News – news http://konjoethiopia.com Ethiopian news Mon, 11 Feb 2019 16:32:31 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.7.1 96470613 በሶሻል ሚዲያ ውዝግብ ስላስነሳው የቀዳማዊ ሃ/ስላሴን ሃውልት በተመለከተ ቀራፂው መልስ ሰጠ http://konjoethiopia.com/2019/02/11/%e1%89%a0%e1%88%b6%e1%88%bb%e1%88%8d-%e1%88%9a%e1%8b%b2%e1%8b%ab-%e1%8b%8d%e1%8b%9d%e1%8c%8d%e1%89%a5-%e1%88%b5%e1%88%8b%e1%88%b5%e1%8a%90%e1%88%b3%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%89%80%e1%8b%b3%e1%88%9b/ Mon, 11 Feb 2019 16:32:27 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1284 ስለማክበር ሲባል የተፃፈ የፌስ ቡክ ላይ እሰጥ አገባ፡ ባለመፈለግ በሰሞኑ የጃንሆይ ሀውልት ውዝግብ ላይ ዝምታን መርጨ ነበር ። ሆኖም በርካታ፡ብዙሃን መገናኛ አውታሮች እየደወሉ ቃሌን ስላስተጋቡት እንዲሁም አብላጫው ትችት ሰንዛሪ ምንነቱን ባላየውና፡ባላስተዋለው ጉዳይ በቅንነት ድፍረት ብቻ፡ እየተቀባበለ ከግራ፡ቀኝ የሚወራወር መሆኑን ስለተገነዘብኩ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ የሚከተለውን ማስገንዘቢያ ፡ ብፅፍስ ብዬ አሰብኩ ። በመሰረቱ ለአደባባይ ያበቃኸውን ማናቸውንም ቁስ […]]]>

ስለማክበር ሲባል የተፃፈ

የፌስ ቡክ ላይ እሰጥ አገባ፡ ባለመፈለግ በሰሞኑ የጃንሆይ ሀውልት ውዝግብ ላይ ዝምታን መርጨ ነበር ። ሆኖም በርካታ፡ብዙሃን መገናኛ አውታሮች እየደወሉ ቃሌን ስላስተጋቡት እንዲሁም አብላጫው ትችት ሰንዛሪ ምንነቱን ባላየውና፡ባላስተዋለው ጉዳይ በቅንነት ድፍረት ብቻ፡ እየተቀባበለ ከግራ፡ቀኝ የሚወራወር መሆኑን ስለተገነዘብኩ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ የሚከተለውን ማስገንዘቢያ ፡ ብፅፍስ ብዬ አሰብኩ ።
በመሰረቱ ለአደባባይ ያበቃኸውን ማናቸውንም ቁስ ማንም ያገባኛል ባይ ባቅሙና በተረዳበት ደረጃ፡በመሰለው መንገድ የሚሰጠው አስተያየት ሊከበር ይገባል ። በሰሞኑም የሆነው ይኸው ነው። ጃንሆይ ሀውልት አይገባቸውም ከሚለው ፅንፍ ሀውልቱ እርሳቸውን አይመስልም እስከሚለው ድረስ የተባለውን ሰብስበን ለመመዘን ሞከረን ነበር።( ሀውልቱ ስራ፡ ላይ የተሳተፍነው ማለቴ ነው ።) ጃንሆይ ሀውልት አይገባቸውም የሚለው ሩቅ አማራጭ በሀገሩ ላይ የሀሳብ ነፃነት ማመልከቻ ስለሚሆን እንደተከበረ እንደተደመጠ እንለፈው ።ምክንያቱም የአፍሪካ ህብረትና፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከአብላጫው/አሸናፊ ካሉት ሀሳብ ጋር ቆመው መሰራቱን ሰለወሰኑ። የተረፈውንና አስፈላጊ መስሎ የታየንን ሶስት መሰረታዊ ጥያቄ ግን እንደሚከተለው አፍታተነዋል ።

  1. መልኩ ጃንሆይን አይመስልም። ይህ አስተያየት ለደቂቃም ቢሆን ሊያጨቃጭቅ አይገባም ። ሀውልቱ ካልመሰለ እንዲመስል መደረግ አለበት ከመሰለ ደግሞ መስሎ መቀጠል አለበት ። ይህንኑ በማሰብ ምን ጎደለ ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ላይ ሳለን አስተያየቱ ከየትና፡እንዴት እንደተሰነዘረ ሲነገረን ለጥያቄው መልስ በመስጠት መድከሙን አቆምነው። መልኩ አልመሰለም ባዮቹ በጠቅላላ ንጉሱንም ሆነ የተሰራውን ሀውልት ለደቂቃ ባይናቸው አይተው የማያውቁ መሆኑን አረጋገጥን። ታዲያ፡ከየት የመጣ ውርጅብኝ ነው ስንል መነሻው ሁለት አየር ላይ የሚሯሯጡ ፎቶግራፎች መሆናቸው ተነገረን። አንደኛው ፎቶ ስራው ገና፡ የጭቃ ሞዴል ሂደት ላይ ሳለ ከድንገተኛ ጥግ በስርቆሽ የተነሳ የጭቃ ምስል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በምረቃው ቀን ከሃያና ሰላሳ ሜትር ላይ በሞባይል ከርቀት የተነሳ የሰለለ አካል ብቻ የሚያሳይ ሆነው አገኘናቸው። ብቻ ሞተ ሲሉ ተቀበረ ሆነ ነገሩ ። ባጭሩ አሁንም ስለ ሀውልቱ ምንም ዓይነት ትችት መሰንዘር የሚከበር ነገር ሆኖ በተበላሸና ምስሉ በሰለለ ፎቶ ለመዳኘት ከመድፈር በፊት መቸም ጃንሆይ ዛሬ የሉም እንደምንም መጀመሪያ ሀውልቱን ቀርበው ባይናቸው ቢያዩት እላለሁ ። ሀውልትን ባይንና፡በምስል ማየት የሚያጎድለው ብዙ ነገር አለ ።አንዱም ግርማ ሞገስ የሚሉ ሰዎች ከፎቶ ላይ የሚያጡት ነው ። ካልቻሉ ጅምር ስራና፡መናኛ ምስል ላይ ከመመስረት ለምሳሌ ደህና፡ ደህና፡ ፎቶግራፈሮች ያነሱትን መመልከትና፡መተቸት ይመረጣል። ለምሳሌ የቢቢሲውን ድረ ገፅ ለምሳሌ እዚህ ለጥፌዋለሁ።
  2. ለምን በዚህ ልብስ ተቀረፁ ?

