Take a fresh look at your lifestyle.

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በተመለከተ የ konjoEthiopia.comዝርዝር ሪፖርታዥ

311

 


የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ዛሬ በሰጡት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት ተጠርጣሪዎች ከሰብአዊ መብት አያያዝና ከሙስና ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሰው በዚህም መሰረት እስካሁን 63 ግለሰቦች መያዛቸውንና ሌሎች በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር ተደብቀው የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የመዋል ጥረቱ እንደቀጠለ በዚህም መሰረት በውጭ ተደብቀው ያሉትን ወደ ሃገር በማስመጣቱ በኩል ሃገራት በጎ ትብብር እያሳዩ እንደሚገኙ ገልፀዋል ።
አቃቤ ህጉ አያይዘውም በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉትን ሰዎች ይፈፅሟቸው ከነበሩት ወንጀሎች መሃከል
ተጠርጣሪዎች በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው በስውር እስር ቤቶች ውስጥ እንዲቆዩ ሲደረግ ነበር፡፡ በተጠርጣሪዎች ላይ ይፈፀሙ ከነበሩት ኢሰብአዊ ድርጊቶች መሃልም ኤሌክትሪክ ሾክ፣ የብልትን ቆዳ በፒንሳ መሳብ፣ ዛፍ ላይ ሰቅሎ መግረፍ፣ ጫካ ውስጥ ራቁታቸውን ማሳደር፣ በአፍንጫ ስክሪፕቶ አስገብቶ ማሰቃየት፣ በብልታቸው ላይ በሃይላንድ ውሃ ሞልቶ ማንጠልጠል በሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር በወንዶች ላይ የግብረ ሰዶም ድርጊቶች ጥፍር መንቀል፡ ከዱር አውሬ ጋር ማሳደርና ሌሎች የመብት ጥሰቶች ይፈፀሙባቸው እንደነበርና በዚህ ሁኔታም የተገደሉና የተሰወሩ ሰዎችም አሉ ፡፡ ብለዋል ።
በአዲስ አበባ 7 የሚሆኑ የስውር እስር ቤቶች ድብቅ ማቆያዎች ተጠርጣሪዎች ያልሠሩትን ወልጀል ፈጽመናል ብለው እንዲያምኑ ለማድረግ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ የገለጹት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ፣ ተጠርጣሪዎች አይናቸው ተሸፍኖ በአምቡላንስ ታፍነው እንደሚወሰዱ ተናግረዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲ አባላት በግድ ከአባልነታቸው እንዲወጡ ይደረግ እንደነበርና እምቢ ካሉም ድብደባ ይደረግባቸው እንደ ነበር ገልፀዋል ።
በቁጥጥር ውስጥ ከዋሉት በተጨማሪም ሌሎች የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉ ገልፀዋል ። ከሙስና ጋር በተያያዘ ከደረሰው ሃገራዊ ጥፋት ጋር መሰረት የተከናወኑ ጉዳዮች ምን ይመስላሉ የሚሉትን ጉዳዮች ለማጣራት ጥረት ተደርጓል በዚህም መሰረት ሜቴክ ከ2004 አ/ም እስከ 2010 37 ቢሊየን ብር የውጭ ሃገር ግዥ ያለጨረታ ግዥ ተከናውኗል ብለዋል ።
በኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራሮች ጋር የጥቅምና የዝምድና ትስስር ባላቸው ግለሰቦች አማካኝነትም ከአንድ የውጭ ሃገር ግዥ እስከ 400ፐርሰንት በላይ ኮሚሽን በመያዝ ህገወጥ ግዥዎች ተከናውነዋል ።
ከአንድ ተቋም እስከ አርባና ሃምሳ ጊዜ ድግግሞሽ ያለው ከቻይናና ከሲንጋፖር ካምፓኒዎች ተከናውነዋል ። ከነዚህም መሃከል በዚሁ መልኩ ተገዝተው ወደ ሃገር ውስጥ መግባት ከነበረባቸው አምስት ክሬኖች መሃከል አራቱ ወደ ድርጅቱ ሲገቡ አንደኛው ወደ ግለሰብ ተላልፎ እየተሰራበት እንደሆነ ተደርሶበታል ።
በሃገር ውስጥ የተከናወኑ ህገወጥ ግዥዎችም ከኮርፖሬሽኑ አመራር ጋር ዝምድና ያላቸውን ሰወች ለመጥቀም ሲባል ከአንድ ድርጅት 21 ጊዜ ከአንድ ድርጅት 18 እና 17 ጊዜ ተደጋጋሚ ግዥ የተፈፀመ ሲሆን በዚህ መሰረት በተከናወነ ግዥ ከአንድ ድርጅት ብቻ የ 2መቶ አምስት ቢሊየን ግዥ ያለጨረታ ተከናውኗል ።
ከተቋሙ ተልእኮ ውጭ የተፈፀሙ ግዥዎችን በተመለከተ ሲያስረዱ ያለምንም አዋጭነት ና ጥናት የመርከብ ግዥ ተከናውኗል ከነዚህም የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ መሃከል አባይና ጣና የተሰኙትን የባህር ትራንዚት መርከቦች መርከቦቹን ቆራርጦ ብረቱን ለመጠቀም በሚል ሜቴክ ለባህርና ትራንዚት ቦርድ ባመለከተው መሰረትመርከቦቹን ሊገዛ ከተዋዋለው የውጭ ድርጅት ተነጥቆ ለሜቴክ በ 3.26 ሚሊየን ብር ገዝቶ በመ
ካሳደሰ በኋላ ወደ ንግድ ስራ አስገብቷል ። መርከቦቹ ለረጅም ጊዜ በጅቡቲ ወደብ ቆመው ለተጨማሪ ጥገና አምስት መቶ ሚሊየን በላይ ወጪ ተደርጎ ከሜቴክ አመራሮች ጋር ዝምድና ባላቸው ሰወች ድለላነት መርከቡ ተጠግኖ እንደወጣ በማስመሰል ከኢራን ወደ ሞቃዲሾ ስራ ሰርተው ያገኙት 500 ሚሊየን ዶላር ወደ ግለሰቦች አካውንት ገብቷል ። በ 2።6 ሚሊየን ብር ተሽጣለች
የአውሮፕላን ግዥን በተመለከተ 11 ሚሊየን ብር በላይ ግዥ ተፈፅሞ ወደ ንግድ ገብቷል ከሃምሳ አመት በላይ ያገለገሉ አውሮፕላኖች ሲሆኑ አንደኛው አውሮፕላን የት እንዳለና ምን እየሰራ እንደሆነ አልታወቀም ተብሏል። የሆቴል ግዥ በተመለከተ የባንክ እዳ ያላቸውን ሆቴሎች ግዥ ተፈፅሟል ።

Comments are closed.