አቶ እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ዘይኑ ጀማል የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አቶ እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል ።
አቶ እንደሻው ከ1983 ጀምሮ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከመምህርነት እስከ ክፍለ ጦር አመራርነት በትምህርቱ ዘርፍእስከ 1992 ድረስ አገልግለዋል። ከመከላከያ በኋላ በአዲስ አበባ የተለያዪ የሃላፊነት ቦታዎች ከወረዳ ጀምሮ እስከ ከተማ ድረስ በተለያዩ የመንግስትን ሃላፊነት ቦታዎች ሲሰሩ የቆዪ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባው የህዝብ ግንኙነት አማካሪ እና የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል ።
አቶ እንደሻው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከሐገር ውጭ ተከታትለው አጠናቀዋል ። ፡፡
Eprdf
Comments are closed.