ይህ ጥያቄ ከላይኛው የተሻለ ነው ለምን ቢያንስ ታስቦ የተጠየቀ በመሆኑ ። የአፍሪካ፡ህብረትና፡የኢትዮጵያ፡መንግስት ይህንን ሀውልት በአፍሪካ፡ህብረት ግቢ እንዲቆም የተስማሙት ጃንሆይ ከፈፀሙዋቸው አያሌ ገድሎች መካከል አፍሪካን ለማስተባበርና፡አንድ ለማድረግ ለታገሉት ለይቶ ለመዘከር መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ይመስለኛል ።ይህ በተለይ የተሰራበት ዓላማ ጃንሆይን ሌላ ነገር አልሰሩም ለማለት ሳይሆን ለዚህ ለሚቆምበት ቦታ ፡የተመረጠበት የተተኮረበት ገድላቸው ነው ። አፍሪካን ለማስተባበር ወጥተው በወረዱበት ዘመን ሁሉ ጃንሆይ ይለብሱ የነበረው ሁሌም ጥቁር ወይም ግራጫ፡ ሱፍ በክራቫት ብቻ፡ነው። በአፍሪካ ህብረት እንግዳ፡ሲያስተናግዱም ሆነ ሲስተናገዱ አቁዋቁዋማቸውና፡ እጆቻቸው ሁሌም በዚህ መልክ ተመዝቦ የሚታወቅ መሆኑን ቤተሰባቸውን ጨምሮ በሁሉም ዘንድ ምክክር ከተደረገበት በሁዋላ የተወሰነ ነው። እርግጥ፡ ነው ንጉሱ ብዙ የሚያምር ልዩ ልዩ ጌጥ ያለው ልብስና፡አቁዋቁዋም አላቸው ። እሱን ለራሳችን ስሜትና ከተማ ስንቀርፅ የምንመርጠው ይሆናል።መቸም ይሄ ሀውልታቸው የመጨረሻው አይመስለኝም።

  1. ሀውልቱ ለምን የዚህ ዓይነት መልክ ያዘ ?

አደባባይ የሚቀመጥ ፡ሀውልት በዓለም ዙሪያ ከክርስቶስ ልደት በፊት አንስቶ ባብዛኛው በነሀስ መስራት የተለመደና፡ የተመረጠ ነው ። ለምን ቢሉ ቢያንስ ለሶስት ጉዳይ አንድ በጣም ጠንካራ፡የብረት ዘር በመሆኑ ሁለተኛ፡ ተፈላጊውን ቅርፅ ለማስያዝ ለስራ፡አመቺ በመሆኑ ሶስተኛ ከአካባቢው ጋር በጊዜ ውስጥ፡ የሚመሳሰልና፡በመልኩ የማይረብሽ በመሆኑ ። ስለሆነም ባደባባይ ሲቀመጥ በየቀኑ ተላላፊው ተመልካች ሁሌም እንዲወደው ፓቲኔት ይደረጋል። ያደባባይ ሀውልት እንደሜዳሊያና እንደ ዋንጫ ተብለጭልጮ አይቀመጥም። ወይም ማናቸውንም ዓይነት ቀለም አይቀባም።በፍፁም። ፓቲኔት ይደረጋል ማለት በተመረጠ አሲድ በከፍተኛ የወላፈን እሳት (ብዙ ጊዜ ከ800 ዲግሪ ሴልሸስ ባልበለጠ ) እየተለበለበ ነሀሱ ከያዘው አብላጫ የመዳብ ይዘት ጋር ኦክሲጂንን እንዲቀላቅል ይደረጋል ። በዚህም ሰማያዊ አረንግዋዴ መልክ ወይም ያረጀ ሳንቲም እንዲመስል ይሆናል።በዓለም ላይ ይህ የተለመደ ነው። ለምሳሌ ሁሉም የሚያውቀው የኒውዮርኩዋ የሊበርቲ ሀውልት በዕድሜ ብዛት ወደዚህ ሰማያዊ አረንጉዋዴ መጥታለች። አዲስ የነሃስ ሀውልትም በዚህ ዓይነት የአሲድ ፕሮሰስ የአንቲክ ስሜት ተሰጥቶት ራሱ ደግሞ በጊዜ ብዛት አያደር ከአየር ኦክሲጂን እየተሻማ፡እንደሊበርቲ የማማሩን ዕድል ያፋጥንለታል። ውበት ማለት ላደባባይ ሀውልት እንዲህ ለነገም ለዛሬም የሚታሰብ እንጂ እንደ ስጦታ ዕቃ መብለጭለጭ የለበትም ወይም መቀባት የለበትም። የሙያው ዲሲፕሊን ይህንን ያስተምራል ። ይመክራል። ስለሆነም በላዩ ላይ ያለውን ቀለም በዚህ መንገድ ብታስቡት አንወዳለን። ይህንን ባህል የተላመዱት በውጭ የሚኖሩ የንጉሱ ቤተ ዘመዶች በምረቃው ላይ ረክተው በደስታና፡በምስጋና፡ተለያይተናል። የሁሉንም አስተያየት አከብራለሁ ግን ሁሌም ከሃላፊነትና ከጨዋነት ጋር ቢሆን ለሁላችን ይጠቅማል። ያዘመመ ዛፍ ተገኘ ሲባሉ ፈጥነው ለመገርሰስ መጥረቢያ ስለው የሚጠብቁ ብዙ እንዳሉ ሰሞኑን ታዝበናል ።ለነገሩ ባንድ ቀን ያልበቀለ ዛፍ ባንድ ቀንና የሚገረሰስ መስሏቸው ነዋ አመሰግናለሁ።

