Take a fresh look at your lifestyle.

ቴዲ አፍሮ የኢትዮ-ኤርትራ የፍቅር ሩጫን በክብር እንግድነት ያስጀምራል።

655

ቴዲ አፍሮ የኢትዮ-ኤርትራ የፍቅር ሩጫን በክብር እንግድነት ያስጀምራል።

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የኢትዮ-ኤርትራ የፍቅር ሩጫ ላይ በክብር እንግድነት ይገኛል።

የውድድሩ ዋና አስተባባሪ አቶ ሰለሞን ታፈረ እንደገለጹት 20 ሺህ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንየበሚሳተፉበትን የፍቅር ሩጫ ቴዲ አፍሮ ያስጀምረዋል።

የሩጫው ዓላማ የኢትዮጵያንና የኤርትራን ወንድማማችነት ማጠናከር ሲሆን ተሳታፊዎች ይህን የሚያሳዩ መልዕክቶችን እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።
ከከተማዋ ፖሊስ ጋር በመተባበር በፀጥታ በኩል ችግሮች እንዳይኖሩ በቂ ዝግጅት እንደተደረገም ተገልጿል።

ኢዜአ እንደዘገበው ሩጫው መነሻውን መስቀል አደባባይ ያደርግና በመሿለኪያ-አጎና ሲኒማ -ጎተራ ማሳለጫ-ወሎ ሰፈር-አሎምፒያ-መስቀል አዳባባይ የሚጠናቀቅና የ10 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ነው።
፩ ፍቅር
ፍቅር_ያሸንፋል

Comments are closed.