news http://konjoethiopia.com Ethiopian news Mon, 11 Feb 2019 16:32:31 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.1.7 በሶሻል ሚዲያ ውዝግብ ስላስነሳው የቀዳማዊ ሃ/ስላሴን ሃውልት በተመለከተ ቀራፂው መልስ ሰጠ http://konjoethiopia.com/2019/02/11/%e1%89%a0%e1%88%b6%e1%88%bb%e1%88%8d-%e1%88%9a%e1%8b%b2%e1%8b%ab-%e1%8b%8d%e1%8b%9d%e1%8c%8d%e1%89%a5-%e1%88%b5%e1%88%8b%e1%88%b5%e1%8a%90%e1%88%b3%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%89%80%e1%8b%b3%e1%88%9b/ Mon, 11 Feb 2019 16:32:27 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1284 ስለማክበር ሲባል የተፃፈ የፌስ ቡክ ላይ እሰጥ አገባ፡ ባለመፈለግ በሰሞኑ የጃንሆይ ሀውልት ውዝግብ ላይ ዝምታን መርጨ ነበር ። ሆኖም በርካታ፡ብዙሃን መገናኛ አውታሮች እየደወሉ ቃሌን ስላስተጋቡት እንዲሁም አብላጫው ትችት ሰንዛሪ ምንነቱን ባላየውና፡ባላስተዋለው ጉዳይ በቅንነት ድፍረት ብቻ፡ እየተቀባበለ ከግራ፡ቀኝ የሚወራወር መሆኑን ስለተገነዘብኩ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ የሚከተለውን ማስገንዘቢያ ፡ ብፅፍስ ብዬ አሰብኩ ። በመሰረቱ ለአደባባይ ያበቃኸውን ማናቸውንም ቁስ […]]]>

ስለማክበር ሲባል የተፃፈ

የፌስ ቡክ ላይ እሰጥ አገባ፡ ባለመፈለግ በሰሞኑ የጃንሆይ ሀውልት ውዝግብ ላይ ዝምታን መርጨ ነበር ። ሆኖም በርካታ፡ብዙሃን መገናኛ አውታሮች እየደወሉ ቃሌን ስላስተጋቡት እንዲሁም አብላጫው ትችት ሰንዛሪ ምንነቱን ባላየውና፡ባላስተዋለው ጉዳይ በቅንነት ድፍረት ብቻ፡ እየተቀባበለ ከግራ፡ቀኝ የሚወራወር መሆኑን ስለተገነዘብኩ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ የሚከተለውን ማስገንዘቢያ ፡ ብፅፍስ ብዬ አሰብኩ ።
በመሰረቱ ለአደባባይ ያበቃኸውን ማናቸውንም ቁስ ማንም ያገባኛል ባይ ባቅሙና በተረዳበት ደረጃ፡በመሰለው መንገድ የሚሰጠው አስተያየት ሊከበር ይገባል ። በሰሞኑም የሆነው ይኸው ነው። ጃንሆይ ሀውልት አይገባቸውም ከሚለው ፅንፍ ሀውልቱ እርሳቸውን አይመስልም እስከሚለው ድረስ የተባለውን ሰብስበን ለመመዘን ሞከረን ነበር።( ሀውልቱ ስራ፡ ላይ የተሳተፍነው ማለቴ ነው ።) ጃንሆይ ሀውልት አይገባቸውም የሚለው ሩቅ አማራጭ በሀገሩ ላይ የሀሳብ ነፃነት ማመልከቻ ስለሚሆን እንደተከበረ እንደተደመጠ እንለፈው ።ምክንያቱም የአፍሪካ ህብረትና፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከአብላጫው/አሸናፊ ካሉት ሀሳብ ጋር ቆመው መሰራቱን ሰለወሰኑ። የተረፈውንና አስፈላጊ መስሎ የታየንን ሶስት መሰረታዊ ጥያቄ ግን እንደሚከተለው አፍታተነዋል ።

  1. መልኩ ጃንሆይን አይመስልም። ይህ አስተያየት ለደቂቃም ቢሆን ሊያጨቃጭቅ አይገባም ። ሀውልቱ ካልመሰለ እንዲመስል መደረግ አለበት ከመሰለ ደግሞ መስሎ መቀጠል አለበት ። ይህንኑ በማሰብ ምን ጎደለ ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ላይ ሳለን አስተያየቱ ከየትና፡እንዴት እንደተሰነዘረ ሲነገረን ለጥያቄው መልስ በመስጠት መድከሙን አቆምነው። መልኩ አልመሰለም ባዮቹ በጠቅላላ ንጉሱንም ሆነ የተሰራውን ሀውልት ለደቂቃ ባይናቸው አይተው የማያውቁ መሆኑን አረጋገጥን። ታዲያ፡ከየት የመጣ ውርጅብኝ ነው ስንል መነሻው ሁለት አየር ላይ የሚሯሯጡ ፎቶግራፎች መሆናቸው ተነገረን። አንደኛው ፎቶ ስራው ገና፡ የጭቃ ሞዴል ሂደት ላይ ሳለ ከድንገተኛ ጥግ በስርቆሽ የተነሳ የጭቃ ምስል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በምረቃው ቀን ከሃያና ሰላሳ ሜትር ላይ በሞባይል ከርቀት የተነሳ የሰለለ አካል ብቻ የሚያሳይ ሆነው አገኘናቸው። ብቻ ሞተ ሲሉ ተቀበረ ሆነ ነገሩ ። ባጭሩ አሁንም ስለ ሀውልቱ ምንም ዓይነት ትችት መሰንዘር የሚከበር ነገር ሆኖ በተበላሸና ምስሉ በሰለለ ፎቶ ለመዳኘት ከመድፈር በፊት መቸም ጃንሆይ ዛሬ የሉም እንደምንም መጀመሪያ ሀውልቱን ቀርበው ባይናቸው ቢያዩት እላለሁ ። ሀውልትን ባይንና፡በምስል ማየት የሚያጎድለው ብዙ ነገር አለ ።አንዱም ግርማ ሞገስ የሚሉ ሰዎች ከፎቶ ላይ የሚያጡት ነው ። ካልቻሉ ጅምር ስራና፡መናኛ ምስል ላይ ከመመስረት ለምሳሌ ደህና፡ ደህና፡ ፎቶግራፈሮች ያነሱትን መመልከትና፡መተቸት ይመረጣል። ለምሳሌ የቢቢሲውን ድረ ገፅ ለምሳሌ እዚህ ለጥፌዋለሁ።
  2. ለምን በዚህ ልብስ ተቀረፁ ?

ይህ ጥያቄ ከላይኛው የተሻለ ነው ለምን ቢያንስ ታስቦ የተጠየቀ በመሆኑ ። የአፍሪካ፡ህብረትና፡የኢትዮጵያ፡መንግስት ይህንን ሀውልት በአፍሪካ፡ህብረት ግቢ እንዲቆም የተስማሙት ጃንሆይ ከፈፀሙዋቸው አያሌ ገድሎች መካከል አፍሪካን ለማስተባበርና፡አንድ ለማድረግ ለታገሉት ለይቶ ለመዘከር መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ይመስለኛል ።ይህ በተለይ የተሰራበት ዓላማ ጃንሆይን ሌላ ነገር አልሰሩም ለማለት ሳይሆን ለዚህ ለሚቆምበት ቦታ ፡የተመረጠበት የተተኮረበት ገድላቸው ነው ። አፍሪካን ለማስተባበር ወጥተው በወረዱበት ዘመን ሁሉ ጃንሆይ ይለብሱ የነበረው ሁሌም ጥቁር ወይም ግራጫ፡ ሱፍ በክራቫት ብቻ፡ነው። በአፍሪካ ህብረት እንግዳ፡ሲያስተናግዱም ሆነ ሲስተናገዱ አቁዋቁዋማቸውና፡ እጆቻቸው ሁሌም በዚህ መልክ ተመዝቦ የሚታወቅ መሆኑን ቤተሰባቸውን ጨምሮ በሁሉም ዘንድ ምክክር ከተደረገበት በሁዋላ የተወሰነ ነው። እርግጥ፡ ነው ንጉሱ ብዙ የሚያምር ልዩ ልዩ ጌጥ ያለው ልብስና፡አቁዋቁዋም አላቸው ። እሱን ለራሳችን ስሜትና ከተማ ስንቀርፅ የምንመርጠው ይሆናል።መቸም ይሄ ሀውልታቸው የመጨረሻው አይመስለኝም።

  1. ሀውልቱ ለምን የዚህ ዓይነት መልክ ያዘ ?

አደባባይ የሚቀመጥ ፡ሀውልት በዓለም ዙሪያ ከክርስቶስ ልደት በፊት አንስቶ ባብዛኛው በነሀስ መስራት የተለመደና፡ የተመረጠ ነው ። ለምን ቢሉ ቢያንስ ለሶስት ጉዳይ አንድ በጣም ጠንካራ፡የብረት ዘር በመሆኑ ሁለተኛ፡ ተፈላጊውን ቅርፅ ለማስያዝ ለስራ፡አመቺ በመሆኑ ሶስተኛ ከአካባቢው ጋር በጊዜ ውስጥ፡ የሚመሳሰልና፡በመልኩ የማይረብሽ በመሆኑ ። ስለሆነም ባደባባይ ሲቀመጥ በየቀኑ ተላላፊው ተመልካች ሁሌም እንዲወደው ፓቲኔት ይደረጋል። ያደባባይ ሀውልት እንደሜዳሊያና እንደ ዋንጫ ተብለጭልጮ አይቀመጥም። ወይም ማናቸውንም ዓይነት ቀለም አይቀባም።በፍፁም። ፓቲኔት ይደረጋል ማለት በተመረጠ አሲድ በከፍተኛ የወላፈን እሳት (ብዙ ጊዜ ከ800 ዲግሪ ሴልሸስ ባልበለጠ ) እየተለበለበ ነሀሱ ከያዘው አብላጫ የመዳብ ይዘት ጋር ኦክሲጂንን እንዲቀላቅል ይደረጋል ። በዚህም ሰማያዊ አረንግዋዴ መልክ ወይም ያረጀ ሳንቲም እንዲመስል ይሆናል።በዓለም ላይ ይህ የተለመደ ነው። ለምሳሌ ሁሉም የሚያውቀው የኒውዮርኩዋ የሊበርቲ ሀውልት በዕድሜ ብዛት ወደዚህ ሰማያዊ አረንጉዋዴ መጥታለች። አዲስ የነሃስ ሀውልትም በዚህ ዓይነት የአሲድ ፕሮሰስ የአንቲክ ስሜት ተሰጥቶት ራሱ ደግሞ በጊዜ ብዛት አያደር ከአየር ኦክሲጂን እየተሻማ፡እንደሊበርቲ የማማሩን ዕድል ያፋጥንለታል። ውበት ማለት ላደባባይ ሀውልት እንዲህ ለነገም ለዛሬም የሚታሰብ እንጂ እንደ ስጦታ ዕቃ መብለጭለጭ የለበትም ወይም መቀባት የለበትም። የሙያው ዲሲፕሊን ይህንን ያስተምራል ። ይመክራል። ስለሆነም በላዩ ላይ ያለውን ቀለም በዚህ መንገድ ብታስቡት አንወዳለን። ይህንን ባህል የተላመዱት በውጭ የሚኖሩ የንጉሱ ቤተ ዘመዶች በምረቃው ላይ ረክተው በደስታና፡በምስጋና፡ተለያይተናል። የሁሉንም አስተያየት አከብራለሁ ግን ሁሌም ከሃላፊነትና ከጨዋነት ጋር ቢሆን ለሁላችን ይጠቅማል። ያዘመመ ዛፍ ተገኘ ሲባሉ ፈጥነው ለመገርሰስ መጥረቢያ ስለው የሚጠብቁ ብዙ እንዳሉ ሰሞኑን ታዝበናል ።ለነገሩ ባንድ ቀን ያልበቀለ ዛፍ ባንድ ቀንና የሚገረሰስ መስሏቸው ነዋ አመሰግናለሁ።

]]>
አቶ ዛዲግ አብርሃ ለህወሓት ያስገቡት ሙሉ ደብዳቤ http://konjoethiopia.com/2019/02/05/%e1%8a%a0%e1%89%b6-%e1%8b%9b%e1%8b%b2%e1%8c%8d-%e1%8a%a0%e1%89%a5%e1%88%ad%e1%88%83-%e1%88%88%e1%88%85%e1%8b%88%e1%88%93%e1%89%b5-%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%8c%88%e1%89%a1%e1%89%b5-%e1%8b%b0%e1%89%a5/ Tue, 05 Feb 2019 19:14:00 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1274 ለህወሃት ልዩ ዞን ፅ/ቤት አዲስ አበባ ላለፉት አመታት በህውሃት ድርጅት ስር ተደራጅቼ እንቅስቃሴ ሳደርግ እንደቆየሁ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም በፖለቲካው መስክ የመሳተፍ ፍላጎቱ ያልነበረኝ ቢሆንም በታሪክ አጋጣሚ የአገራችንን ፖለቲካ የመቀላቀል እድሉን አግኝቻለሁ፡፡ በተፈጠረው አጋጣሚም ስለሃገሬ የፖለቲካ ምንነት እና በፖለቲካ ገበያው ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦችንና ተቋማትን በቅርበት የማውቅና የመሳተፍ እድሉ ገጥሞኛል፡፡ በዛው ልክ ደግሞ በህወሀት […]]]>