]]>
1284
ሞቶ የተገኘውና ወላጆቹ አልቅሰው የቀበሩት ወጣት ከሳምንታት በኋላ ወደ ወላጆቹ ተመለሰ http://konjoethiopia.com/2019/01/30/%e1%88%9e%e1%89%b6-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%88%e1%8a%98%e1%8b%8d%e1%8a%93-%e1%8b%88%e1%88%8b%e1%8c%86%e1%89%b9-%e1%8a%a0%e1%88%8d%e1%89%85%e1%88%b0%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%89%80%e1%89%a0%e1%88%a9/ Wed, 30 Jan 2019 13:03:34 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1269 ሞተ የተባለው ሰው አልሞትኩም ብሎ መጣ! • ሞቶ የተገኘውና ወላጆቹ አልቅሰው የቀበሩት ወጣት ከሳምንታት በኋላ ወደ ወላጆቹ ተመልሷል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤ ሕዳር 19 ቀን 2011ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳደር አንድ ወጣት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ ይገኛል፡፡ ይህም ከፖሊስ ጆሮ ይደርሳል፡፡ ጉዳዩን የሰማው ፖሊስ የሟችንም ሆነ የገዳይን ማንነት ለማወቅ ያደረገው ጥረት ለጊዜው ሳይሳካለት ይቀራል፡፡ […]]]>

ሞተ የተባለው ሰው አልሞትኩም ብሎ መጣ!

• ሞቶ የተገኘውና ወላጆቹ አልቅሰው የቀበሩት ወጣት ከሳምንታት በኋላ ወደ ወላጆቹ ተመልሷል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፤ ሕዳር 19 ቀን 2011ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳደር አንድ ወጣት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ ይገኛል፡፡ ይህም ከፖሊስ ጆሮ ይደርሳል፡፡
ጉዳዩን የሰማው ፖሊስ የሟችንም ሆነ የገዳይን ማንነት ለማወቅ ያደረገው ጥረት ለጊዜው ሳይሳካለት ይቀራል፡፡ የወንጀሉ መርማሪ ሳጅን አየነው ጎበዜ እንዳሉት ማንነቱ ያልታወቀውን ሟች ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ወደ ቆቦ ሆስፒታል ይወስዱታል፡፡

ነገር ግን ሐሙስ ሕዳር 20 ቀን 2011ዓ.ም ከሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 02 ቀበሌ ገረገራ አካባቢ ከምሽቱ 5፡00 አቶ ታረቀ መንግሥቴ የተባሉ ሰው ወደ ፖሊስ በመሄድ ‹‹ሟች የእኔ ልጅ ነው›› በማለት በኮንትራት መኪና አስከሬኑን መውሰዳቸውን ሳጅን አየነው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

አቶ ታረቀ ልጃቸውን ከቀበሩ በኋላ ሕዳር 24 ቀን ወደ ቆቦ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በመሄድ ክስ መመሥረታቸውንና የልጃቸው ገዳዮች እንዲነግሯቸው መጠየቃቸውንና ፖሊስ በግድያው ዙሪያ የደረሰበትን ለአባት መንገሩን ሳጅን አየነው አስረድተዋል፡፡
አባት አስከሬኑን ሊረከቡ በመጡበት ጊዜ ስለልጃቸው የሚያውቁትን ልዩ ምልክት ተጠይቀው እንደተናገሩና የሟቹን ፎቶግራፍ ሲያዩ በጣም እንዳለቀሱ፤ እንዳጽናኗቸውም መርማሪ ፖሊሱ ተናግረዋል፡፡

