Take a fresh look at your lifestyle.

ከ40 በላይ የሜቴክና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ ።

606

ከ40 በላይ የሚሆኑ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ፡፡

የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት ትናንትና ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ለስብሰባ ከተጠሩበት ስፍራ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ከፍተኛ አመራሩና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር የዋሉት ገርጂ አካባቢ በሚገኘውና ቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ተብሎ ይጠራ በነበረውና አሁን የኮርፖሬሽኑ ንብረት በሆነው አሞራው ሕንፃ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አመራሮቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉበት ምክንያት ባይነለጽም፣ የፌዴራል ፖሊስ ጌዜያዊ እስር ቤት በሆነው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማቆያ ቤት መታሰራቸውን ምንጮቹ አክለዋል፡፡

( ታምሩ ፅጌ ሪፖርተር  )

Comments are closed.