Take a fresh look at your lifestyle.

በመቐለ_ዩኒቨርስቲ የሰው ህይወት አልፏል ተብሎ በውስን ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተገለፀ ያለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ ።

223

 

በመቐለ_ዩኒቨርስቲ የሰው ህይወት አልፏል ተብሎ በድብቅ /በሽፋን/ በተከፈቱ በውስን ማኅበራዊ ሚዲያዎች (በTwitter እና Facebook) እየተገለፀ ያለው መረጃ የሃሰት እና ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን እናረጋግጣልን ሲል ዩኒቨርስቲው አስታውቋል ።

ባደረግነው ማጣረት የሃሰት መረጃዎቹ እየተሰራጩ ያሉት በድብቅ /በሽፋን/ በተከፈቱ ውስን የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሆን፣ በሃገራችን የተጀመረውን ሰላማዊ የመማር እና ማስተማር ሂደት ለማወክ ሆን ተብሎ የሚሰራጭ የሃሰት መረጃ እንጂ በመቐለ ከተማም ሆነ በዩኒቨርስቲያችን በተማሪ ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጥቃት ወይም አደጋ ያልደረሰ መሆኑን በድጋሜ እናረጋግጣለን ሲል የመቀለ ዩኒቨርሲ በድረ ገፁ ባወጣው መረጃ አስታውቋል ። በመቀጠልም ዩኒቨርስቲው ባጠቃላይ በትግራይ ክልል  በሚገኙ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት  የመማር ማስተማር ሂደቱ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የቀጠለ መሆኑን ገልፆ የሃሰት መረጃዎችን  በጋራ በመከላከል እና ትክክለኛ መረጃዎችን ብቻ በመስጠት እና በማሰራጨት ህብረተሰቡ የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ አሳስቧል ።

 

Comments are closed.