የልጃቸውን አስከሬን ከፖሊስ ተቀብለው ሌሊቱን ሲጓዙ ያደሩት አቶ ታረቀ ሕዳር 21 ቀን 2011ዓ.ም ወዳጅ ዘመድ እያስተዛዘናቸው በፍላቂት ገረገራ ደብረ ሃይማኖት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩን ያስፈጽማሉ፡፡
‹‹ቆቦ ሰው መሞቱንና የመቄት ሰው ነው መባሉን ስሰማ አጣራሁ፤ ሊቀበር መሆኑን ስሰማም ለማጣራት ሄድኩ፡፡ ደርሼም አስከሬኑን አገላብጨ አየሁ፤ ልጄ ነው፡፡ አምጥቼ ከዘመድ ወዳጅ ጋር ሆኜ ቀበርኩ፡፡ ሥርዓተ ፍትሐቱንም አስፈጸምኩ፤ ሳልስት፣ ሰባት አስቀደስኩለት፡፡ ሰላሳውን ላስቀድስ እየተዘጋጀሁ ሳለ ግን ነገሮች ተቀዬሩ›› ብለዋል አቶ ታረቀ መንግሥቴ ለአብመድ ሲናገሩ፡፡
‹‹ድንገት ስልክ ተደወለ፤ አነሳሁት፡፡ ‹ሞቷል ብላችሁ እንዳለቀሳችሁ ሰምቻለሁ› ብሎ ልጀ ደወለ፡፡ እሱ መሆኑን ስላላመንኩት የተለያዬ ዘመድ እንዲጠራ አደረኩት፤ ተጠራልኝ፡፡ ከዚያም ወደ ቤተሰቡ መጣ›› ብለዋል አባት፡፡

በወቅቱ የሟችን አስከሬን ሲያዩ ከእጁ ጣት ላይና ከጥርሱ ልዩ ምልክትን መሠረት አድርገው ልጃቸው መሆኑን እንዳረጋገጡ የገለጹት አባት ስለተፈጠረው ነገር ተገርመዋል፡፡
‹‹ሞቷል›› ተብሎ የተለቀሰለት አበበ ቤተሰቦቹ ለማመን መቸገራቸውን ገልፆ ‹‹ከሟች ጋር እንዴት እንደተመሳሰልኩ ገርሞኛል፡፡ ለማንኛውም አሁን በወላጆቼ ፊት በመገኜቴና በሕይወት በመሆኔ ደስተኛ ነኝ›› ብሏል፡፡
ምንጭ ፡ አማራ መገናኛ ብዙሃን

]]>
1269
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የአክሲዮን ባለቤት ሊሆኑ ነው ። http://konjoethiopia.com/2019/01/30/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8a%a0%e1%8b%a8%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8b%b5-%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%89%b0%e1%8a%9e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8a%ad/ Wed, 30 Jan 2019 12:50:10 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1265 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ባስገነባው የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ሠራተኞቹ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት እንዲሆኑ እንደወሰነ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ግሩፕ እሑድ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀክትና ያስገነባውን ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ባስመረቀበት ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ባሰሙት ንግግር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደረሰበት የስኬት […]]]>

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ባስገነባው የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ሠራተኞቹ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት እንዲሆኑ እንደወሰነ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ግሩፕ እሑድ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀክትና ያስገነባውን ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ባስመረቀበት ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ባሰሙት ንግግር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደረሰበት የስኬት ደረጃ የበቃው ከ16,000 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞቹ በትጋት በመሥራታቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የሠራተኛውን የባለቤትነት ስሜት ለመጨመር የአየር መንገዱ ሠራተኞች በስካይላይት ሆቴል የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት እንዲሆኑ፣ ማኔጅመንቱና የዳይሬክተሮች ቦርድ እንደወሰኑ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሠራተኞቻችን ይህን ወርቃማ ዕድል እንዲጠቀሙበት ጥሪዬን አቀርባለሁ፤›› ብለዋል፡፡

በ65 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በ42,000 ካሬ ሜትር ላይ የተገነባው ስካይላይት ሆቴል 373 የመኝታ ክፍሎች፣ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ሦስት ምግብ ቤቶች፣ ሦስት ቡና ቤቶች፣ የጤና ማዕከል፣ የመዋኛ ገንዳ፣ አነስተኛ የጎልፍ መጫወቻ ሜዳና ሌሎች በርካታ የሆቴል አገልግሎቶች አሟልቶ የያዘ ነው፡፡

አየር መንገዱ በሁለተኛ ምዕራፍ የሚገነባው ሆቴል 627 ክፍሎች እንደሚኖሩትና 150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ተገልጿል፡፡

አየር መንገዱ ለሠራተኞቹ ግዙፍ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ቀርፆ ተግባራዊ በመሆን ላይ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ተወልደ 1,200 ቤቶች ተጠናቀው ሠራተኞች መረከባቸውን ገልጸው፣ 12,000 የመኖሪያ ቤት አፓርትመንቶች ገንብቶ በጥቂት ዓመታት ውስጥ እንደሚያስረክብ ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃና ስካይላይት ሆቴልን በክብር እንግድነት መርቀው የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አየር መንገዱ የገነባቸውን የአቪዬሽን አካዴሚ፣ የጥገና ማዕከል ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ አየር መንገዱ በገነባቸው ዘመናዊ የአቪዬሽን መሠረተ ልማቶች መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹በየአገሩ ስንሄድ የማየውን አገሬ ላይ እንዳይ ስላደረጋችሁኝ አኩርታችሁኛል፤›› ብለዋል፡፡

