ጦር አውርድ ( በእውቀቱ ስዩም እንደፃፈው )
ከዘመናት በአንዱ ዘመን የሀበሻ መዲና በነበረችው አክሱም በጎረቤቶቿ በኑብያና የመን ሰላም ነገሰ ይልቁንም በአክሱም ብልጽግና ሰፈነ ሁሉም እንጀራና ወይን ጠገበ ከጥቂት አመታት በኋላ ከተመሰገኑት የአክሱም ሊቃውንት አንዱ ንጉሱ በተገኙበት ጉባኤ ልቦናዬ ያሳየኝን ልናገር አሉ ፡፡ ተፈቀደላቸው
ግርማዊ ጃንሆይ አሉ ባማረ ድምጻቸው ግርማዊ ጃንሆይ አክሱም የምትገኝበት ሁኔታ ለረጋው…