ለህወሃት ልዩ ዞን ፅ/ቤት አዲስ አበባ

ላለፉት አመታት በህውሃት ድርጅት ስር ተደራጅቼ እንቅስቃሴ ሳደርግ እንደቆየሁ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም በፖለቲካው መስክ የመሳተፍ ፍላጎቱ ያልነበረኝ ቢሆንም በታሪክ አጋጣሚ የአገራችንን ፖለቲካ የመቀላቀል እድሉን አግኝቻለሁ፡፡ በተፈጠረው አጋጣሚም ስለሃገሬ የፖለቲካ ምንነት እና በፖለቲካ ገበያው ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦችንና ተቋማትን በቅርበት የማውቅና የመሳተፍ እድሉ ገጥሞኛል፡፡ በዛው ልክ ደግሞ በህወሀት ውስጥ አደርግ በነበረው ትሳትፎ በር የመዝጋት የመጠራጠርና እንደ ባዳ የመታየት ስሜት ከላይ እስከ ታች ድረስ አጋጥሞኛል፡፡ ገና ከጅምሩ ትግሉ ድርብ ድርብርብ ነበር ፡፡ በአንድ በኩል የመጣሁበት አካባቢ በክልሉ ፓለቲካ ውስጥ በዳርነት የሚመደብ ነውና አጠቃላይ ጉዞው እጅግ አቸጋሪ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቱ ወጣቶችን የመጠራጠርና ያለማመን ከፍተኛ ችግር የተንሰራፋበት ነውና እኔም እንደማንኛውም ወጣት ጉዞየ በሳንካ የተሞላ እንዲሆን አድርጎብኛል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአንድ ሙቀጫ መውቀጥ ጥሩ አይደለምና በህይወቴ ነገሮችን በተለየ መልኩ እንዳይ ያደረጉኝ እንዲሁም ትምህርት የሰጡኝ ጥቂት ሰዎች ነበሩና በነሱ ድጋፍና ምክር በችግርም ውስጥ ቢሆን እስካሁን ድረስ ለመዝለቅ ችያለሁ፡፡

በእርግጥም! በየሃገሬ ፖለቲካ ረጅም ርቀት ተጉዤ አስተቃጽኦ ላደርግበት የምችልና የሚገባ መሆኑን የማታ ማታ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ይሁንና ገና ከማለዳው ጀምሮ በህውሃት ውስጥ የነበረኝ የፖለቲካ ተሳትፎ አልጋ በአልጋ አልነበረም፡፡ በአጭሩ በሴራና በአሜኬላ የተሞላ ነበር ብሎ መናገር ማጋነን አይሆንም፡፡ ሆኖም ችግር ሲመጣ መሸሽና ማፈግፈግ ሳይሆን ፊት ለፊት ተጋፍጦና ተፋልሞ ማሸነፍ እንደሚገባ ላስተማረኝ ለውድ አያቴ ለሃዋደ ሻረው አቢቱ አበራ እና በአጠቃላይ ለራያ ማህበረሰብ ምስጋና ይግባውና ምርጫዬ “እግሬ አውጭኝ” ብሎ መሸሽ ሳይሆን አሜኬላውን መንቀልና ሴራውን ደግሞ ማፈራረስ ነበር፡፡

በአንፃራዊነት ከእድሜየና ከቆይታየ እንፃር ሲታይ በእርግጥ እድገቴ ፈጣን ነበር ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ ነገር ግን እድገቱ የመጣው በእኔ የስራ ፍላጎት እምነት ያላቸው የሌሎች ደርጅቶች የግንባሩ አመራሮች እየገፉና እየጠየቁ እንጅ በህወሀት በኩል እንደዛ አይነት ፍላጎት ስለነበረ አይደለም፡፡ እንዲያውም ቅናት ያደረባቸው አንዳንድ የህወሀት አመራሮች እድሉን ለማሰናከል ሲተጉ ተስተውላል ፡፡ አንዳንድ ግብዝ የዚህው ድርጅት አመራሮች ተመልሰው የማይገኙ በትላልቅ የአሜሪካ ትምህርት ቤቶች የመማር የነፃ የትምህርት እድልን ሳይቀር ትቼ አገሬን ለማገልገል በመወሰኔ በስልጣን ፍላጎት ከሰውኛል፡፡ በየቢሮው እየዞሩ የስልጣን ያለህ እያሉ የሚውሉት እነዚህ ግለሰቦች ከስልጣን ሲነሱ ደግሞ እንደ ልጅ እያለቀሱ የሚማፀኑ ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ የሚያስገርመው ነገር ደግሞ እያንዳንዱን እንጥፍጣፊ ስልጣን ለግል ጥቅምና ዝና ያላንዳች ርህራሄ የሚያውሉትና ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የስንቱን ምስኪን ህይወት የቀጠፉት እነዚህ ጨካኞች በግሌ ያገኘሁትን የነፃ የትምህርት እድልን መሰዋእት ያደረኩትን እኔን በስልጣን ፍላጎት ይከሳሉ፡፡

ይህን የመልቀቂያ ደብዳቤ እንዳዘጋጅና ከህወሀት ራሴን በፈቃዴ እንዳሰናብት በርካታ ገፊ ምክንያቶቼን እንደሚከተለው በዝርዝር የገለጽኩ ሲሆን የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች ሊረዱት የሚገባ ትልቅ ቁም ነገር ቢኖር ድርጅቱን በይፋ ለቅቄ ከመውጣቴ በፊት እንዲስተካከል የምችለውን ሁሉ ጥረት ማድረጌን ነው።

እስካሁን መልቀቂያ ሳላቀርብ የቆየሁበት ዋና ምክንያት ከዛሬ ነገ ወደ ማስተዋልና ካለፈው ተምረው በስተታቸውም ተጸጽተው ነገሮችን ያስተካክሉ ይሆናል በማለት ለዚህም ጊዜ መስጠቱ መልካም ነው ብዬ በማሰብ ነበር። ነገር ግን ይህንን እንደማያደርጉና ምንም የሚለወጥ ስብዕና እንደሌላቸው የስካሁኑ አካሄዳቸው ግልጽ ስላደረገልኝ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ደርሻለሁ።
በነዚህ ዓመታት በግሌ የምከተለውን አቋም እና የነበረኝን የትግል አካሄድ ትክክለኛነት እና ፍትሃዊነትን ተረድተው “አይዞህ” ብለው የሞራል ብርታት የሰጡኝ ከፍ ሲልም ከጎኔ ቆመው የታገሉ ጥቂቶች አልነበሩም፡፡ ነገር ግን ወደ ላይ በወጣሁ ቅጥር የተበጀልኝ ሴራ ይበልጥ እየተውሰበሰበ መጣ፡፡ በተለይም የጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዴሊቨሪ ሚኒስትር ሆኜ በተሾምኩ ማግስት ጀምሮ ጥቃቱ ተቋማዊ መልክ እየያዘና ትልልቅ ቱባ የህወሃት ባለስልጣናትም ጭምር የሚሳተፉበት ወደመሆን ተሸጋገረ፡፡ የፖለቲካ እስረኞችን ሙሉ በሙሉ ለመፍታትና የሰቆቃ ማእከል ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ማእከላዊ ተዘግቶ ወደ ሙዝየምነት እንዲቀየር ተወሰኖ ለመላው ህዝባችን ይፋ እንዲሆን ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በግለሰብ ደረጃ ይህ ነው የማይባል ጥቃትና ዛቻ እንዲሁም ማስፈራሪያ ደርሶብኛል፡፡

የአገሪቱ ቁንጮ የህወሐት ባለስልጣናት የተሳተፉበት ይኸው ጥቃት “ለምን የፖለቲካ እስረኛ አለ ብለህ ይፋ አወጣህ፤ ውሳኔው በቀጥታ twitter እና Facebook ለአለም በማሰራጨት የጠቅላይ ሚንስትርሩን ውሳኔ የማስቀየር እድላችንን ዝግ እንዲሆን አድርጋሀል ፤ በአጠቃላይ ከጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ፤ ከምክትል ጠቅላይ ምንስትር ከአቶ ደመቀ መኮንን፤ ከኦህዴድ አመራሮችና ከፈረንጆች ጋር ወግነህ የስርአት ለውጥ ለማምጣት የምትንቀሳቀስ የቀለም አብዮተኛ ነህ፤ ከዚህ በኋላ ከአንተ ጋር የምንነጋገረው በጥይት ነው!” በማለት ውሳኔው ከተላለፈባት ከዚያች ምሽት ጀምሮ ከፍተኛ ዛቻና የስነ-ልቦና ጫና ከትላልቅ የህወሐት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ በተለያዩ ወቅቶች ደርሶብኛል፡፡ እዚህ ላይ ግልፅ የሆነልኝ ነገር የድርጅቱ አመራሮች ምን ያክል እንደተበላሹና በታሰሩ ዜጎች መፈታት ምን ያክል እደሚያማቸው ነው፡፡ ጫናው ሲያይልና ይፋ የተደረገበት ምክንያት ግቡን ሲመታ በፌስቡክ ገፅ የተፃፈንውን ነገር ትንሽ ቆየት ብለንና በነጋታው ደግሞ በተለይም የውጭ ሚዲያ ወኪሎች የቀድሞውን ዘገባ እንዲያስተካክሉ አድርገናል፡፡ነገር ግን መረጃው አስቀድሞ በበቂ መጠን ስለተሰራጨ ግቡን ሊመታ ችላል፡፡
ከዛ በኋላም ቢሆን በነበሩት ተደጋጋሚ የህወሐት ስብሰባዎች ተመሳሳይ ስሞታና ዛቻ ደርሶብኛል፡፡ በእርግጥ አገራችንን ወደ ትልቅ እስር ቤት እየቀየራት የነበረው የጥቂት አምባገነኖች እርምጃ መቆም እንዳለበትና የነሱ ሰለባ የሆኑት የህሊና እስረኞች ከገባባቸው ነጻ መውጣት እንዳለባቸው ካመንኩኝ ውየ አድሬያለሁ፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ የታገልኩት የሰብአዊ መብት ለማክበር ነው፤ እስረኞች በህግ ጥላ ስር ሊመቱ አይገባም እያለ በአደባባይ ላይ ያለአንዳች ሃፍረት የሚለፍፍ ስርአት ራሱን ፉርሽ በሚያደርግ ሁኔታ ደብዳቢ እና ተጋራፊ ሆኖ መገኘቱ አንድ በቅርብ በማውቀው ወዳጄ ላይ ተከስቶ ካገኘሁት ጊዜ ጀምሮ የህሊና እረፍት ሊሰጠኝ ባለመቻሉ ይህ ሁኔታ መለወጥ እንዳለበት ካመንኩኝ ሰናባብቻለሁ፡፡
እናም መልካም እድልና ምቹ ሁኔታ ሲፈጠር መጠቀም ይገባ የነበረ በመሆኑ የህሊና እስረኞችን ለመታደግና ማዕከላዊን ወደ ሙዝየም ለመቀየር በተደረገው ጥረት ግንባር ቀደም ሚና ከተጫወቱ መሪዎች ጋር ሆኜ የድርሻዬን ተወጥቻለሁ፡፡ በዚህ ውሳኔ ሂደት ውስጥ የበኩሌን የጠብታ ታክል ድርሻ ተወጥቼ ከሆነ በህይወቴ የምኮራበት ትልቅ ተግባር እንጂ በምንም መልኩ አላፍርበትም፡፡ ሆኖም የአምባገነንነት እርካቡ እየተናደበት እንደነበር የገባው ህወሐት ውስጥ የመሸገው ቡድን በርግጎና በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ተነሳስቶ ለዚህ ውሳኔ ድርሻ ነበራቸው በሚላቸው ሃይሎች ያነጣጠረ እርምጃ መውሰድ መቼ ይቀርና!!

በተለይም ደግሞ አክራሪው ቡድን በህወሐት ውስጥ መሽጎ እንደሚገኝ የውስጥ አርበኛ ወስዶኝ ነበረና አንገቴን እንድደፋና ሸሽቼ እንድጠፋ ለማድረግ የተቀነባበረ የስም ማጥፋትና የጥቃት ውርጅብኝ ተካሂዶብኛል፡፡ ይህ ሁሉ ሁኔታ እየተካሄደ በነበረበት ሁኔታ እንኳን ምርጫየ ትግል እንጅ መፈርጠጥ አልነበረም፡፡
“ሳይደግስ አይጣላም!” እንዲሉ አበው . . . ከዛ በኋላ በፍጥነት በተቀያየረው ሃገራዊ ሁኔታ ትኩረታቸውን ስቦት እና አዛብቶት እንጅ የታሰበልኝን እና የተደገሰልኝማ ነገር አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነም ቢሆን ምርጫዬ መሸሽና አንገት መድፋት ሳይሆን አንገትን ቀና አድርጎ መታገል ነበር፡፡ ምክንያቱም ጥቃቱ በእኔ በግለሰብ ደረጃ ላይ ያነጣጠረ የነበረ በመሆኑ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የራያ ህዝብ ያለ ምርጫውና ያለውዴታው ገና ከማለዳው “ሆ. . .!” ብሎ የተቃመው አከላለል ከተወሰነበት ጊዜ ጀምሮ መግደልና ማሳደድን መቀጠላቸው ህዝቡም በተደራጀ መልኩም ባይሆን ትግሉ አላቆመም ነበር፡፡ የራያ ህዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ካደረጉት መሰረታዊ ምክንያቶች/ጉዳዮች አንዱ ትግሉ በተደራጀ መንገድ አለመከናወኑ መሆኑን አውቆ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተደራጀ መንገድ ወደ ትግል ገብቷል፡፡ ወንድሜ ከሆነውና በጠንካራ ማህበረሰባዊና ስነልቦናዊ ገመድ ከተሳሰርኩት የአማራ ህዝብ ጋር አብሬ ልኑር ብሎም እየተዋደቀ ይገኛል፡፡

ይህ ሲሆን ታዲያ የኢትዮጵያ የናሽናል ጥያቄ (የብሄረሰቦች ጥያቄ) ብዝሃነትን የማስተናገድ ችሎታ እጦት ነውና “ኢትዮጵያ ብዝሃነትን ልታከብር ይገባታል!” ብሎ በፕሮግራሙ ላይ በነጭና በጥቁር በደማቁ የጻፈው እንዲሁም በዛ ላይ ተመስርቶም ላለፉት 45 አመታት የፖለቲካ ሞብላይዜሽን ያደረገው ህወሐት ምላሽ ጥይት፤ ግድያ፤ ማፈናቀልና እንግልት ሆኗል፡፡