አየር መንገዱ ጠንካራ የማሠልጠኛ ተቋም፣ የጥገና ማዕከልና የካርጎ ተርሚናል መገንባቱን ጠቁመው የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ እንዲገነባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በተገኙት ስኬቶች ሳይዘናጉ ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች እንዲያስቡ ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ 100 ሚሊዮን መንገደኞች የሚያስተናግድ ግዙፍ ኤርፖርት እንዲገነቡ አሳስበዋል፡፡

መላ የአየር መንገዱን ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላት ያመሠገኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ግርማ ዋቄና ለአቶ ተወልደ ልዩ ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡ ኩባንያው የሠራተኞቹ የአክሲዮን ባለቤት እንዲሆኑ መጋበዙ ሠራተኞች ተቀጣሪ ብቻ ሳይሆኑ ባለቤት ሊሆኑ እንደሚችሉ፣ ለሌሎች ተቋማትም ትምህርት የሚሆን ዕርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሙስሊም፣ ክርስቲያን ሳንል እንዲህ ያለ ያማረ ሥራ መሥራት አለብን፡፡ የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ አየር መንገዱን ወደ ኋላ መመለስ የለበትም፤›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ መንግሥት በአየር መንገዱ ማኔጅመንት ሥራ ጣልቃ እንደማይገባ ይልቁንም የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ከአራት ዓመት በፊት ግንባታውን በ245 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያስጀመረው የአዲስ አበባ ኤርፖርት ተርሚናል ማስፋፊያ ፕሮጀክት፣ በሒደት በተካተቱ ተጨማሪ ሥራዎች ወጪው ወደ 363 ሚሊዮን ዶላር አድጓል፡፡

ግንባታው በሦስት ምዕራፍ ተከፈሎ የሚካሄድ ነው፡፡ የመጀመርያው ምዕራፍ የምዕራብና ምሥራቅ ክንፍ ሕንፃ ግንባታ፣ ሁለተኛው ምዕራፍ የቪአይፒ ተርሚናል ግንባታና ሦስተኛ ምዕራፍ የአገር ውስጥ ተርሚናል ማስፋፊያ ናቸው፡፡ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎችና የመዳረሻ መንገዶች ግንባታ በፕሮጀክቱ ተካተዋል፡፡

የዋናው ተርሚናል ግንባታ 86 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የቪአይፒ ተርሚናሉ ግንባታ ከአንድ ዓመት በፊት ተጀምሯል፡፡ የአገር ውስጥ ተርሚናል ማስፋፊያ ሥራም በቅርቡ ተጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ ዳዊት ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ አዲስ አበባ በአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ቀዳሚ መዳረሻ ትሆናለች፡፡

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ በነሐሴ 2009 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አቪዬሽን ግሩፕ እንዲቀላቀል መደረጉ ይታወሳል፡፡ ዋናው ተርሚናል እ.ኤ.አ. 2003 ዓ.ም. ሲመረቅ በዓመት ስድስት ሚሊዮን መንገደኞች የማስተናገድ አቅም እንዳለው ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ብሔራዊ አየር መንገዱ ከተገመተው በላይ በማደጉ ምክንያት በዓመት 11 ሚሊዮን መንገደኞች በማስተናገድ ላይ ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ የተፈጠረውን መጨናነቅ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀርፈው ይታመናል፡፡

አሁን ያለው ተርሚናል የወለል ስፋት 48,000 ካሬ ሜትር ሲሆን፣ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ አዲስ የተገነባው ሕንፃ ወለል ስፋት 74,000 ካሬ ሜትር ነው፡፡

አዲሱ ሕንፃ 72 የመንገደኛ ማስተናገጃ መስኮቶችና 21 የመሳፈሪያ ቢሮዎች አሉት፡፡ ግንባታው በሰኔ 2011 ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ የፕሮጀክቱ ዋና መሐንዲስ አቶ ኃይሉ ለሙ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የቪአይፒ ተርሚናሉ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ የአገር ውስጥ ተርሚናሉ ማስፋፊያ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ አቶ ኃይሉ ገልጸዋል፡፡ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ የተርሚናሉን የማስተናገድ አቅም በዓመት ከ11 ሚሊዮን ወደ 22 ሚሊዮን መንገደኞች እንደሚያሳድገው ተገልጿል፡

Source ፡ ሪፖርተር

]]>
1265
በአምስት ቀናት 18 ባንኮች ተዘርፈዋል ። http://konjoethiopia.com/2019/01/15/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%89%b5-%e1%89%80%e1%8a%93%e1%89%b5-18-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ae%e1%89%bd-%e1%89%b0%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%8d%88%e1%8b%8b%e1%88%8d-%e1%8d%a2/ Tue, 15 Jan 2019 16:13:21 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1261 በምዕራብ ኦሮሚያ 3 ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስትና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የክልሉ መንግስት ገለፀ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ፥ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ ምእራብ ወለጋ፣ […]]]>

