Take a fresh look at your lifestyle.

‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም። ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ለፍርድ ቤቱ ከተናገሩት። 

433

ዛሬ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
በትናንትናው የፍርድ ቤት ውሎ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ”ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ” በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
ዛሬ ፖሊስ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ጠበቃ የመቅጠር አቅም እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ አለኝ ብሏል። ፖሊስ እንደሚለው ሜጄር ጄኔራል ክንፈ በጸረ-ሙስና ኮሚሽን ያስመዘገቡት የሃብት መጠን እና በአንድ ባንክ ውስጥ ያላቸው ተቀማጭ ሂሳብ ጠበቃ የመቅጠር አቅም እንዳላቸው ያመላክታል ብሏል።
ፖሊስ ጨምሮም ከ15 ቀን በፊት አንድ መቶ ሺህ ብር ከባንክ ሂሳባቸው ወጪ መደረጉን እና በስማቸው 80 ሺህ ብር የሚያወጣ መኪና እና ቤት ተመዝግቦ እንደሚገኝ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
ሜጀር ጄኔራል ክንፈ በበኩላቸው ፖሊስ የጠቀሰው ንብረት እና ገንዘብ ‘‘የእኔ አይደለም’’ ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ ‘‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም። ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’ በማለት ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ ሜጄር ጄኔራል የራሳቸውን ጠበቃ እንዲያቆሙ ውሳኔ አስተላልፎ ለህዳር 10 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
ከሜጄር ጄኔራሉ ጋር ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘው፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዤጠኛ ፍጹም የሺጥላ፣ ሳጅን ኪዳኔ አሰፋ፣ ትዕግስት ታደሰ እና አቶ ቸርነት ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

BBC

Comments are closed.