Take a fresh look at your lifestyle.

የEBC የመጨረሻው ነውረኛ ዘገባ ፡ 48 አመታትን በትዳር ባሳለፉ ቤተሰቦች ዙሪያ የተሰራ ፕሮግራም።

( by Wasihune Tesfaye )

853

ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የመጣች አሜሪካዊት ቱሪስት ብልቱን በቅጠል ሸፍኖ በከብት ጀርባ ሲዘል ያየችውን የሱርማ ተወላጅ አፍቅራ በትዳር አብረው በሚኖሩበት ወቅት ፡  ጥቁርና ነጭ ተጋብተው የልጅ ልጅ በሚያዩበት ዘመን ። ሚሊዮኖች የሚያዩት ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያችን  ለሺህ ዘመናት ዘርና ብሄር ሳይቆጥሩ አብረው ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትርጉም አልባ የሆነ  ዘገባ ሰርቶ አሳይቶናል ።

ከሌላ ብሄር ተገኝቶ የልጅ ልጅ ልጅ ማየት  ፡ ከሁለት የተለያዩ ብሄሮች ተፋቅሮ ትዳር መመስረት ለኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር የሆነ ይመስል ። ” የተለያዩ ብሄር ተወላጅ ሆነው 48 አመት በትዳር የቆዩ ቤተሰቦችን ፈልጎ ልክ እንደ አዲስ ነገር በዘገባ መልክ ሰርቶ ማቅረብ ምን የሚሉት እብደት ነው  ?  ለኛ ለኢትዮጵያውያን አዲስ የሆነው ይህ መች ሆነ   ? እንደ ተአምር ተቆጥሮ ዘገባ ሊሰራበት የሚገባው ከቅርብ ጊዜ በኋላ መታየት የጀመረው ብሄር ተኮር ጥላቻ እንጂ አብሮ መኖሩማ ለኛ ምን ይገርማል   ?

EBC ይህን ዘገባ በማሳየት በነሱ አተያይ  የላላ የመሰለውን የብሄር ብሄረሰብ ጥምረት ለማጥበቅ አስቦም ከሆነ መስራት የሚገባው እንደ ጉድ እና  ተአምር ተቆጥሮ ሊዘገብለት የሚገባው በቅርብ በጥቂት ግለሰቦች ላይ እየተንፀባረቀ ባለው የአግላይነትና የዘረኝነት  ስሜት ላይ እንጂ አብሮ መኖሩማ የመተንፈስ ያህል ስንወለድ የታደልነው ነው ።

ለማንኛውም Ebc በዚህ ረብ የለሽ ዘገባው ሊያፍር ይገባዋል ። ለኛ ለኢትዮጵያውያን አብሮ መኖር ተአምር አይደለም ።

 

 

 

Comments are closed.