በምዕራብ ኦሮሚያ 3 ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስትና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የክልሉ መንግስት ገለፀ
በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ፥ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 18 ባንኮች ላይ ነው ዝርፊያው የተፈፀመው።
ዝርፊያውም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ላይ ነው የተፈፀመው ያለው ቢሮው፥ ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ተቋም ላይም ዝርፊያ መፈፀሙን አስታውቋል።
ከባንኮች ዝርፊያ በተጨማሪም የተለያዩ የግል እና የመንግስት ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱንም ቢሮው በመግለጫው አክሎ አስታውቋል።
በዚህም ቁጥራቸው 10 የሚደርሱ የመንግስት እና የግል ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው በመግለጫው ተመልክቷል።
ከዚህ በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሱት ዞኖች የመንግስት መሳሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል ያለው ቢሮው፥ የተለያዩ የስራ ሰነዶችን የማቃጠል እና የማውደም፣ የመንግስት ተሽከርካሪ እና የግል ንብረቶች ዝርፊያ እንዲሁም መንገድ በመዝጋት የህዝቡን የመንቀሳቀስ መብት የመገደብ ተግባር ተፈፅሟል ብሏል።
እንዲህ አይነቱን ህገ ወጥ ተግባርም ህዝቡ አምርሮ በመቃወም አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ ከመንግስት እና ከፀጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
በዚሁ መሰረት ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ቢሮው ያስታወቀው።
ይህንን የወንጀል ተግባር በማቀነባበር እና በመፈፀም የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በህግ ቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑንም ገልጿል።
በአሁኑ ወቅትም የህግ የበላይነትን ለማስከበር እና የህዝቡን ደህንነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለው ስራም በምእራብ ኦሮሚያ ያለው የሰላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱንም ጠቅሷል።
አሁን የተገኘው የሰላም ሁኔታ ቀጣይነት እንዲኖረውም የአካባቢው ህዝብ እና መንግስት ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን እየሰሩ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።
በተመሳሳይ የደቡብ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጦር የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች ያቀረቡለትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላማዊ ትግል እየተመለሱ መሆኑን ቢሮው በመግለጫው ጠቅሷል።
በዚህም መሰረት ኤሊያስ ጋምቤላ ጎሎ የሚመራው የጉጂ ዞን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጦር ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ወደተዘጋጀለት ማረፊያ እየገባ መሆኑንም አስታውቋል።
Source Fbc

]]>
1261
በኦሮሚያ ባንክ ላይ የተፈፀመው የ80 ሚሊየን ብሩ የዘረፋ ድራማ http://konjoethiopia.com/2019/01/11/%e1%89%a0%e1%8a%a6%e1%88%ae%e1%88%9a%e1%8b%ab-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ad-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8d%88%e1%8d%80%e1%88%98%e1%8b%8d-%e1%8b%a880-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95/ Fri, 11 Jan 2019 14:29:55 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1258 ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ንብረት የሆነ ገንዘብ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላው ሲዘዋወር እንደተዘረፈ ተሰምቷል። ታህሳስ 19፣ 2011 ዓ. ም. በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና ከተማ ጭሮ ውስጥ የሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 80 ሚሊዮን ብር ወጭ ያደርጋል። ገንዘቡን ወደ ደብረ ዘይት ቅርንጫፉ ለማዘዋወርም ጉዞ ይጀምራል። ሆኖም ገንዘቡን የጫነው መኪና የታሰበበት ሳይደርስ መኤሶ ወረዳ […]]]>

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ንብረት የሆነ ገንዘብ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላው ሲዘዋወር እንደተዘረፈ ተሰምቷል።

ታህሳስ 19፣ 2011 ዓ. ም. በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና ከተማ ጭሮ ውስጥ የሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 80 ሚሊዮን ብር ወጭ ያደርጋል።

ገንዘቡን ወደ ደብረ ዘይት ቅርንጫፉ ለማዘዋወርም ጉዞ ይጀምራል። ሆኖም ገንዘቡን የጫነው መኪና የታሰበበት ሳይደርስ መኤሶ ወረዳ አሰቦት አካባቢ መሳሪያ በያዙ ሰዎች ተከበበ።

ከዚያስ? የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሐላፊ ኮማንደር ጋዲሳ ንጉሳ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን ብለዋል ” የተወሰኑ ኃይሎች ሽጉጥ የያዙ እንዲሁም ባዶ እጃቸውን የነበሩ ግለሰቦች መኪናውን መንገድ ላይ አስቆሙት። ሾፌሩን አስፈራርተው በማስወረድ አሰቦት ወደምትባል አካባቢ መኪናዋን ወሰዷት”

ከተዘረፈው 80 ሚሊዮን ብር ውስጥ በሽምግልና፣ በድርድርና በፍተሻ ማስመለስ የቻሉት ገንዘብ እንዳለም ይናገራሉ።

ይህን ያህል ገንዘብ አስመልሰናል ለማለት ሰነድ ባያጠናቅሩም “እጅ ከፍንጅ የተያዘ ገንዘብ የለም። አብዛኛው ብር የተመለሰው በጥቆማ ነው። በርካታ መኪና ይዘው ሲሄዱ በፍተሻ የተያዙ አሉ” ብለዋል።

ለመሆኑ አንድ ባንክ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ገንዘብ ሲያዘዋውር የሚደረግለት የጥበቃ ኃይል ወደየት ሄዶ ነው ዝርፊያው ሊፈፀም የቻለው? በሚል ቢቢሲ ኮማንደሩን ጠይቋል።

