Take a fresh look at your lifestyle.

የሜቴክና የኢንሳ ሃላፊዎችን ማን ያዛቸው ? በስፍራው ከነበረ የአይን እማኝ የደረሰን መረጃ

4,012

መንግስት በሃላፊነት የሚጠየቁ ሰወች ከሃገር ሊወጡ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸውን ሰወች ስም ዝርዝር በድንበር አካባቢ ላሉ የጥበቃና የደህንነት ሃይል በላከው መረጃ መሰረት በትናንትናው እለት ምሽት አምስት ሰአት ላይ በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ልዩ ስሙ በአኸር የሚባል ቦታ ላይ ያሉ የትግራይ ሚሊሻዎች አንድ ለየት ያለ መኪና ያዩና ያስቆሙታል ። በመኪናው ውስጥ ያሉት የኢንሳው ሃላፊ ብ/ጄኔራል ተ/ብርሃንና የሜቴኩ ብ/ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ነበሩ ። ይህን የተረዱት የአካባቢው ሚሊሻዎች በአካባቢው ላሉ የትግራይ ሃይል ልዩ ሃይሎች አሳልፈው ይሰጧቸዋል ። ይህ መረጃ የደረሰው መከላከያ ተጠርጣሪዎቹን ለመውሰድ ይጠይቃል ። በዚህ ጊዜ የትግራይ ልዩ ሃይሎች ሰወቹን ለክልሉ ፖሊስ እንጂ ለሌላ እንደማይሰጡ ይናገራሉ ይህ ውዝግብ ይካረርና የትግራይ ክልል ሃላፊዎች ወደ ስፍራው ተጉዘው ይህ ትእዛዝ የመጣው ከፌዴራል መንግስት በመሆኑ ሰወቹን መስጠት እንዳለባቸው ከስምምነት በመድረሳቸው ሁለቱን ጄኔራሎች አሳልፈው ሊሰጧቸው ችለዋል ።እንደ konjoEthiopia.com መረጃ መሰረትም ዛሬ ከሰአት በኋላ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ( wasihune tesfaye  )

Comments are closed.