ነገሩ “ሆድ ሲያውቅ ደሮ ማታ ነው!” እና ድርጅቱ ለፕሮግራሙና ለዚያም ሲባል መስዋእት ለሆኑት ታጋዮቹ ክብር እንደሌለው በአደባባይ አስመስክሯል፡፡ የማንነት ጥያቄን ያነሱ እምቦቃቅላ ህጻናትን እስከ አፍንጫው በታጠቀው የክልሉ ልዩ ሃይል አናት አናታቸው እየተመቱ በእንጭጩ ተቀጭተዋል፡፡

በአጠቃላይ የራያ ህዝብ የተደራጀ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የስንቱ ህይወት እንደተቀጠፈ፤ ለእስር እንደተዳረገና እንደተፈናቀለ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ አካባቢው በዚህ ምክንያት ለከፋ ማህበራዊ መስቅልቅልና ቀውስ እንዲሁም ለጸጥታ ቀውስና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ተዳርጓል፡፡ በራያ ህዝብ ላይ ይህን የመሰለ ግፍና መከራ እየፈጸመ ካለ ድርጅት ጋር አብሬ እንድቀጥል ህሊናዬ አልፈቀደልኝም፡፡

በእርግጥ ገና ከገባሁ በጥቂት አመታት ውስጥ ልቤ ሸፍቶ በመንፈስ የራቅኩት ድርጅት ዛሬ ቀኑ ደርሶ በወጉ የአባልነት ግንኝነታችን ያበቃ ዘንድ የራያው ጉዳይ አንዱ ምክንያት ሆኗል፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ የለውጥ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በእርግጥ የአገራችን ችግር መሰረታዊ ለውጥ የሚሻና ውስብስብ ቢሆንም ችግሩን የሚመጥን መሰረታዊ የለውጥ ፕሮግራም ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ መናገር ይቻላል፡፡

ህወሐት በጥቂት ጠባብ ጸረ ለውጥ ቡድን ተጠልፎ ከሃገራዊ ለውጥ ጎን መቆም ሳይሆን ፀረ- አቋምን ምርጫው አድርጎ ለውጡ የትግራይን ህዝብ ጨምሮ መላው የአገሪቱ ህዝብ የሚጠቅም ቢሆንም ቅሉ፤ የውስን ሰዎች ጥቅም የሚያስቀር ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ድርጅቱ ሊታገልለት የሚገባውን የትግራይ ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ሳይሆን የጥቂት የህወሐት ባለስልጣናት ጥቅም ለማስከበር ሲል ለውጡን ተቃርኖ ብቻ ሳይሆን አፍራሽ በሆነ የሰላ ጥግ ላይ ቆሟል፡፡

በመሰረቱ ዲሞክራሲም ሆነ እኩልነት የትግራይ ህዝብ ለዘመናት የታገለላቸው እና ውድ ልጆቹን የገበረላቸው የህልውና ጥያቄዎች እንጂ ባለጋራዎቹ አይደሉም፡፡ አዲሱ የለውጥ ፕሮግራምም ተንጋዶ የበቀለውንና የማቃናትና አሜኬላውን የመንቀል እንጅ ከትግራይ ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ተቃርኖ የመጣ አይደለም፡፡ ህወሐት በዚህ ታሪካዊ ወቅት እየተወሰደ ያለውን ትክክለኛ እርምጃ የመቃወም ግዙፍ ስህተት ከድርጅቱ ጋር አብሬ እንዳልቀጥል ካደረጉኝ መሰረታዊ ምክንያቶች ሁለተኛው ነው፡፡

ከዛሬ ነገ ችግሮች ተቀርፈውና ተሻሽለው ከመስመር የወጡ አካሄዶችም ፈር ይዘው ይራመዳሉ በሚል ትዕግስትና ተስፋ ፤ ብዙ ነገሮችን በራሴ ይዤ እየታገልኩ ቆይቻለሁ:: በግሌም ሆነ በተገኘሁበት ማህበረሰብ ላይ እጅግ መራር ውርጅብኝ እየወረደ፤ ይባስ ብሎም በአገር ደረጃ ነገሮች እየተበለሻሹ እየሄዱ እንኳ ነገሮችን ለማቃናትና ለማሻሻል የበኩሌን እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ አካሂጃለሁ:: የሆነ ሆኖ ከግትር አቋማቸው ፈቀቅ የማይሉ ተቸካዮች በህዝብና በአገር ላይ የሚያደርሱት ግፍ አልበቃ ብሏቸው፤ በተገኘችው ጭላንጭል ዕድል ይህን መከራ ለማስቆም የሞከርኩትን ግለሰብ ስም ለማጥፋት በየመንደሩ ሲባዝኑ ይውላሉ::

ከጥንት ጀምሮ ለነፃነት ከኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር አብሮ የተዋደቀውን የትግራይ ህዝብ፤ ዛሬ እንደሰብዓዊ ምሽግ ተጠቅመው ሊለያዩት ቢሞክሩም ፤ ይህ የአክራሪ ወንጀለኞች የቀን ቅዠት እንደጉም መብነኑ እና መክሸፉም የማይቀር ነው! ኢትዮጵያዊነትን ከትግራይ ህዝብ ልብ ላይ መፋቅ ከቶም የማይቻልና ዛሬም ቢሆን እላዩ ላይ ተጋድመው የተጫኑትን የቀንበር እንጨቶች ሰብሮ ዳግም ለእኩልነትና ነፃነት እንደሚበቃ ቅንጣት ጥርጥር የለኝም!

በመጨረሻም ፀረ-ለውጥ እና ፀረ-ዴሞክራሲ ከሆነው ድርጅት ጋር ለመቀጠል ህሊናዬ ባለመፍቀዱ በገዛ ፍቃዴ ከድርጅት አባልነት የለቀቅኩኝ መሆኑን እያሳወቅኩ በቅርቡ ያታግለኛል ከምለው ድርጅት ጋር ተደራጅቼ የራያና መላ የአገሬ ራችን ህዝብ ጥያቄ ይበልጥ መልስ እንዲያገኝና ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተደረገ ያለውን ርብርብ አቅም በፈቀደው ሁሉ ለማገዝና ለመታገል እንደምሰራ ከወዲሁ ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡ የራያ ህዝብ በተድላና በፍቅር ከወሎ አማራና ከመላው የአማራ ህዝብ ጋር ለዘላለሙ ይኖራል ። ምክንያቶቹ በትንሹ እነዚህ ሲሆኑ በማወቅም ይሁን ባለማቅ በስካሁኑ የፓለቲካ ህይወቴ ያስቀየምኳችሁ ካላችሁ ከልብ የመነጨ ይቅርታን እጠይቃቹሃለው።

ዛዲግ አብርሀ
ድልና ነፃነት ለራያ ህዝብ !!!!!
ዴሞክራሲና ሰላም ለመላ የአገራችን ህዝብ!!!!!!
ገጽ 5

]]>
ሞቶ የተገኘውና ወላጆቹ አልቅሰው የቀበሩት ወጣት ከሳምንታት በኋላ ወደ ወላጆቹ ተመለሰ http://konjoethiopia.com/2019/01/30/%e1%88%9e%e1%89%b6-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%88%e1%8a%98%e1%8b%8d%e1%8a%93-%e1%8b%88%e1%88%8b%e1%8c%86%e1%89%b9-%e1%8a%a0%e1%88%8d%e1%89%85%e1%88%b0%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%89%80%e1%89%a0%e1%88%a9/ Wed, 30 Jan 2019 13:03:34 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1269 ሞተ የተባለው ሰው አልሞትኩም ብሎ መጣ! • ሞቶ የተገኘውና ወላጆቹ አልቅሰው የቀበሩት ወጣት ከሳምንታት በኋላ ወደ ወላጆቹ ተመልሷል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤ ሕዳር 19 ቀን 2011ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳደር አንድ ወጣት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ ይገኛል፡፡ ይህም ከፖሊስ ጆሮ ይደርሳል፡፡ ጉዳዩን የሰማው ፖሊስ የሟችንም ሆነ የገዳይን ማንነት ለማወቅ ያደረገው ጥረት ለጊዜው ሳይሳካለት ይቀራል፡፡ […]]]>

ሞተ የተባለው ሰው አልሞትኩም ብሎ መጣ!

• ሞቶ የተገኘውና ወላጆቹ አልቅሰው የቀበሩት ወጣት ከሳምንታት በኋላ ወደ ወላጆቹ ተመልሷል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፤ ሕዳር 19 ቀን 2011ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳደር አንድ ወጣት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ ይገኛል፡፡ ይህም ከፖሊስ ጆሮ ይደርሳል፡፡
ጉዳዩን የሰማው ፖሊስ የሟችንም ሆነ የገዳይን ማንነት ለማወቅ ያደረገው ጥረት ለጊዜው ሳይሳካለት ይቀራል፡፡ የወንጀሉ መርማሪ ሳጅን አየነው ጎበዜ እንዳሉት ማንነቱ ያልታወቀውን ሟች ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ወደ ቆቦ ሆስፒታል ይወስዱታል፡፡

ነገር ግን ሐሙስ ሕዳር 20 ቀን 2011ዓ.ም ከሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 02 ቀበሌ ገረገራ አካባቢ ከምሽቱ 5፡00 አቶ ታረቀ መንግሥቴ የተባሉ ሰው ወደ ፖሊስ በመሄድ ‹‹ሟች የእኔ ልጅ ነው›› በማለት በኮንትራት መኪና አስከሬኑን መውሰዳቸውን ሳጅን አየነው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

አቶ ታረቀ ልጃቸውን ከቀበሩ በኋላ ሕዳር 24 ቀን ወደ ቆቦ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በመሄድ ክስ መመሥረታቸውንና የልጃቸው ገዳዮች እንዲነግሯቸው መጠየቃቸውንና ፖሊስ በግድያው ዙሪያ የደረሰበትን ለአባት መንገሩን ሳጅን አየነው አስረድተዋል፡፡
አባት አስከሬኑን ሊረከቡ በመጡበት ጊዜ ስለልጃቸው የሚያውቁትን ልዩ ምልክት ተጠይቀው እንደተናገሩና የሟቹን ፎቶግራፍ ሲያዩ በጣም እንዳለቀሱ፤ እንዳጽናኗቸውም መርማሪ ፖሊሱ ተናግረዋል፡፡

የልጃቸውን አስከሬን ከፖሊስ ተቀብለው ሌሊቱን ሲጓዙ ያደሩት አቶ ታረቀ ሕዳር 21 ቀን 2011ዓ.ም ወዳጅ ዘመድ እያስተዛዘናቸው በፍላቂት ገረገራ ደብረ ሃይማኖት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩን ያስፈጽማሉ፡፡
‹‹ቆቦ ሰው መሞቱንና የመቄት ሰው ነው መባሉን ስሰማ አጣራሁ፤ ሊቀበር መሆኑን ስሰማም ለማጣራት ሄድኩ፡፡ ደርሼም አስከሬኑን አገላብጨ አየሁ፤ ልጄ ነው፡፡ አምጥቼ ከዘመድ ወዳጅ ጋር ሆኜ ቀበርኩ፡፡ ሥርዓተ ፍትሐቱንም አስፈጸምኩ፤ ሳልስት፣ ሰባት አስቀደስኩለት፡፡ ሰላሳውን ላስቀድስ እየተዘጋጀሁ ሳለ ግን ነገሮች ተቀዬሩ›› ብለዋል አቶ ታረቀ መንግሥቴ ለአብመድ ሲናገሩ፡፡
‹‹ድንገት ስልክ ተደወለ፤ አነሳሁት፡፡ ‹ሞቷል ብላችሁ እንዳለቀሳችሁ ሰምቻለሁ› ብሎ ልጀ ደወለ፡፡ እሱ መሆኑን ስላላመንኩት የተለያዬ ዘመድ እንዲጠራ አደረኩት፤ ተጠራልኝ፡፡ ከዚያም ወደ ቤተሰቡ መጣ›› ብለዋል አባት፡፡

በወቅቱ የሟችን አስከሬን ሲያዩ ከእጁ ጣት ላይና ከጥርሱ ልዩ ምልክትን መሠረት አድርገው ልጃቸው መሆኑን እንዳረጋገጡ የገለጹት አባት ስለተፈጠረው ነገር ተገርመዋል፡፡
‹‹ሞቷል›› ተብሎ የተለቀሰለት አበበ ቤተሰቦቹ ለማመን መቸገራቸውን ገልፆ ‹‹ከሟች ጋር እንዴት እንደተመሳሰልኩ ገርሞኛል፡፡ ለማንኛውም አሁን በወላጆቼ ፊት በመገኜቴና በሕይወት በመሆኔ ደስተኛ ነኝ›› ብሏል፡፡
ምንጭ ፡ አማራ መገናኛ ብዙሃን

]]>
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የአክሲዮን ባለቤት ሊሆኑ ነው ። http://konjoethiopia.com/2019/01/30/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8a%a0%e1%8b%a8%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8b%b5-%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%89%b0%e1%8a%9e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8a%ad/ Wed, 30 Jan 2019 12:50:10 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1265 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ባስገነባው የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ሠራተኞቹ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት እንዲሆኑ እንደወሰነ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ግሩፕ እሑድ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀክትና ያስገነባውን ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ባስመረቀበት ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ባሰሙት ንግግር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደረሰበት የስኬት […]]]>

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ባስገነባው የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ሠራተኞቹ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት እንዲሆኑ እንደወሰነ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ግሩፕ እሑድ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀክትና ያስገነባውን ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ባስመረቀበት ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ባሰሙት ንግግር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደረሰበት የስኬት ደረጃ የበቃው ከ16,000 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞቹ በትጋት በመሥራታቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የሠራተኛውን የባለቤትነት ስሜት ለመጨመር የአየር መንገዱ ሠራተኞች በስካይላይት ሆቴል የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት እንዲሆኑ፣ ማኔጅመንቱና የዳይሬክተሮች ቦርድ እንደወሰኑ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሠራተኞቻችን ይህን ወርቃማ ዕድል እንዲጠቀሙበት ጥሪዬን አቀርባለሁ፤›› ብለዋል፡፡