“በወቅቱ አብረው የነበሩት ፖሊሶች ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ መያዝ አልቻሉም። ወደ ሌላ እርምጃ ከተገባ በነሱም ደህንነት ላይ አደጋ ስለሚመጣ በልመናና በድርድር ገንዘቡን መውሰድ እንዲያቆሙ ለማድረግ ተሞክሯል። ማስፈራራትና ወደ ሰማይም ተተኩሷል።”

ዘራፊዎቹ በቁጥር ብዙ እንደነበሩ የሚናገሩት ኮማንደሩ፤ ዘራፊዎቹ ገንዘቡን ከዘረፉበት ቦታ ወደ ከተማ ይዘው ከሄዱ በኋላ ለመከፋፈል ሲሞክሩ የከተማው ከንቲባ “የሕዝብ ንብረት ነው” ብለው በድርድር ለማስቆም ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ይገልጻሉ።

ፎርቹን ጋዜጣ፤ ብሩ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ ላይ እንደነበር ጠቅሶ 100 ግለሰቦች በዝርፊያው ተጠርጥረው ተይዘዋል ሲል ዘግቧል።

ከዘረፋው ጀርባ ያሉ ሰዎችን ማንነት ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ኮማንደሩ ቢናገሩም፤ “ዘራፊዎቹ ከሩቅ የመጡ አይደሉም” የሚል ጥቆማ ሰጥተዋል።

ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከድሬዳዋ ቅርንጫፍ 80 ሚሊዮን ብር ጭኖ በመኢሶ ወረዳ ሲተላለፍ ነበር። ያኔ ገንዘቡን ይዞ ይጓዝ የነበረው መኪና አሽከርካሪ አህያ ገጭቶ በአካባቢው ፖሊስ ተይዟል። በወቅቱ የተገኘው ገንዘብና አጓጓዡ የያዘው ሰነድ ላይ የሰፈረው የገንዘብ መጠን መካከል ልዩነት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

ገንዘቡን መጫን የነበረበት መኪና ሰሌዳ ቁጥርና በፖሊስ የተያዘው መኪና ታርጋ ቁጥርም የተለያየ ነው ተብሎ ነበር። ለመሆኑ የዚህ ገንዘብ ጉዳይ ከምን ደረሰ? ኮማንደር ጋዲሳ ምላሽ አላቸው።

“አምሳ ሚሊዮኑን የሚያሳይ ሰነድ በገንዘብ ያዡ እጅ አልነበረም። ይህም ከኔትወርክ ችግር ጋር የተያያዘ ነው። መንገድ ላይ በኢሜይል እንልክላችኋለን የሚል ነገር ነበር”

ገንዘቡ ከወጣበት ቅርንጫፍ ጀምሮ ስለነበረው ሂደት ምርመራ ተእየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

መጀመሪያ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የነበረው መኪና ሰሌዳው ቁጥር ሌላ ሲሆን፤ ይህም በአጋጣሚ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የታሰበው ሾፌር በህመም ላይ ስለነበር ነው ብለዋል።

“ስለ ሹፌር ለውጥ የሚገልጽ ደብዳቤ ሳይቀየርብ ሌላ መኪና በመተካቱ ነው” ሲሉ የድሬዳዋ ስራ አስኪያጅ እንደነገሯቸው ኮማንደሩ ገልፀዋል።

“ገንዘቡ ህጋዊ መሆኑን ነው የምናውቀው። አሁን ምርመራ ላይ ነው። በቅርብ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ” ብለዋል።

መኪና ውስጥ የተገኘው ገንዘብ ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ ገንዘቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ቅርንጫፍ ውስጥ እንዲቆይ መወሰኑንም ኮማንደር ጋዲሳ ገልፀዋል።

ምንጭ ቢቢሲ

]]>
1258
Ethiopia-Eritrea border restrictions tighten http://konjoethiopia.com/2018/12/26/ethiopia-eritrea-border-restrictions-tighten/ Wed, 26 Dec 2018 14:39:59 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1233 Ethiopia-Eritrea border restrictions tighten December 26, 2018 | by Ethiopia Observer | 0 The border crossing between Ethiopia and Eritrea closed this morning for reasons not disclosed yet, according to informants from the area. The main road between Zalambessa and the Eritrean town of Serha is no longer accessible since this morning after Eritrean soldiers were deployed in the […]]]>

Ethiopia-Eritrea border restrictions tighten

December 26, 2018 | by Ethiopia Observer | 0

Ethiopia-Eritrea border restrictions tighten

The border crossing between Ethiopia and Eritrea closed this morning for reasons not disclosed yet, according to informants from the area. The main road between Zalambessa and the Eritrean town of Serha is no longer accessible since this morning after Eritrean soldiers were deployed in the area, sources say. The border was officially opened following the rapprochement between the one-time enemies on September 10.

After its opening up, people from both countries were crossing the border without official permission, the informants said. But since this morning, Ethiopian nationals heading in the direction of Eritrea were told to have special permit from the federal government detailing the purpose of their visits, the informants said. Vehicles are not being allowed across the border, leaving travellers stranded.

Even after the rapprochement, only two border checkpoints in a more than 1,000 kms common border were re-opened. The crossing through Badme and Humera remain closed.

