉጂና በቦረና እንዲሁም በአፋርና በአማራ . . . መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭትን በመፍጠር ዜጎች በማይጠቅም ጉዳይ እንዲጋደሉና ብዙ ንብረትም እንዲወድም አድርጓል፡፡ እያደረገም ይገኛል፡፡
- በኩል ዜጎች በአካባቢያቸው መዳኘትና ፍትሕ ማግኘት ሲገባቸው የዘር ግንዳቸውን በመቁጠር ብዙ ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ ለፍትሕ ፍለጋ ሲንገላቱና ሲቸገሩ ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ የምንጃር ወረዳ ሕዝብ በ20 ኪሎ ሜትር ከሚገኘው ከአዳማ ፍትሕ ማግኘት ሲኖርበት፣ የዘር ግንዱን ፈልጎ 800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ባህር ዳር ድረስ እንዲሄድ ያስገደደው ይህ ዓይነቱ ፌዴራሊዝም መሆኑ ነው፡፡
- የኢትዮጵያ አንድነትና መረጋጋት፣ የሕዝብም ዕድገትና ብልፅግና ይሰምር ዘንድ ከላይ በተጠቀሱ የሊበራል ዴሞክራሲ መርሆዎች ላይ በመመርኮዝ በዘር ግንድና በቋንቋ ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝም ሳይሆን በጂኦግራፊ፣ በኢኮኖሚና በባህል ትስስር ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያ መተኪያ የሌለውና ጠቃሚ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝባንን ይባርክ፡፡
ፌዴራሊዝም
- በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት ፌዴራሊዝም አሉ፡፡
- አንደኛው በጂኦግራፊ፣ በኢኮኖሚና፣ በማኅበራዊ ትስስር ላይ የተመሠረተ፣
- በዘርና በቋንቋ ላይ የተመሠረተ “That Ethnic and language based”:
- ላይ የትኛው ፌዴራሊዝም ነው ለኢትዮጵያ የሚጠቅመው? ይህ ነው ጥልቅ ጥናት የተደረገበት ውሳኔ የሚያስፈልገው፡፡
- አስተያየት የዜጎች ባህል፣ ቋንቋ፣ ማንነትና የሰብዓዊ መብት ተከብሮ እንዲሁም የማዕከላዊ መንግሥት የአካባቢ መስተዳድሮችን ሥልጣን ሳይሸራርፍ እንዲያከብር ሆኖ፣ በአንደኛው ላይ እንደተጠቀሰው በኢኮኖሚ፣ በጂኦግራፊና በባህል ትስስር ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያ ጠቃሚ ነው ብዬ አምናለሁ
- የምልበት ምክንያት ዛሬ በዘር ግንድና በቋንቋ ላይ የተመሠረተ የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም የዜጎችን ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመሥራት መብት ገድቧል፡፡ ክልሎች በግጭት ውስጥ እንዲገቡ በማድረጉ የተነሳ አገሪቱ የተረጋጋች እንዳትሆን አድርጓታል፡፡
ለምሳሌ በኦሮሚያና በሶሚሊያ፣ በኮንሶና በአሪ፣ በጉጂና በቦረና እንዲሁም በአፋርና በአማራ መካከል ከፍተኛ ግጭት በመፍጠር ዜጎች በማይጠቅም ነገር እንዲጋደሉና ብዙ ንብረትም እንዲወድም አድርጓል፡፡
- ዴሞክራሲ መሠረቱ የእያንዳንዱ ዜጋ መብትና ድምፅ ተከብሮ የመንግሥት ሥልጣን ብቸኛው ባለቤት ሕዝብ መሆኑን መቀበል ነው፡፡ በዚህም መሠረት የዜጎች ማለትም የግለሰቦች የመጻፍ፣ የመናገር፣ የመደራጀት፣ መሪውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመምረጥና የመመረጥ፣ የእምነት ነፃነት፣ በየትኛውም ክልል ንብረት የማፍራት ነፃነትና የሌሎችንም የሲቪክና የፖለቲካ ነፃነት ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ ዋስትና መስጠት ።
- ( ቢኒያም ገ/የሱስ Ethiopian Reporter )
Comments are closed.