Take a fresh look at your lifestyle.

የለገሃር የተቀናጀ የመኖርያ መንደር እውነታዎችና አስገራሚ ዲዛይኖቹ

441

 

በዛሬው እለት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ(ዶ/ር) በይፍ ያስጀመሩት የለገሃር የተቀናጀ የመኖርያ መንደር እውነታዎች፡፡
******************************

– ከ25 ሺህ በላይ የስራ እድል ይፈጥራል፡፡
-ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የ50 ቢልየን ብር ይፈጃል፡፡
– ቅንጡ ባለ-4 እና ባለ-5 ኮከብ አለም አቀፍ ሆቴሎች
– የተለያየ መጠን ያላቸው የንግድ ቤቶች
– ለሃገራችን በአይነታቸው ለየት ያሉ ሲኒማ ቤቶች
– ለልጆች የመጫወቻ ስፍራዎች
– ለአዋቂዎች የአረንጓዴ እና የመዝናኛ ስፍራ
– የስፖርት ማዘውተርያ ጂምናዝየሞች / ሜዳዎች
– የአገልግሎት መስጫ ተቋማት
– ለግልም ሆነ ለመንግስት ተቋማት የሚሆኑ ቢሮዎች
– ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራን
ያካተተ የግንባታ ፕሮጀክት ሲሆን የግንባታው የመጀመሪያ ምዕራፍ የሚሆነውም ከቦታው ለሚነሱ 1600 አባ ወራዎች የመኖርያ ግንባታ ይሆናል፡፡
– ከ4000 ሺህ በላይ የመኖርያ አፖርትመንት ተጨማሪ ግንባታ ይኖረዋል፡፡
በ36 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው ይሄው ዘመናዊ የመኖርያ እና ሁለገብ መንደር ከ4000 በላይ ነዋሪ የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል፡፡
ግንባታው በሚከናወንበት አካባቢ የሚኖሩ 10 ሄክታር መሬት ላይ ያረፉ ከ1600 በላይ ነዋሪዎች ከመኖርያ ቀዬአቸው ሳይርቁ አዲስ በሚገነባው ዘመናዊ የመኖርያ ህንፃ ላይ የመኖርያ ቤት በቅድሚያ ከማግኘታቸው በተጨማሪ የለገሃር ፕሮጀክት ውስጥ በሚኖሩ የስራ እድሎች ተጠቃሚም ይሆናሉ፡፡ በተጨማሪም የለገሃር ፕሮጀክት ከአካባቢው ህብረተሰብ አልፎም ለከተማዋ ነዋሪ ተጨማሪ መስህብ ይሆናል፡፡

ቪዲዮውን ይመልከቱ

Comments are closed.