በ65 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በ42,000 ካሬ ሜትር ላይ የተገነባው ስካይላይት ሆቴል 373 የመኝታ ክፍሎች፣ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ሦስት ምግብ ቤቶች፣ ሦስት ቡና ቤቶች፣ የጤና ማዕከል፣ የመዋኛ ገንዳ፣ አነስተኛ የጎልፍ መጫወቻ ሜዳና ሌሎች በርካታ የሆቴል አገልግሎቶች አሟልቶ የያዘ ነው፡፡

አየር መንገዱ በሁለተኛ ምዕራፍ የሚገነባው ሆቴል 627 ክፍሎች እንደሚኖሩትና 150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ተገልጿል፡፡

አየር መንገዱ ለሠራተኞቹ ግዙፍ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ቀርፆ ተግባራዊ በመሆን ላይ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ተወልደ 1,200 ቤቶች ተጠናቀው ሠራተኞች መረከባቸውን ገልጸው፣ 12,000 የመኖሪያ ቤት አፓርትመንቶች ገንብቶ በጥቂት ዓመታት ውስጥ እንደሚያስረክብ ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃና ስካይላይት ሆቴልን በክብር እንግድነት መርቀው የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አየር መንገዱ የገነባቸውን የአቪዬሽን አካዴሚ፣ የጥገና ማዕከል ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ አየር መንገዱ በገነባቸው ዘመናዊ የአቪዬሽን መሠረተ ልማቶች መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹በየአገሩ ስንሄድ የማየውን አገሬ ላይ እንዳይ ስላደረጋችሁኝ አኩርታችሁኛል፤›› ብለዋል፡፡

አየር መንገዱ ጠንካራ የማሠልጠኛ ተቋም፣ የጥገና ማዕከልና የካርጎ ተርሚናል መገንባቱን ጠቁመው የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ እንዲገነባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በተገኙት ስኬቶች ሳይዘናጉ ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች እንዲያስቡ ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ 100 ሚሊዮን መንገደኞች የሚያስተናግድ ግዙፍ ኤርፖርት እንዲገነቡ አሳስበዋል፡፡

መላ የአየር መንገዱን ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላት ያመሠገኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ግርማ ዋቄና ለአቶ ተወልደ ልዩ ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡ ኩባንያው የሠራተኞቹ የአክሲዮን ባለቤት እንዲሆኑ መጋበዙ ሠራተኞች ተቀጣሪ ብቻ ሳይሆኑ ባለቤት ሊሆኑ እንደሚችሉ፣ ለሌሎች ተቋማትም ትምህርት የሚሆን ዕርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሙስሊም፣ ክርስቲያን ሳንል እንዲህ ያለ ያማረ ሥራ መሥራት አለብን፡፡ የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ አየር መንገዱን ወደ ኋላ መመለስ የለበትም፤›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ መንግሥት በአየር መንገዱ ማኔጅመንት ሥራ ጣልቃ እንደማይገባ ይልቁንም የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ከአራት ዓመት በፊት ግንባታውን በ245 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያስጀመረው የአዲስ አበባ ኤርፖርት ተርሚናል ማስፋፊያ ፕሮጀክት፣ በሒደት በተካተቱ ተጨማሪ ሥራዎች ወጪው ወደ 363 ሚሊዮን ዶላር አድጓል፡፡

ግንባታው በሦስት ምዕራፍ ተከፈሎ የሚካሄድ ነው፡፡ የመጀመርያው ምዕራፍ የምዕራብና ምሥራቅ ክንፍ ሕንፃ ግንባታ፣ ሁለተኛው ምዕራፍ የቪአይፒ ተርሚናል ግንባታና ሦስተኛ ምዕራፍ የአገር ውስጥ ተርሚናል ማስፋፊያ ናቸው፡፡ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎችና የመዳረሻ መንገዶች ግንባታ በፕሮጀክቱ ተካተዋል፡፡

የዋናው ተርሚናል ግንባታ 86 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የቪአይፒ ተርሚናሉ ግንባታ ከአንድ ዓመት በፊት ተጀምሯል፡፡ የአገር ውስጥ ተርሚናል ማስፋፊያ ሥራም በቅርቡ ተጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ ዳዊት ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ አዲስ አበባ በአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ቀዳሚ መዳረሻ ትሆናለች፡፡

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ በነሐሴ 2009 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አቪዬሽን ግሩፕ እንዲቀላቀል መደረጉ ይታወሳል፡፡ ዋናው ተርሚናል እ.ኤ.አ. 2003 ዓ.ም. ሲመረቅ በዓመት ስድስት ሚሊዮን መንገደኞች የማስተናገድ አቅም እንዳለው ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ብሔራዊ አየር መንገዱ ከተገመተው በላይ በማደጉ ምክንያት በዓመት 11 ሚሊዮን መንገደኞች በማስተናገድ ላይ ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ የተፈጠረውን መጨናነቅ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀርፈው ይታመናል፡፡

አሁን ያለው ተርሚናል የወለል ስፋት 48,000 ካሬ ሜትር ሲሆን፣ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ አዲስ የተገነባው ሕንፃ ወለል ስፋት 74,000 ካሬ ሜትር ነው፡፡

አዲሱ ሕንፃ 72 የመንገደኛ ማስተናገጃ መስኮቶችና 21 የመሳፈሪያ ቢሮዎች አሉት፡፡ ግንባታው በሰኔ 2011 ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ የፕሮጀክቱ ዋና መሐንዲስ አቶ ኃይሉ ለሙ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የቪአይፒ ተርሚናሉ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ የአገር ውስጥ ተርሚናሉ ማስፋፊያ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ አቶ ኃይሉ ገልጸዋል፡፡ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ የተርሚናሉን የማስተናገድ አቅም በዓመት ከ11 ሚሊዮን ወደ 22 ሚሊዮን መንገደኞች እንደሚያሳድገው ተገልጿል፡

Source ፡ ሪፖርተር

]]>
በአምስት ቀናት 18 ባንኮች ተዘርፈዋል ። http://konjoethiopia.com/2019/01/15/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%89%b5-%e1%89%80%e1%8a%93%e1%89%b5-18-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ae%e1%89%bd-%e1%89%b0%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%8d%88%e1%8b%8b%e1%88%8d-%e1%8d%a2/ Tue, 15 Jan 2019 16:13:21 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1261 በምዕራብ ኦሮሚያ 3 ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስትና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የክልሉ መንግስት ገለፀ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ፥ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ ምእራብ ወለጋ፣ […]]]>

በምዕራብ ኦሮሚያ 3 ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስትና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የክልሉ መንግስት ገለፀ
በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ፥ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 18 ባንኮች ላይ ነው ዝርፊያው የተፈፀመው።
ዝርፊያውም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ላይ ነው የተፈፀመው ያለው ቢሮው፥ ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ተቋም ላይም ዝርፊያ መፈፀሙን አስታውቋል።
ከባንኮች ዝርፊያ በተጨማሪም የተለያዩ የግል እና የመንግስት ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱንም ቢሮው በመግለጫው አክሎ አስታውቋል።
በዚህም ቁጥራቸው 10 የሚደርሱ የመንግስት እና የግል ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው በመግለጫው ተመልክቷል።
ከዚህ በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሱት ዞኖች የመንግስት መሳሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል ያለው ቢሮው፥ የተለያዩ የስራ ሰነዶችን የማቃጠል እና የማውደም፣ የመንግስት ተሽከርካሪ እና የግል ንብረቶች ዝርፊያ እንዲሁም መንገድ በመዝጋት የህዝቡን የመንቀሳቀስ መብት የመገደብ ተግባር ተፈፅሟል ብሏል።
እንዲህ አይነቱን ህገ ወጥ ተግባርም ህዝቡ አምርሮ በመቃወም አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ ከመንግስት እና ከፀጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
በዚሁ መሰረት ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ቢሮው ያስታወቀው።
ይህንን የወንጀል ተግባር በማቀነባበር እና በመፈፀም የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በህግ ቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑንም ገልጿል።
በአሁኑ ወቅትም የህግ የበላይነትን ለማስከበር እና የህዝቡን ደህንነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለው ስራም በምእራብ ኦሮሚያ ያለው የሰላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱንም ጠቅሷል።
አሁን የተገኘው የሰላም ሁኔታ ቀጣይነት እንዲኖረውም የአካባቢው ህዝብ እና መንግስት ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን እየሰሩ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።
በተመሳሳይ የደቡብ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጦር የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች ያቀረቡለትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላማዊ ትግል እየተመለሱ መሆኑን ቢሮው በመግለጫው ጠቅሷል።
በዚህም መሰረት ኤሊያስ ጋምቤላ ጎሎ የሚመራው የጉጂ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጦር ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ወደተዘጋጀለት ማረፊያ እየገባ መሆኑንም አስታውቋል።
Source Fbc

]]>
በኦሮሚያ ባንክ ላይ የተፈፀመው የ80 ሚሊየን ብሩ የዘረፋ ድራማ http://konjoethiopia.com/2019/01/11/%e1%89%a0%e1%8a%a6%e1%88%ae%e1%88%9a%e1%8b%ab-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ad-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8d%88%e1%8d%80%e1%88%98%e1%8b%8d-%e1%8b%a880-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95/ Fri, 11 Jan 2019 14:29:55 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1258 ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ንብረት የሆነ ገንዘብ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላው ሲዘዋወር እንደተዘረፈ ተሰምቷል። ታህሳስ 19፣ 2011 ዓ. ም. በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና ከተማ ጭሮ ውስጥ የሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 80 ሚሊዮን ብር ወጭ ያደርጋል። ገንዘቡን ወደ ደብረ ዘይት ቅርንጫፉ ለማዘዋወርም ጉዞ ይጀምራል። ሆኖም ገንዘቡን የጫነው መኪና የታሰበበት ሳይደርስ መኤሶ ወረዳ […]]]>

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ንብረት የሆነ ገንዘብ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላው ሲዘዋወር እንደተዘረፈ ተሰምቷል።

ታህሳስ 19፣ 2011 ዓ. ም. በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና ከተማ ጭሮ ውስጥ የሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 80 ሚሊዮን ብር ወጭ ያደርጋል።

ገንዘቡን ወደ ደብረ ዘይት ቅርንጫፉ ለማዘዋወርም ጉዞ ይጀምራል። ሆኖም ገንዘቡን የጫነው መኪና የታሰበበት ሳይደርስ መኤሶ ወረዳ አሰቦት አካባቢ መሳሪያ በያዙ ሰዎች ተከበበ።

ከዚያስ? የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሐላፊ ኮማንደር ጋዲሳ ንጉሳ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን ብለዋል ” የተወሰኑ ኃይሎች ሽጉጥ የያዙ እንዲሁም ባዶ እጃቸውን የነበሩ ግለሰቦች መኪናውን መንገድ ላይ አስቆሙት። ሾፌሩን አስፈራርተው በማስወረድ አሰቦት ወደምትባል አካባቢ መኪናዋን ወሰዷት”

ከተዘረፈው 80 ሚሊዮን ብር ውስጥ በሽምግልና፣ በድርድርና በፍተሻ ማስመለስ የቻሉት ገንዘብ እንዳለም ይናገራሉ።

ይህን ያህል ገንዘብ አስመልሰናል ለማለት ሰነድ ባያጠናቅሩም “እጅ ከፍንጅ የተያዘ ገንዘብ የለም። አብዛኛው ብር የተመለሰው በጥቆማ ነው። በርካታ መኪና ይዘው ሲሄዱ በፍተሻ የተያዙ አሉ” ብለዋል።

ለመሆኑ አንድ ባንክ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ገንዘብ ሲያዘዋውር የሚደረግለት የጥበቃ ኃይል ወደየት ሄዶ ነው ዝርፊያው ሊፈፀም የቻለው? በሚል ቢቢሲ ኮማንደሩን ጠይቋል።

“በወቅቱ አብረው የነበሩት ፖሊሶች ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ መያዝ አልቻሉም። ወደ ሌላ እርምጃ ከተገባ በነሱም ደህንነት ላይ አደጋ ስለሚመጣ በልመናና በድርድር ገንዘቡን መውሰድ እንዲያቆሙ ለማድረግ ተሞክሯል። ማስፈራራትና ወደ ሰማይም ተተኩሷል።”

ዘራፊዎቹ በቁጥር ብዙ እንደነበሩ የሚናገሩት ኮማንደሩ፤ ዘራፊዎቹ ገንዘቡን ከዘረፉበት ቦታ ወደ ከተማ ይዘው ከሄዱ በኋላ ለመከፋፈል ሲሞክሩ የከተማው ከንቲባ “የሕዝብ ንብረት ነው” ብለው በድርድር ለማስቆም ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ይገልጻሉ።

ፎርቹን ጋዜጣ፤ ብሩ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ ላይ እንደነበር ጠቅሶ 100 ግለሰቦች በዝርፊያው ተጠርጥረው ተይዘዋል ሲል ዘግቧል።

ከዘረፋው ጀርባ ያሉ ሰዎችን ማንነት ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ኮማንደሩ ቢናገሩም፤ “ዘራፊዎቹ ከሩቅ የመጡ አይደሉም” የሚል ጥቆማ ሰጥተዋል።

ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከድሬዳዋ ቅርንጫፍ 80 ሚሊዮን ብር ጭኖ በመኢሶ ወረዳ ሲተላለፍ ነበር። ያኔ ገንዘቡን ይዞ ይጓዝ የነበረው መኪና አሽከርካሪ አህያ ገጭቶ በአካባቢው ፖሊስ ተይዟል። በወቅቱ የተገኘው ገንዘብና አጓጓዡ የያዘው ሰነድ ላይ የሰፈረው የገንዘብ መጠን መካከል ልዩነት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

ገንዘቡን መጫን የነበረበት መኪና ሰሌዳ ቁጥርና በፖሊስ የተያዘው መኪና ታርጋ ቁጥርም የተለያየ ነው ተብሎ ነበር። ለመሆኑ የዚህ ገንዘብ ጉዳይ ከምን ደረሰ? ኮማንደር ጋዲሳ ምላሽ አላቸው።

“አምሳ ሚሊዮኑን የሚያሳይ ሰነድ በገንዘብ ያዡ እጅ አልነበረም። ይህም ከኔትወርክ ችግር ጋር የተያያዘ ነው። መንገድ ላይ በኢሜይል እንልክላችኋለን የሚል ነገር ነበር”

