Take a fresh look at your lifestyle.

የEBC የመጨረሻው ነውረኛ ዘገባ ፡ 48 አመታትን በትዳር ባሳለፉ ቤተሰቦች ዙሪያ የተሰራ ፕሮግራም።

ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የመጣች አሜሪካዊት ቱሪስት ብልቱን በቅጠል ሸፍኖ በከብት ጀርባ ሲዘል ያየችውን የሱርማ ተወላጅ አፍቅራ በትዳር አብረው በሚኖሩበት ወቅት ፡  ጥቁርና ነጭ ተጋብተው የልጅ ልጅ በሚያዩበት ዘመን ። ሚሊዮኖች የሚያዩት ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያችን  ለሺህ ዘመናት ዘርና ብሄር ሳይቆጥሩ አብረው ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትርጉም አልባ የሆነ  ዘገባ ሰርቶ አሳይቶናል ።…

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲሱ መዋቅር መሰረት አምስት ቋሚ ተጠሪዎችን ሾመ ።

የቋሚ ተጠሪነት (Permanent Secretary) ሹመት የተሰጣቸው አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ፣ አምባሳደር ዶ/ር ቦጋለ ቶሎሳ፣ አምባሳደር ነገ ፀጋዬ እና አምባሳደር ደዋኖ ከድር ናቸው፡፡ ሹመት የተሰጣቸው አምባሳደር ወይንሸት በሲዊዲን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ…

«የኦሮሞ ህዝብ ባለመታጠቁ ጥቃቶች እየደረሰበት ይገኛል» የኦነግ ቃል አቀባይ

«የኦሮሞ ህዝብ ራሱን ከጥቃቶች ለመከላከል መታጠቅ እንዳለበት» ኦነግ እንደ ድርጅት እንደሚያምንበት የግንባሩ ቃል አቃባይ አቶ ቶሌራ አደባ ዛሬ ለDW ገለጹ። የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው «መንግስት የማህበረሰቡን ሰላም ያስጠብቃል፣ ሁለት የታጠቁ አካላት በአንድ ክልል ብሎም አገር ዉስጥ መንቀሳቀስ የለባቸዉም፤ ኦነግ ትጥቁን መፍታት አለበት» የሚል አቋም ማንጸባረቃቸውን…

ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዲስ አበባ ፡ ጉዳዩ የጥይት ግዥ እንዲፈቀድልን ትብብር ስለመጠየቅ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዲስ አበባ ጉዳዩ የጥይት ግዥ እንዲፈቀድልን ትብብር ስለመጠየቅ በ2011 በጀት አመት ለክልላችን የፀጥታ ተቋማት እና መሰረተ ልማት ጥበቃ አገልግሎት የሚውል የጥይት እጥረት ስላጋጠመን ግዥ መፈፀም አስፈላጊ ሆኗል ። ስለዚህ በብር ( ከነቫቱ ሰባት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ…

ኤርትራዊቷ ድምፃዊት ሄለን መለስ መቐለ ገብታለች ።

አርቲስት ሄለን በቅርቡ በመቐለ ከተማ በሚካሄደው የሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ ለመሳተፍ ዛሬ መቐለ የገባች ሲሆን መቐለ ከተማ ስትደርስም የእራት ግብዣ ተደርጎላታል ። በዚህ የእራት ግብዣ ስነ ስርአት ላይ በርካታ የአርቲስቷ ወዳጆችና አድናቂዎች ተገኝተዋል  ( በሆቴሉ የነበረውን ድባብ ለማየት ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ ። https://youtu.be/rsF_BwcE8DA

አቶ እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

አቶ እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ዘይኑ ጀማል የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አቶ እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል ። አቶ እንደሻው ከ1983 ጀምሮ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከመምህርነት እስከ ክፍለ ጦር አመራርነት…