ገንዘቡ ከወጣበት ቅርንጫፍ ጀምሮ ስለነበረው ሂደት ምርመራ ተእየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

መጀመሪያ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የነበረው መኪና ሰሌዳው ቁጥር ሌላ ሲሆን፤ ይህም በአጋጣሚ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የታሰበው ሾፌር በህመም ላይ ስለነበር ነው ብለዋል።

“ስለ ሹፌር ለውጥ የሚገልጽ ደብዳቤ ሳይቀየርብ ሌላ መኪና በመተካቱ ነው” ሲሉ የድሬዳዋ ስራ አስኪያጅ እንደነገሯቸው ኮማንደሩ ገልፀዋል።

“ገንዘቡ ህጋዊ መሆኑን ነው የምናውቀው። አሁን ምርመራ ላይ ነው። በቅርብ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ” ብለዋል።

መኪና ውስጥ የተገኘው ገንዘብ ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ ገንዘቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ቅርንጫፍ ውስጥ እንዲቆይ መወሰኑንም ኮማንደር ጋዲሳ ገልፀዋል።

ምንጭ ቢቢሲ

]]>
ጃዋር መሃመድ በለውጡ ሂደት ውስጥ የእሱን ሚና የገለፀበት አስገራሚ አባባል ። http://konjoethiopia.com/2019/01/09/%e1%8c%83%e1%8b%8b%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%88%83%e1%88%98%e1%8b%b5-%e1%89%a0%e1%88%88%e1%8b%8d%e1%8c%a1-%e1%88%82%e1%8b%b0%e1%89%b5-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%8a%a5%e1%88%b1%e1%8a%95/ Wed, 09 Jan 2019 15:00:45 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1252 “ዶ/ር አብይ ማለት አሁን የምንጓዝበት ባስ ሹፌር ነው። እኔ ደግሞ ከረዳቶቹ መካከል ነኝ። እንደረዳት ተሳፋሪው ችግር ሲፈጥር አረጋጋለሁ፤ ሾፌሩ እንቅልፍ እንዳይወስደው አነቃዋለሁ። ፍጥነቱን ጨምሮ ከተገቢ በላይ ከተጓዘ እንዲቀንሰው፣ ከተገቢው በታች በዝግታ ከተጓዘ ደግሞ ጨመር እንዲያረግበት አማክረዋለሁ፤ ግን ዝም ብለህ እያጨበጨብክ ብቻ ተከተለኝ ካለ absolutely wrong. ከኔም ይሁን ከወንድሞቼ የሚጠበቀው ዝም ብሎ እጅ ማጨብጨብ ሳይሆን መንገዱን […]]]>

“ዶ/ር አብይ ማለት አሁን የምንጓዝበት ባስ ሹፌር ነው።
እኔ ደግሞ ከረዳቶቹ መካከል ነኝ። እንደረዳት ተሳፋሪው ችግር ሲፈጥር አረጋጋለሁ፤ ሾፌሩ እንቅልፍ እንዳይወስደው አነቃዋለሁ። ፍጥነቱን ጨምሮ ከተገቢ በላይ ከተጓዘ እንዲቀንሰው፣ ከተገቢው በታች በዝግታ ከተጓዘ ደግሞ ጨመር እንዲያረግበት አማክረዋለሁ፤ ግን ዝም ብለህ እያጨበጨብክ ብቻ ተከተለኝ ካለ absolutely wrong.

ከኔም ይሁን ከወንድሞቼ የሚጠበቀው ዝም ብሎ እጅ ማጨብጨብ ሳይሆን መንገዱን ማየት፤ ተሳፋሪውን መመልከት፤ ጎማውን ተመልክቶ አየር ከጎደለው መሙላትና ሾፌሩ ደግሞ ሲሳሳት ሹፌሩ ያላየውን ረዳቱ በደንብ ስለሚመለከተው መምከር ነው። ባሱ እንኳን ትንሽ ችግር ቢኖርበት #ወርዶ ታኮ አስገብቶ የሚያስተካክለው ረዳቱ ነው።
ከዚህ ውጪ ዛሬ ከኛበላይ የሱ ደጋፊ የለም ብሎ ሚያጨበጭበው ሀገራችን የሆነ ችግር ውስጥ ብትገባ ከውጪየመጡት ወደመጡበት ይወጣሉ። ሀገር ውስጥ ያሉት ደግሞ እኔ_አላውቅም እንደሚሉ በሚገባ እናቃለን።

መንግስታች ትክክል ሲሰራ ልክ ነው እንላለን፤ መንግስታችን ላይ ጠላት ሲነሳ ጠላት ላይ እንነሳለን። መንግስት ሲያጠፋ ደግሞ ስህተቱን ነግረን ወደ መንገዱ እንዲመለስ እናረጋለን።
(Jawar Mohammed)

]]>
” አቶ ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ ተኩስ መግጠም አስፈላጊ አይደለም” የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ http://konjoethiopia.com/2019/01/02/%e1%8a%a0%e1%89%b6-%e1%8c%8c%e1%89%b3%e1%89%b8%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%88%b0%e1%8d%8b%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%88%98%e1%8b%ab%e1%8b%9d-%e1%89%b0%e1%8a%a9%e1%88%b5-%e1%88%98%e1%8c%8d%e1%8c%a0%e1%88%9d/ Wed, 02 Jan 2019 12:41:57 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1244 ቁጥራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ የአገሪቱ ዜጎች የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፤ የ2011 በጀት ዓመት የአምስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለ5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ተቋሙ […]]]>

ቁጥራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ በርካታ የአገሪቱ ዜጎች የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፤ የ2011 በጀት ዓመት የአምስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለ5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ተቋሙ በሚመጡ ጥቆማዎች ከአንድ ቤተሰብ ብቻ ከአራት በላይ የቤተሰብ አባላት እንደተያዙ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ተቋሙም ይህን መነሻ አድርጎ የማጥራት ሥራ ቢሠራም ግለሰቦቹ ሲያዙ የፍርድ ቤት ትዕዛዝም ሆነ ያዢው ማን እንደሆነ በውል ባለመታወቁ ሥራውን በሚፈለገው ደረጃ ለማከናወን ተቸግሯል፡፡

በከባድ የአገር ሀብት ምዝበራ ወንጀልና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው ከተያዙ ግለሰቦች ውጪ አሁንም በመንግሥት የሥራ ኃላፊነትና በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ተሳታፊ  መሆናቸውን ጠቅሰው፣  ሕግን መሠረት ባደረገ መልኩ በተደራጀ ሁኔታ የተቀነባበሩ በመሆናቸው ምርመራውን አዳጋችና ተጠርጣሪዎችን ወደ ሕግ የማቅረብ ሂደቱን ፈታኝ አድርጎታል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ከአገር ውጭ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በኢንተርፖል እየመጡ ከአገር ውስጥ ግን ተሸሽገዋል የሚባሉትን ስለምን መያዝ አዳጋች ሆነ? በዚህ መንገድስ የህዝብ አመኔታ ማግኘት ይቻላል ወይ? ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አለማድረግስ የችግሩን ዕድሜ አያራዝመውም ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ከምክር ቤቱ የሕግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና አባላት ተነስተዋል፡፡              በተመሳሳይ ክልሎች በወንጀል ተጠይቆ ይፈለጋል የተባለ የለም በሚል ካለም አሳልፈው እንደሚሰጡ ሲናገሩ ይሰማል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተጠርጣሪዎችን የደበቁ እንዳሉ ይገልፃልና ይህ እንዴት ይታያል? ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተደበቁ ተጠርጣሪዎች በሌሉበት የሚታይበት አግባብ ላይ እንዲሁም የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት  ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ  ምክትል ለሕግ ቀርበው ጉዳያቸው ሲታይ ግብረአበራቸው በሚል ስማቸው ይነሳልና ያለመከሰስ መብት አላቸው ወይ?፣ ምንም እንኳ በአገሪቱ በነበረው የአመራር ሂደት ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጣ ቢሆንም ተጠርጣሪዎችን የመያዙ ጉዳይ ግን ብሔር ተኮር እንደሆነ ይነሳልና ከዚህ አንፃር በእኩል ደረጃ ተጠያቂ ማድረግ ጋር ተያይዞ ምን እየተሠራ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ከምክር ቤቱ አባላት ተነስተዋል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ  ጥያቄዎቹ ትክክለኛና ተገቢ እንደሆኑ በመግለጽ፤ መንግሥት ሕግን መሠረት አድርጎ ተጠያቂ የማድረግ ተግባሩን እያከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከተሸሸጉ ተጠርጣሪዎች ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሻቸውን ሲሰጡም አንዳንዶቹ  ቦታቸውን በመለዋወጥ፣ የተወሰኑት ደግሞ ያሉበት የማይታወቅ ሲሆን፤ ከአገር ውጭ ያሉትን ግን በመነጋገር ወደ አገር እንዲመጡ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር ተያይዞ ያለመከሰስ መብት አላቸው በሚል ለተነሳው ጥያቄ ግለሰቡ የፌዴራልም ሆነ የክልል ምክር ቤት አባል አለመሆናቸውን በመግለጽ ያለ መከሰስ መብት የሌላቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የተሸሸጉትም በክልሉ ውስጥ ቢሆንም እርሳቸውን ለመያዝ ግን በተኩስ መሆን አለበት ብሎ መንግሥት አያምንም ብለዋል፡፡ ክልሎች ወንጀለኛ ተብሎ የተጠየቁት እንደሌለና አሳልፈው እንደሚሰጡ የሚያነሱትም ትክክል አይደለም፡፡ ይልቁንም በደብዳቤ ጭምር የተጠየቀ በመሆኑ ይህን መሠል ምላሽ የሚሰጠው ‹‹አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም›› ሆኖ ነው ሲሉ ድርጊቱ ሆነ ተብሎ እየተፈፀመ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከብሔር ተኮር ተጠያቂነት ጋር ተያይዞ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፤ በከፍተኛ አመራር ቦታዎች ላይ አብላጫውን ቦታ ይዞ የነበረ ብሔር ተጠያቂ ሲደረግ ሊያዝ ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህን ለማሟያ በሚል ሌሎችን የማካተት ሥራ አይሠራም፡፡ ተጠያቂነቱ ወንጀል ተፈጽሟል አልተፈፀመም? የሚለውን እንጂ በፖለቲካ አቋምና በብሔር አለመሆኑንም ነው  የገለጹት፡፡ በመሆኑም በሁሉም ክልሎች ወንጀለኞችን የሚሸሽጉ አካላትን አጋልጦ ለሕግ እንዲቀርቡ የማድረግ ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ፣ የፖለቲካ አመራርና የምክር ቤቱም ነው ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አዲስ ዘመን ታህሳስ 24/20111

]]>
ዓረና የህወሓት ተቃዋሚ ነው ፤ ደጋፊ አይደለም ። http://konjoethiopia.com/2019/01/01/%e1%8b%93%e1%88%a8%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8b%88%e1%88%93%e1%89%b5-%e1%89%b0%e1%89%83%e1%8b%8b%e1%88%9a-%e1%8a%90%e1%8b%8d-%e1%8d%a4-%e1%8b%b0%e1%8c%8b%e1%8d%8a-%e1%8a%a0%e1%8b%ad%e1%8b%b0/ Tue, 01 Jan 2019 14:04:07 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1241 ከህወሓት ድጋፍ አንጠብቅም! ================= ዓረና የህወሓት ተቃዋሚ ነው፤ ደጋፊ አይደለም። የህወሓት ደጋፊዎችና ተላላኪዎች ህወሓትን አትንኩብን እያሉ ነው። ልክ ናቸው። ምክንያቱም ህወሓት ከተነካች ትጋለጣለች። ከተጋለጠች ከስልጣን ትወርዳለች። ከስልጣን ከወረደች ጥቅማቸው ይነካል። ጭቁን የትግራይ ህዝብ ነፃ ይወጣል፣ በእኩል ዓይን ይታያል። ሰዎች በብቃታቸው ይመዘናሉ፣ ስራ ያገኛሉ። የተዘረፈው ገንዘብ ለህዝብ ይከፋፈላል። ህዝብ ይጠቀማል። ትግራይ የህዝቧ እንጂ የህወሓት ተላላኪዎች የግል […]]]>

ከህወሓት ድጋፍ አንጠብቅም!
=================

ዓረና የህወሓት ተቃዋሚ ነው፤ ደጋፊ አይደለም። የህወሓት ደጋፊዎችና ተላላኪዎች ህወሓትን አትንኩብን እያሉ ነው። ልክ ናቸው። ምክንያቱም ህወሓት ከተነካች ትጋለጣለች። ከተጋለጠች ከስልጣን ትወርዳለች። ከስልጣን ከወረደች ጥቅማቸው ይነካል። ጭቁን የትግራይ ህዝብ ነፃ ይወጣል፣ በእኩል ዓይን ይታያል። ሰዎች በብቃታቸው ይመዘናሉ፣ ስራ ያገኛሉ። የተዘረፈው ገንዘብ ለህዝብ ይከፋፈላል። ህዝብ ይጠቀማል። ትግራይ የህዝቧ እንጂ የህወሓት ተላላኪዎች የግል ንብረት አትሆንም። እናም ይጎዳሉ (ከህዝብ ጋር እኩል ይሆናሉ) ለብቻ መብላት አይኖርም።

ስለዚህ ህወሓትን ስንተች ቢንገበገቡ አይገርምም፤ የጥቅም ጉዳይ ነውና። ዓረና የህወሓት ተቃዋሚ እንደመሆኑ መጠን የህወሓት ደጋፊዎች እንዲደግፉን አንጠብቅም። ስለዚህ ቢቃወሙን አይደንቀንም። ከቁብም አንቆጥረውም። (ህወሓት ስትነካ የሚያንገበግበው ሰው የህወሓት ደጋፊና ተጠቃሚ እንጂ ሌላ ማን ሊሆን ይችላል? ያልሆነማ የተለያዩ አማራጭ ሐሳቦች ማየት አለበት)። የህወሓት ሰዎች ሲቃወሙን ልክ ናቸው። የጥቅም ጉዳይ ነውና።

ግን አንድ ነገር ተሳስተዋል። ዓረና የህወሓት ደጋፊ እንዲሆን ይፈልጋሉ። ሊሆን አይችልም። ዓረና ከህወሓት የተለየ ዓላማ ያለው ድርጅት ነው። ህወሓቶች ለውጥ አይፈልጉም፤ ዓረና ለውጥ ለማምጣት ነው ሚታገለው። ስለዚህ የተለያየን ነን። ለውጥ ከመጣ እንደግፋለን። ለለውጥ እየታገልን ለውጥን አንቃወምምና! የኛ ጉዳይ ለውጡ ህዝብ ሚጎዳ ሳይሆን ሚጠቅም መሆን አለበት ነው።

ለውጥ ለማምጣት ትግል የጀመርነው ከ10 ዓመት በፊት ጀምሮ ነው (የወራት ዕቅድ አይደለም)። ዴሞክራሲ ሰፍኖ ህዝባዊ መንግስት እስኪመሰረት ድረስም ይቀጥላል።

አሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ ባጠቃላይ ለትግራይ ህዝብ ደግሞ በተለይ የሚጠቅም አማራጭ ሐሳብ ስናቀርብ የስድብ ዘመቻ ያካሂዳሉ። ህወሓትን አትንኩብን ይላሉ። ህወሓትን የተቃወመ የጠቅላይ ሚኒስተር ዶር ዐብይ አሕመድ ተላላኪ በማለት ለማጥላላት ይሞክራሉ (ዶር ዐቢይ ግን የዓረና አባል ሆነንዴ?!)። “ወደኛ ተቀላቀልና ሌሎችን ሁሉ በመሳደብ የተጋሩን ደሕንነትና ጥቅም እናስከብር” ይሉሃል። ሌሎችን በመሳደብ የተጋሩን ጥቅምና ደሕንነት የሚከበር ይመስላቸዋል። ህወሓት ያልደገፈ ትግራዋይ እንዳልሆነ ይሰብካሉ፤ ትግራዋይነት የሚታደለው እንደ ፓርቲ መታወቅያ በህወሓት ይመስል!

አሁን ህወሓቶችን በሚተቹ አክቲቪስቶች ላይ የስድብ መዓት በማውረድ የማጥላላት ዘመቻ እንዲከፍቱ መመርያ ተሰጥቶዋቸዋል (መደብ ወርዶላቸዋል)። የስድብ ጦርነት ከፍተዋል። ዋና አዛዥ የህወሓቱ ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ሲሆን በደሕንነት፣ በኮሙኒኬሽን ቢሮ እና በክልሉ ሚድያ ተቋማት አስተባባሪነት በተለየ በሚከፈላቸው አክቪስቶች ነን ባዮች የሚከናወን ነው፤ የማይከፈላቸው ግን በህወሓት “የተከበናል” (የፀጥታ ችግር) ፕሮፖጋንዳ የተሸወዱም አሉ። የፀጥታ ችግር ቢያጋጥም እንኳ በህወሓት መሪነት ሊፈታ እንደማይችል ያልተገነዘቡ አሉ።

ከነዚህ ቅልብተኛ አክቲቪስት ነን ባዮች አንዱ በክልሉ ቴለቪዥን ጣብያ ቀርቦ “እነዚህ ፀረ ህወሓት አክቲቪስቶች ከፌስቡክ ወደ ትዊተር አባረናቸዋል” ብሏል (በመንጋ ስድብ መሆኑ ነው)። ዓላማቸው የስድብ ዘመቻ በመክፈት ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ደጋፊ የለንም ብለው እንዲሸማቀቁ፣ ስድብ ፈርተው ህወሓትን ከመተቸት እንዲቆጠቡና ህወሓት መልሳ እንድታገግም ዕድል ለመስጠት ነው።

አሁን ስለ ህወሓት ጥሩ ነገር ብፅፍ ራሱ መሳደባቸው አያቆሙም። ምክንያቱም መደብ (መመርያ) ተሰጥቷቸዋል። ዝም ብለው ስድብ ይፅፋሉ። እንደ ፓሮት የተነገራቸውን ይደግማሉ። ከነዚህ ተከፋይ ተሳዳቢዎች በቅርቡ በትእምት ስፖንሰርነት “አንዳንድ ነገሮች” እንዲጎበኙ ተጋብዘው ነበር። ከተጋበዙት አብዛኞቹ ብዙ የፌስቡክ አካውንቶች ከፍተው እንዲሳደቡ የሚከፈላቸው ናቸው።

ዓረና ግን እንኳን በስድብ በጠመንጃም አይሸማቀቅም፤ ዓላማ ነዋ። ከህወሓትም ድጋፍ አይጠብቅም። በትግራይም ለውጥ እንፈልጋለን። ሊያስተዳድረን የሚገባ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ነው። ህወሓት የህዝብ ድጋፍ አለኝ ብሎ የሚያምን ከሆነ አማራጭ ሐሳብ ለምን ይፈራል?

ይህን የትእምት ገንዘብ ለቅልብተኛ ተሳዳቢዎች ከሚከፈል ዩኒቨርስቲ ተመርቀው ስራ ያላገኙ ግን ብዙ ማምረት የሚችሉ ወጣቶች ስራ የሚጀምሩበት ዕድል ለምን አይከፈትላቸውም? ያመርታሉኮ! መሳደብ ግን ምርት የለውም! እናም የትእምት ገንዘብ ለተሳዳቢዎች ከሚሰጥ ለአምራች ወጣቶች ቢውል ውጤታማ ይሆናል።

አትድከሙ! ከህወሓት ተላላኪዎች ድጋፍ አንጠብቅም፤ የራሳችን ለውጥ ፈላጊ ወጣት ደጋፊዎች አሉን። የህወሓት ደጋፊም አንሆንም፤ የምንደግፈው የራሳችን ድርጅት አለን። የዓረና ማሕበራዊ መሰረት (Social Base) የህወሓት አባል ወይ ደጋፊ አይደለም። ለዚህም የትግራይን ህዝብ እንጂ ህወሓቶችን ለማስደሰት አንሰራም። ከድርጅት ህዝብ ይቀድማል!

ዴሞክራሲ ያሸንፋል!

It is so!!!

]]>
“ለረዥም ጊዜ ፖለቲካ ውስጥ የመቆየት ፍላጎት የለኝም” ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ http://konjoethiopia.com/2018/12/27/%e1%88%88%e1%88%a8%e1%8b%a5%e1%88%9d-%e1%8c%8a%e1%8b%9c-%e1%8d%96%e1%88%88%e1%89%b2%e1%8a%ab-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%89%86%e1%8b%a8%e1%89%b5-%e1%8d%8d%e1%88%8b%e1%8c%8e/ Thu, 27 Dec 2018 15:29:39 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1236 የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የሆኑትና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋን በጽህፈት ቤታቸው አግኝተናቸው በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርገናል። ቢቢሲ አማርኛ፡ አንዳርጋቸው ታፍኖ መወሰዱን ባወቅክባት ቅፅበት ምን ተሰማህ? ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ፡ አንዳርጋቸው የተያዘ ጊዜ ኒው ዮርክ ነበርኩ። እንደተያዘ እዚያው የመን እያለ ነው የሰማሁት፤ በተያዘ በግማሽ ወይንም በአንድ ሰዓት አብረው ሲበሩ ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ነው […]]]>
ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ

የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የሆኑትና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋን በጽህፈት ቤታቸው አግኝተናቸው በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርገናል።

ቢቢሲ አማርኛ፡ አንዳርጋቸው ታፍኖ መወሰዱን ባወቅክባት ቅፅበት ምን ተሰማህ?

ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ፡ አንዳርጋቸው የተያዘ ጊዜ ኒው ዮርክ ነበርኩ። እንደተያዘ እዚያው የመን እያለ ነው የሰማሁት፤ በተያዘ በግማሽ ወይንም በአንድ ሰዓት አብረው ሲበሩ ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ነው የሰማሁት። እዚያ ያሉ እኛን የሚያውቁ ሰዎች እንደዚህ አይነት ነገር አለ ተከታተሉ ብለው የነገሩን ያኔ ነው።

በዚያ በኩል እንደሚሄድም አላውቅም ነበር፤ በሌላ በኩል እንደሚሄድ ነበር የማውቀው። ያው መጀመሪያ ላይ ትደነግጣለህ። የመጀመሪያ ሥራህ የሚሆነው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄድ ወይንም ችግር እንዳይደርስበት ማድረግ የሚቻለውን ለማድረግ ለተለያዩ መንግሥታት፣ አቅም ላላቸው ሰዎች፣ መንገርና አንድ ነገር እንዲያደርጉ መሞከር ነበር።

ቢቢሲ አማርኛ፡ እርሱ እስር ቤት በነበረበት ወቅት እርሱን በተመለከተ ምን አይነት ስሜቶችን አስተናገድክ?

ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ፡ ከአንዳርጋቸው ጋር ለረዥም ጊዜ ነው የምንተዋወቀው። ብዙ አውርተናል። ምን እንደሚፈልግ አውቃለሁ። እኔም ምን እንደምፈልግ ያውቃል። ሲታሰር የተወሰነ የድርጀቱን ሥራ ኃላፊነት እርሱ ስለነበር የወሰደው ኢትዮጵያ መምጣቱን ካወቅሁ ጊዜ ጀምሮ ለእኔ ግልፅ የሆነልኝ በምንም አይነት እንደማይፈቱት፣ እንደማይገድሉትም አውቅ ነበር።

ጥያቄው ያለው እንዴት ታግለን ቶሎ ይህንን ነገር እናሳጥራለን የሚል ነው። ከዛ በኋላ ብዙ ጊዜ አልፈጀብኝም ሥራዬን ሁሉ ትቼ እርሱ የጀመራቸውን ሥራዎች ወደ መቀጠል ነው የገባሁት። በእንዲህ አይነት የትግል ወቅት አንዳርጋቸው ሲታሰር ምን ይፈልጋል? ማንም ሰው ቢለኝ፤ የታገለለትን አላማ ከዳር እንድናደርስለት ነው እንጂ የሚፈልገው ሌላ ለግሉ እንዲህ አይነት ነገር ይደርስብኛል የሚል የስሜት ስብራት ውስጥ እንደማይገባ አውቅ ስለነበር፤ ያለኝን ጠቅላለ ጉልበቴን ያዋልኩት እንዴት አድርገን ይህንን ትግል በቶሎ ገፍተን እርሱንና በየቦታው የሚታሰሩትን ጓዶቻችንን ነፃ እናወጣለን ወደ ሚለው ነው።

ከዚያ ባሻገር ግን የታገልንለትን አላማ፣ ኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ የማድረግ አላማ፣ ከዳር እንዴት እናደርሳለን የሚለው ነው፤ ከዚያ ውጪ ሌላ አልነበረም። ከመጀመሪያው አንድ ቀን ሁለት ቀን ውጪ ጠንካራ የሆነ የስሜት መዋዠቅ ውስጥ መግባት አይገባም ብዬ ነው ለራሴ የነገርኩት።

አሁን ሥራው ይህንን ነገር ከዳር ማድረስ ነው። በእንዲህ አይነት ትግል ውስጥ ችግሮች ይፈጠራሉ፤ ግን እያንዳንዱ ችግር ላይ ከፍተኛ የሆነ የስሜት መዋዠቅ ካስቀመጥክ ሥራ አትሰራም። ሁሉን ነገር ዘግቼ ይህንን ነገር እንዴት ከዳር እናደረሳለን የሚለው ላይ ነው ጊዜዬን ያጠፋሁት።

ቢቢሲ አማርኛ፡ አሁን ያለው ለውጥ የሚሾፈረው በኢህአዴግ መሆኑ ምን አይነት ስሜት ነው የሚፈጥረው?

ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ- አንዱ ትልቁ ጥያቄ ኢህአዴግን የምናየው የድሮው ኢህአዴግና የአሁኑ ኢህአዴግ አንድ ነው፤ ወይንስ ቢያንስ ያንን ለውጥ ካመጡ ሰዎች በኋላ በመሰረታዊ መልኩ ለውጥ አድርጓል የሚለውን መመለስ አለብህ።

የትግል ለውጥ ስትራቴጂ ለውጥ ስናደርግ የወሰንነው ይህንን ለውጥ ለማምጣት የመጡት ሰዎችን፤ በእንዲህ አይነት የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ስትሆን አንዱ ሥራህ የመንግሥት ስልጣንን በያዘው ኃይል ውስጥ ያለውን ነገር ማጥናት ነው።

ስለዚህ በኢህአዴግ ውስጥ የሚደረጉትን ለውጦች እንከታተል ነበር፤ እና አንዱ ትልቁ ጥያቄ የነበረው እነ ዐቢይ ሲመጡ ኢህአዴግን በአዲስ መልኩ ለማስቀጠል የመጡ ሰዎች ናቸው ወይንስ እውነተኛ ለውጥ ፈልገው የመጡ ናቸው የሚለውን መመለስ ነበር። እነዚህ ሰዎች ዝም ብሎ በፊት የወያኔ ሥርዓት ይከተል የነበረውን ነገር ለማስቀጠል የሚያስቡ ሰዎች እንዳልሆኑ ስንረዳ ብዙ ጊዜ አልወሰደብንም።

ምክንያቱም በከፊል የመጡትም በህዝብ ትግል ነው። ሀያ ምናምን ዓመት ያልተቋረጠ ትግል ሲካሄድበት የነበረው ከዛም ሦስት ዓመት ደግሞ ያላቋረጠና የተጋጋለ ሰፊ የህዝብ ትግል ሲካሄድበት የነበረው ነው። ኢህአዴግ በነበረበት ሊቀጥል እንደማይችል ግልፅ የሆነበት ጊዜ ነው። በዚያን ጊዜ የመጡት እነዚህ ሰዎች ኢህአዴግን ሸውደን ሌላ አዲስ መልክ አምጥተን እናስቀጥል ብለው የሚያምኑ ሳይሆኑ በርግጥም የበፊቱ ሥርዓት ተሸንፎ የመጡ ናቸው።

ይህንን አንዴ ከወሰንክ በኋላ፣ ተጋግዘህ ያንን ሥርዓት ለማቆም ትሞክራለህ እንጂ በፊት የነበሩት ሰዎች እንዲህ ነበሩና በመሳሪያ ልቀጥል የምትለው ነገር አይደለም። እኛ በምንም አይነት፣ መቼም ቢሆን የመሳሪያ ትግልን እንደጥሩ ነገር አድርገን ገብተንበት አናውቅም። ምርጫ አጥተን የገባንበት ነው። ያን አላስፈላጊ የሚያደርግ ነገር ሲፈጠር ደቂቃም አልፈጀብንም። ተመልሰን ወደ እውተኛ ሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ ወደ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ መንገድ መሄድ የተሻለ ነው ብለን ነው የገባንበት።

በኢህአዴግ ውስጥ ወጥ ነው ማለት ባይቻልም ለውጡን ይዘው የመጡት ኃይሎች በርግጥም ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚፈልጉ መሆናቸውን እናምናለን። ያንን ሥርዓት ለማምጣት ከእነርሱ ጋር አብረን እንሰራለን፤ ከዚያ በኋላ ኢህአዴግ ካሸነፈ፤ እኛ እኮ በፊትም ኢህአዴግ ለምን አሸነፈ አይደለም፤ የሕዝብ ፍላጎት የህዝብ ፈቃድ አግኝቶ ያሸንፍ ነው የምንለው።

ማንም የህዝብ ፍቃድ አግኝቶ ያሸንፍ የህዝብ መብት ይከበር፣ ሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ። የህግ ልዕልና ይኑር። እነኚህ ናቸው ጥያቄዎቹ። ማን ስልጣን ያዘ አይደለም። ዋናው ጥያቄ በምን መልክ ስልጣን ይያዛል? የህዝብ ፈቃድ አግኝቶ ነወይ? ህዝብ በፈለገ ጊዜ ሊያወርደው የሚችል ነወይ? ከዛ በተጨማሪ ደግሞ እውነተኛ ነፃ የሆኑ ተቋማት አሉ ወይ? ፍርድ ቤቱ በነፃነት ይሰራል ወይ? ጦር ኃይሉ በርግጥም ህብረተሰቡን የሚጠብቅ ነው ወይስ የአንድ ፓርቲ መሳሪያ? የምርጫ ተቋሞቹ እርግጥም ነፃና የህዝብ ፍላጎት የሚንፀባረቅባቸው ምርጫዎች ለማድረግ ፈቃደኞች ናቸው? እነዚህ ናቸው ጥያቄዎቹ። ያንን ለማድረግ ፍላጎት ያለው አካል እስከመጣ ድረስ እኛ ምንም ችግር የለብንም።

ቢቢሲ አማርኛ፦ ሥርዓቱን ሰው ባይጥለው ኢኮኖሚ ይጥለዋል ትል ነበር። አሁን ያለውንስ መንግት?

ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ፡ ይኼ አዲሱ የለውጥ ኃይል ከነበረው የወጣ ነው ብለህ ብታስብ፣ ፕሮፓጋንዳውን ምናምኑን ትተህ የተረከበው ኢኮኖሚ ደንበኛ የዝርፊያ ሥርዓት የሽፍታ ኢኮኖሚ ሥርዓት ነበር። ዝም ብለህ ያገኘኸውን ዘርፈህ የምትሄድበት። የነበሩትን ፕሮጀክቶች ይካሄዱ የነበሩትን እንዳለ ብታይ ከዝርፊያ ጋር የተያያዙ ናቸው።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ምናምን ብለህ አንድ ጤነኛ ሰውና ስለከተማ ትራንስፖርት የሚያውቅ ሰው እንዲህ አይነት የከተማ ትራንስፖርት፣ በዚህን ያህል ወጪ አውጥቶ አይተክልም ነበር። በጣም ቀላል የሆኑ፣ በቀላሉ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግሮች የሚፈቱ፣ እንደዚህ ከተማዋን ለሁለት ከፍለህ አስቀያሚ ሳታደርገው ልትፈታ የምትችልባቸው መንገዶች ነበሩ።

ፕሮጀክቶቹ በአንድ መልኩ ወይም በሌላ ለመስረቂያ ተብለው የተዘረጉ ናቸው። ለዚህ ነው ማለቅ ያልቻሉት። ለዚህ ነው ከአስር ከሃያ እጥፍ በላይ ወጪ የሚያስወጡት። እነኚህ ሁሉ የሆኑት ደግሞ በሕዝብ ስም በሚገኝ ብድር ነው። ይህ ሁሉ ብድር ሀገሪቱ ላይ ተከምሮ ወደ ሰላሳ ቢሊየን ዶላር ብድር ያለባት ሀገር ነች።

ይህ የሆነው ያ ሁሉ ብድር ከተሰረዘ በኋላ፣ በተለይ ከምርጫ 97 በኋላ የመጣ ይህንን የዘረፋ ሥርዓት ለማቆየት የተዘረጋ ሥርዓት ነው። ይኼ ነገር መጥቶ መጥቶ በተወሰነ ደረጃ ኢኮኖሚውን ዝም ብሎ ያራግበዋል። ምክንያቱም ዝም ብሎ ገንዘብ ኢኮኖሚ ውስጥ ስላለ። በኋላ ላይ ግን ተንገራግጮ መቆሙና ችግር ውስጥ መጣሉ የማይቀር ነው። እና በዚህ ምክንያት ይህንን ሥርዓት የተረከቡት ሰዎች በጣም ከባድ የሆነ ችግር ይገጥማቸዋል። አንደኛው እዳውን መክፈሉ፤ ሁለተኛ በአጠቃላይ የንግድ ሥራን በሚመለከት ያለው ባህል ተበላሽቷል። ሁሉም በስርቆት በማጭበርበር በምናምን አገኛለሁ ብሎ የሚያስብ የኢኮኖሚ ክላስ ነው የተፈጠረው።

ሀብታም የሚባሉትን፣ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር ሚሊየነር ሆኑ የሚባሉትን፣ አይነት ግለሰቦችን ብታይ ቁጭ ብለው አስበው ምን ያዋጣል ለህብረተሰቡ የተሻለ እቃ እንዴት እናቅርብ በማለት አይደለም። ወይ መሬት ዘርፈው፣ ወይ ከባንክ ገንዘብ ተበድረው ያገኙት ነው። በዚያ አይነት መሰረት ላይ የቆመ ኢኮኖሚ ሁል ጊዜ ችግር ይገጥመዋል። ይህንን ሁሉ መቀየር በማክሮ ኢኮኖሚ ደረጃ ያሉብህን ችግሮች መፍታት ብቻ ሳይሆን የንግድ አመለካከቱን ባህሉን ራሱ መቀየር በጣም ሰፊ ሥራ የሚጠይቅ ነገር ነው።

ይህንን ለማስተካከል ግን በመጀመሪያ የፖለቲካው ሥርዓቱ መስተካከል አለበት። ከዚያም ባሻገር ግን ሰላምና መረጋጋቱ ወዲያውኑ መምጣት አለበት። ይህንን የፖለቲካ ነገር ሳታስተካክል የኢኮኖሚውን ነገር ማስተካከል ከባድ ነው። ለዚህ ነው ቅድሚያ የፖለቲካ ማስተካከያዎች መወሰድ ያለባቸው እንጂ፤ ቶሎ ብሎ የእነዚህን የኢኮኖሚ ችግሮች አንድ በአንድ መመልከት ግዴታ ነው። መንግሥትም ይኼን ይገነዘባል ብዬ አስባለሁ። የለውጥ ኃይልም ስለሆነ ከሌሎችም ሀገሮች በተወሰነ መልኩ እዳውን ለመቀነስ ትብብር ያገኛል ብዬ አስባለሁ። ምንም እንኳ ፖለቲካውን የመፍታት እርምጃ መውሰድ ቀዳሚ ቢሆንም የኢኮኖሚውንም ችግር ለመፍታት በአንድ ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።

ቢቢሲ አማርኛ-አንዳንድ የተወረሱብህን ንብረቶች ለማስመለስ ሞክረሃል?

ፕሮፌ. ብርሃኑ፡ እስካሁን አልተመለሱም። ይኼ ለውጥ ስለእኔ አይደለም። 100 ሚሊየን ህዝብ የሚበላው ያጣ ያለበት ሀገር አሁን የእኔን ንብረት መለሱ አትመለሱ በጣም ትልቅ

ፕሮፌ. ብርሃኑ፡ የደህንነት፣ ሰላም የማረጋጋት፣ ባለፈው27 ዓመት የተፈጠረው የክልል አደረጃጀት። የክልል አደረጃጀቱ ደግሞ ዝም ብሎ በዘር ላይ፣ በደም ቆጠራ ላይ መመስረቱ ብቻ አይደለም። በዚያ ላይ የተመሰረተው አከላለል የራሱ ጦር ያለው አገር ነው። አሁን እነዚህ ክልሎች የምትላቸው የራሳቸው ሀያ ሺህ፣ ሰላሳ ሺህ. . . ጦር አላቸው የሚባል ነው።

በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም። በአንድ ሀገር እንደዚህ አይነት ኃይል ሊኖር የሚገባው የመንግሥት መከላከያ ነው። ለሁሉም እኩል የሆነ፣ ሁሉንም በጋራ የሚያገለግል፣ የሁላችንንም ደህንነት የሚጠብቅ ኃይል። አሁን ግን በሁሉም ክልሎች ያሉ ኃይሎች አሉ።

እነዚህን ሁሉ እንዴት አድርጎ በአንድ ሀገራዊ የመከላከያ እዝ ስር ታደርጋቸዋለህ? በየአካባቢው ከብሔር ጋር በተያያዘ የተነሱ ግጭቶችን እንዴት ታስቆማቸዋለህ? እንደ አገር ወይ ከዚህ ችግር ወጥተን እንበለፅጋለን። ወይ እንደሃገር እንፈርሳለን። የተወሰነ ቡድን አልፎለት፣ ሌላው የማያልፍለት አገር ሊኖረን አይችልም።

ሁላችንም ተሰባስበን የምንኖርባት፣ የሁላችንም መብት የተከበረባት፣ የሁላችንም ባህል የሚከበርባት፣ የሁሉም ቋንቋ የሚከበርባት የተረጋጋች ሀገር መፍጠር በጣም ከባዱ ከእነ ዶ/ር አብይ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ይሄንን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባት ሂደት ላይ የሚገጥመን ችግር ነው።

ነገር ግን በደንብ መነጋገር ከቻልን በማስፈራራት ሳይሆን ቁጭ ብለው እየተነጋገሩ ህብረተሰቡ ያሉትን አማራጮች እየሰማ የምንነጋገርበት አይነት የፖለቲካ ምህዳር መፍጠር ከቻልን፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በምን አይነት የፖለቲካ ሂደት ፖለቲካቸውን እንደሚያስተዋውቁ በደንብ ከተስማሙና ሁሉም ለዚያ ታማኝ ከሆኑ የምንወጣው ችግር ነው። የሚያቅተን አይደለም። አሁን ብዙ ችግር ያለ ይመስላል። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች ማስተካከል ከቻልን ወደዚያ እንሄዳለን። ግን ትልቁ ተግዳሮት አሁን ያለው ግን ይኼ ነው። ፖለቲካውን ማረጋጋት፣ ፖለቲካውን ወደ ሰለጠነ ፖለቲካ መውሰድ ትልቁ ተግዳሮት ነው የሚመስለኝ።

ቢቢሲ አማርኛ፦ አሁን ያለው የሀገሪቷ ነባራዊ ሁኔታ አንተ ስትሄድ ከነበረው በበለጠ የብሔርተኝነት ስሜት ናኝቶ በኦሮሚያና በአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ተቃውሞ ሲገጥማችሁ እያየን ነው። እንዲህ ባለው ሁኔታ የድጋፍ መሰረታችን የት ነው የምትሉት?

ፕሮፌ. ብርሃኑ፦ ሁለት ነገር ማንሳት እፈልጋለሁ። አንደኛ ለእኛ የሚያሳስበን ነገር ምን ያህል የፖለቲካ ድጋፍ የት እናገኛለን የሚለው አይደለም። ትልቁ የሚያሳስበው ጥያቄ ይህችን አገር እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ማድረግ ላይ ነው። ትልቁ ጉልበታችንን የምናፈስበት ጉዳይ እሱ ነው። ሁለተኛ አንድ ነገር እውነታ ሆኗል ማለት አይቀየርም ማለት አይደለም። ኢትዮጵያ እኮ ደሃ ሀገር ነች። ይሄ እውነታ ሁሌም ደሃ አገር ያደርጋታል ማለት አይደለም።

የተለያዩ ፖሊሲዎችንም ያረቀቅነው ይህንን እውነታ ለመቀየር ነው። የኢትዮጵያም የፖለቲካ እውነታ በአብዛኛው ለ27 ዓመት ይሰማው የነበረ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ብሔር ብሔረሰቦች ስሜት ውስጥ ገብተዋል ከሆነ አንደኛ ቁጥሩ ላይ መስማማት አንችልም። ምክንያቱም በተጨባጭ የምናውቀው ነገር የለም። ምን ያህሉ ሰው በዜግነት ፖለቲካ ያምናል? ምን ያህሉስ በብሔር? የሚለው ሁኔታ ላይ በተጨባጭ የተሰራም ሆነ የተሰበሰበ ጥናት የለም።

በአብዛኛው ልኂቅ በብሔር ፖለቲካ ውስጥ እንደተዘፈቀ ግልፅ ነው። ህብረተሰቡ ገብቷል ወይ? የሚለው አጠራጣሪ ነው። ሁለተኛ ብዙ ሰው ዘንግቶታል እንጂ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ኢትዮጵያ ማህበረሰቧ የተደባለቀ ነው። ንፁህና ያልተቀላቀለ ማህበረሰብ ለማግኘት አዳጋች ነው። ሦስትና አራት ትውልድ ብንቆጥር ሁላችንም ከተለያየ ብሔር ጋር የተደባለቅን ነን። እሱ ቀርቶ በአንድ ትውልድ እንኳን አባት አንድ ብሔር እናት ሌላ ብሔር ሆና የተወለደው በትክክለኛ መንገድ ቢቆጠር ከማንኛውም ከአንድ ብሔር ነኝ ከሚለው የሚበልጥ ይመስለኛል።

ይሄ ሁሉ ከዚህ የብሔር ፖለቲካና ከመጣው ግጭት መውጣት የሚፈልግ የማህበረሰብ አካል ነው። እኛ የምንለው አንደኛ እነዚህ ሃሳቦች በነፃነት የሚገለፁበት፣ ህብረተሰቡ ከስሜት ወጥቶ ለአገራችን፣ ለህዝባችን፣ ለራሳችን የሚጠቅመን የቱ ነው ብሎ በደንብ ማሰብ በሚጀምርበት ጊዜ እነኚህ ነገሮች ይቀየራሉ። የፖለቲካ ስሜት የማይቀየር በድንጋይ ላይ የታተመ ነገር አይደለም። ሁልጊዜም ይቀያየራል።

ከአርባ አመት በፊት ሁላችንም ሶሻሊስቶች ነበርን። የሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለም በተግባር ሲታይ ምን እንደሆነ ካየ በኋላ ነው ሰው ሁሉ የሚያዋጣ አለመሆኑን ተረድቶ የተቀለበሰው።

ከ27 ዓመት በፊት ይሄ የዘር ፖለቲካ ሲመጣ፤ ብሔር ብሔረሰቦች በሰላም የሚኖሩበት ብልፅግና ያለበት ሁሉም እኩል የሚሆንበት ተብሎ ነበር። አሁን ስናየው ግን ሰላምና እኩልነት የሌለበት፣ ብሔርና ብሔረሰቦች ራሳቸውን ማስተዳደር ያልቻሉበት፣ የውሸት እንደሆነ ማህበረሰቡ ተገንዝቦታል።

አሁን እንግዲህ መጪውን ጊዜ ሰው ቁጭ ብሎ ማሰብ የሚጀምርበት ጊዜ ነው። በነፃነት ማሰብ፣ መወያየትና ሃሳቦቹን ለህብረተሰቡ ማቅረብ ከቻልን እኔ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊያን በዜግነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ይመርጣሉ ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ አያስፈራኝም!

ስለዚህ ትልቁ ነገር እኛ እንደ ፓርቲ ምን ያህል ድምፅ እናገኛለን፣ የቱጋ እናሸንፋለን የሚለው አይደለም፤ ጥሩ የፖለቲካ ምህዳር ተፈጥሮ ሁሉም ሃሳቦች በነፃ የሚንሸራሸሩበት፤ በውሸት ስሜት ህብረተሰብን ማነሳሳት የሚቀርበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንፈልጋለን።

ስሜት፣ መገፋፋትና ዘላቂ ጥቅምህን ማወቅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ቀስ ብለው ሰዎች መወያየት ሲጀምሩም ነው ለእኔ፣ ለቤተሰቤ የሚበጀኝ፤ ዘላቂ ጥቅሜ ምንድን ነው? ብለው ማሰብ የሚችሉት። በዚያ ጉዳይ ላይ የዜግነት ፖለቲካ ከምንም ነገር በላይ ለዚች ሀገር ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና መሰረት እንደሆነ ጥያቄ የለንም። ለዚሀም ነው ዛሬ ባይሆን መቼም ወደፊትም የዜግነት ፖለቲካ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የማናስገባው።

ቢቢሲ አማርኛ፡ ኤርትራውስጥ ስትንቀሳቀሱ በነበረበት ወቅት ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር የነበራችሁ ግንኙነት ምንድን ነው?

ፕሮፌ. ብርሃኑ፡ ኤርትራ በነበርንበት ጊዜ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር ጋር ተገናኝተን አናውቅም። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባላት ጋር [ማለትም] ከተራ አባላት ጋር በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ከተለያዩ ሰዎች ጋር እንገናኛለን። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የመጡ ብዙ የኦሮሞ ተወላጅ አባሎች ነበሩን፤ አሉን።

ከብሔር ውጪ የሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ክፍት የሆነ ድርጅት ስለሆነ ከየትም አማራም፣ ትግሬም፣ ኦሮሞም የሚገባበት ድርጅት ነው። ብዙም ችግር ስላልነበረ ብዙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጋዮች የነበሩ አባሎች ነበሩን። እኛም ጋር አባል ሳይሆኑ ኤርትራ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ብዙ የኦሮሞ ወገኖቻችን ጋር በጓደኝነት፣ በወዳጅነት ስንሠራ ነበር።

ከኦነግ ከወጡት ከእነ ከማል ገልቹ፣ ኮለኔል አበበ ጋር ብዙ ጉዳዮች ላይ አብረን እንወያያለን። ለሀገራችን የሚሻለው ምንድን ነው? የሚሉ ነገሮች ላይ እንወያያለን። እንደ ድርጅት ከዚህ በፊት ጀምሮና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም ከሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ጋር አብረን እንሠራ ነበር። ከኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፍሮንት ጋር በጋራ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የሚል ፈጥረን ስንንቀሳቀስ ነበር። ከነከማል ገልቹ ጋርም ተመሳሳይ ነበር።

ስለዚህ ለእኛ ኦሮሞ ሆነ፣ ትግሬ ሆነ፣ አማራ ሆነ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። እንደ ድርጅት የሀገሪቱን አንድነትና ለሁሉም ሕዝቦቿ እኩል የሆነች ሀገር እንድትሆን የሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጋር አብረን እንሰራለን። አሁንም የኦሮሞ ወገኖቻችን ድርጅታችን ውስጥ አባል ናቸው።

አሁን ካለው በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ ጋር ኤርትራ ከገባን ሳይሆን ከሰባት፣ ስምንት ዓመት በፊት እንዴት በጋራ አብሮ እንደሚሠራ ውይይት ነበረን። ከዚያ በኋላ እዛም ውስጥ ችግሮች ነበሩ። እኛ ከበፊትም የነበረን ግልጽ የሆነ አንድ አቋም ነው። ለአገር አንድነት ቅድሚያ መስጠት አለብን። እንደ ሀገር አንድ ካልሆንን በጋራ ፖለቲካ መሥራት አንችልም የሚል አቋም ነው። ከማንኛውም ድርጅት ጋር ስንሠራ የምንለው በኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት ታምናለህ? በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ታምናለህ? ነው። ከዚያ በኋላ ሌላውን ውይይት ማድረግ፤ መደራደርም እንችላለን።

ለመጨረሻ ጊዜ አቶ ዳውድን ያገኘሁት ወደ ኤርትራ ለአንድ ጉዳይ ስመለስ ኤርፖርት ውስጥ ነው። ሰላም እንባባላለን። እዚህም ተገናኝተናል። በፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች ውይይት ውስጥ ገንቢ የሆነ ውይይት እናደርጋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ይቺ አገር የጋራችን ነች። ለሁላችንም የምትሆን ሀገር መፍጠር ነው። የተሻለ ሀሳብ አለን የሚሉ ሀሳባቸውን ለማኅበረሰቡ አቅርበው በዚያ በሚደረግ ውይይት ሕዝብ የመረጠውን መቀበል ግዴታችን ነው።

ሁላችንም መረዳት ያለብን በአንድ ሀገር ውስጥ ሦስት ወይም አራት የታጠቁ ኃይሎች ሊኖሩ አይችሉም። ፖለቲካ እንደዛ ሊሆን አይችልም። በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካችንን እንሠራለን ብለን ካሰብን፤ ሁላችንም መሳሪያ አውርደን እንገባለን ነው ያልነው። ስለዚህ አውርደን በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካው ውስጥ ገብተን ለሀገራችን ይበጃል የምንለውን ለኅብረተሰቡ አቅርበን ሕዝቡ የሚወስነውን መቀበል ነው።

ቢቢሲ አማርኛ፡ ከፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ያገኟቸውስ መቼ ነው?

ፕሮፌ. ብርሀኑ፡ መጨረሻ የተገናኘነው ነሀሴ ላይ ነው። ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት ለመሰነባበት ተገናኝተን በሀገራችን በአካባቢያችን ጉዳዮች ላይ አውርተናል።

ቢቢሲ አማርኛ፡ ምን አይነት ግንኙነት ነበራችሁ?

ፕሮፌ. ብርሀኑ፡ እሳቸው ፕሬዘዳንት ናቸው። እኔ አንድ ታጋይ ነኝ። ስለዚህ ምን ግንኙነት ይኖረናል? አንዳንድ ጊዜ እንገናኛለን። በሀገርና በአካባቢ ጉዳይ እናወራለን። ግን ከእሳቸው በታች ያሉ በእኛ ሥራ ዙሪያ አብረናቸው የምንሠራ ሌሎች ሰዎች አሉ። ፕሬዘዳንቱ ፕሬዘዳንት ናቸው፤ በየጊዜው እየሄድኩ እሳቸውን የማገኝበት ሁኔታ የለም።

ቢቢሲ አማርኛ፡ለወደፊት ጡረታ ወጥተውስ ምናልባት በሲቪል ወይም በቢዝነስ ዘርፍ ሲተፉ ራስዎን ያያሉ?

ፕሮፌ. ብርሀኑ፡ በጣም አያለሁ። የጀመርነው፣ በጣም ብዙ ሰው የሞተበት፣ የተጎዳበት፣ ይቺን ሀገር ዴሞክራሲያዊ የማድረግ ነገር በደንብ መሰረት ከያዘ በኋላ ለረዥም ጊዜ ፖለቲካ ውስጥ የመቆየት ፍላጎት የለኝም። በ94 [በአውሮፓውያኑ] ስመጣም ፖለቲካ ውስጥ ልገባ አልነበረም። አስተምር ነበር። በኢኮኖሚው ዙሪያ እሳተፍ ነበር። ጋዜጦች ላይ እጽፍ ነበር። የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበር ውስጥ እሠራ ነበር። ፖለቲካ የሚባል ነገር ውስጥ ተመልሼ እገባለሁ አላልኩም።

በልጅነቴ ኢሕአፓ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ተመልሼ [ፖለቲካ ውስጥ] እገባለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። በአንድ መልኩ ወይም በሌላ ፖለቲካ ውስጥ መልሶ ያስገባኝ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለተማሪዎች ስለ አካዳሚክ ነጻነት ንግግር ካደረግን በኋላ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር ስንታሰር ነው። እንዲህ አይነት ሥርዓት ካለ፣ ነጻነት ከሌለ፣ በነጻነት መነጋገር ካልተቻለ ሌሎች የሚሠሩ ሥራዎችም የውሸት ይሆናሉ።

አካዳሚሽያን [ትምህርታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ባለሙያ] ነኝ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አስተምራለሁ ብለህ ነጻነት ከሌለህ፣ የምታስተምረውን ነገር በነጻነት ማስተማር ካልቻልክ፤ የምታስተምረው በተወሰነ ደረጃ የውሸት ነው የሚሆነው። የፖለቲካ ሥርዓቱ ለፖለቲካ ስልጣን ሳይሆን ለዕለት ተዕለት ሥራዎች እንኳ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አይደለም።

ባለፈው 27 ዓመት ውስጥ ነጋዴ ብትሆን የሚያሳብድ ነው የሚመስለኝ። ንግድ ማለት የውድድር ቦታ ከሆነ፤ የኢኮኖሚው ሥርዓት ሙሉ በሙሉ በአድልዎ ላይ የተመሰረተ ከሆነ ምንም ልትነግድ አትችልም። አንተንም ከፀባይህ አውጥተው እንደነሱ አጭበርባሪ ሆነህ የምትኖርበት ሁኔታ ነው የሚፈጠረው።

እንደ አንድ እውነተኛ ዜጋ ለመኖር የፖለቲካ ምህዳሩ ነጻነትህን የሚያከብር፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሀሳብህን በነጻነት መግለጽ መቻልህ፣ በምትሠራው ሥራ ጣልቃ የማይገባ መሆኑ አስፈላጊ ነው። ከብዙ ሰዎች ጋር የምለየው በዚህ ነው። እነሱ ይሄ ፖለቲካ ውስጥ መግባት ነው የሚመስላቸው። እኔ ፖለቲካ ውስጥ መግባት አልለውም። ይሄ መሰረታዊ የሆነ ዜግነትህን ማስከበር ነው።

ኢትዮጵያዊ ነኝ ካልኩ እንደ ኢትዮጵያዊ ይገባኛል የምለው መሰረታዊ ነጻነት አለ። ያንን ካላገኘሁ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም። ከዚህ ጠፍቼ፤ ከዚህ ሸሽቼ አሜሪካና አውሮፓ የምኖር ጊዜ ያለኝ ነጻነት ሀገሬ ውስጥ ካለው ነጻነት የበለጠ ከሆነ እውነተኛ ዜጋ አይደለሁም። ፖለቲካ ውስጥ ያስገባኝ ይሄ ነው።

እስር ቤት ከገባን በኋላ በጣም ብዙ ኦሮሞ ወገኖቻችን ታስረው ሳይ ሀገሪቱ ወደ ምን አይነት አደጋ ውስጥ እየገባች እንደሆነ ነው ያየሁት። አሁንም ለእኔ ፖለቲካ ማለት እነዚህን መሰረታዊ የሆኑ የዜግነት መብቶች ማስከበር፤ ሁሉም የሀገሩ ባለቤት የሚሆንበት ድባብ መፍጠር ነው። ይሄ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታችን ነው።

ያንን ማድረግ ካልቻልክ፤ የዜግነት መብትህን እየወረወርክ ነው። ይህንን በፍጹም ማንኛውም ዜጋ ማድረግ የለበትም ብዬ አምናለሁ። ለእኔ ፖለቲካ የሚያያዘው ከዚህ ጋር ነው። ከዚያ በኋላ ያለው ምርጫ ምናምን አድካሚውና በፍጹም የማይረባው የፖለቲካ ክፍል ነው። ዋናው ሥራ ካደረስኩ በኋላ ለጡረታም ደርሻለሁ፤ ትንሽ የማርፍበት ጊዜ ነው።

Source ፡ bbc

]]>