]]>
1233
ኦዴፓ እና ኦነግ በጋራ ለመስራት ያደረጉት ስምምነት እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም http://konjoethiopia.com/2018/12/25/%e1%8a%a6%e1%8b%b4%e1%8d%93-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8a%a6%e1%8a%90%e1%8c%8d-%e1%89%a0%e1%8c%8b%e1%88%ab-%e1%88%88%e1%88%98%e1%88%b5%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%8b%ab%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%8c%89%e1%89%b5/ Tue, 25 Dec 2018 15:14:32 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1223 የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በሰላምና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያደረጉት ስምምነት እስካሁን ተግባራዊ መሆን እንዳልቻለ ኦዴፓ አስታወቀ። ሁለቱ ፓርቲዎች በደረሱት ስምምነት መሰረት የጋራ ኮሚቴ ቢያዋቅሩም ከያዟቸው እቅዶች መካከል ብዙዎቹን መፈፀም አልቻሉም። የሰላም ስምምነቱ አስፈጻሚ ኮሚቴና የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሞገስ ኢደኤ በሰጡት መግለጫ፤ በስምምነቱ መሰረት በአስራ አምስት […]]]>


የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በሰላምና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያደረጉት ስምምነት እስካሁን ተግባራዊ መሆን እንዳልቻለ ኦዴፓ አስታወቀ።

ሁለቱ ፓርቲዎች በደረሱት ስምምነት መሰረት የጋራ ኮሚቴ ቢያዋቅሩም ከያዟቸው እቅዶች መካከል ብዙዎቹን መፈፀም አልቻሉም።

የሰላም ስምምነቱ አስፈጻሚ ኮሚቴና የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሞገስ ኢደኤ በሰጡት መግለጫ፤ በስምምነቱ መሰረት በአስራ አምስት ቀናት የሚፈጸም እቅድ አውጥተው ቢንቀሳቀሱም ከታቀደው አብዛኛው እስካሁን አልተተገበረም።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) አመራር ወደ አገር የገባው መስከረም 5 ቀን 2011 ዓ.ም ነው።

የአመራር ቡድኑ ከሁለት አስርተ ዓመታት የስደትና የትጥቅ ትግል በኋላ ወደ አገር ቤት ሲገባ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ለማከናወን ወስኖ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል።

“የህግ የበላይነት ጊዜ ሳይሰጠው ከዛሬ ጀምሮ መከበር አለበት” በማለት ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ሲናገሩ፤ በአገሪቷ የለውጡ መሪ ከሆነው መንግስት ጋር በሰላማዊ መንገድ ለመስራት ወስነው መመለሳቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ከስምምነቶቹ መካከል ትጥቅ ያልፈቱ የኦነግ ሰራዊቶች በአጭር ጊዜ ትጥቅ ፈተው ወደ ማስልጠኛ እንዲገቡ፣ ለአካባቢው ሰላም በጋራ በመስራት የህግ የበላይነት እንዲከበርና ለልማት እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተንቀሳቅሰዋል።

ይሁን እነጂ በኦነግ በኩል ሰራዊቱ ትጥቅ ባለመፍታቱ በተለይም  በምዕራብ ኢትዮጵያ እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች ምክንያት ሆኗል።

እንደ አቶ ሞገስ ገለፃ፤ የተደረሰው ስምምነት በህዝቡ ዘንድ ብዥታን እየፈጠረ በመሆኑ በጋራ መግለጫ ለመስጠት ቢታሰብም እስካሁን አልተፈፀመም።

በአሁኑ ወቅት  በአንዳንድ አካባቢዎች የሰው ህይወት መጥፋቱንና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም መዘጋታቸውን አቶ ሞገስ ተናግረዋል።

መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ብርቱ ጥረት ቢያደረግም ‘የኦነግ አመራር አባላት ግን ለእቅዱ መፈጸም ፈጣን ምላሽ አልሰጡም’ ብለዋል።

የተያዘው እቅድ ተግባራዊ ያልሆነው በኦነግ በኩል በእቅድ ያልተያዙ ጥያቄዎችን በማንሳቱ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር የሚደረጉ ጥረቶች ማነስና ለሰላም ፈጣን ምላሽ ባለመስጠቱ መሆኑን አስረድተዋል።

ይሁን እንጂ መንግስት ትጥቅ ፈተው ወደ አገር ውስጥ ለገቡ የኦነግ ሰራዊት አባላት በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት የኦነግ አባላት ትምህርት ደረጃቸውንና ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ የስራ ምደባ የተሰጣቸው ሲሆን 747 አባላቱም በአዳማ ፖሊስ ማሰልጠኛ ገብተው እየሰለጠኑ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልሉ መንግስት በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብና በህዝብ  መስዋዕትናት የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ መሆኑንም አቶ ሞገስ ተናግረዋል።

ኮሚቴውም የተጀመረው የሰላም ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን “ጥረቱን ይቀጥላል” ብለዋል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ያልሆነበትን ምክንያትና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ  የኢዜአ ሪፖርተር  የግንባሩን ቃል አቀባይ ቢያነጋግርም በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት አልቻለም።

]]>
1223
4583 ካ.ሜ መሬት ለባለሃብቶች ያስተላለፈው ኃላፊ ለከንቲባ ፅ/ቤት በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ http://konjoethiopia.com/2018/12/24/4583-%e1%8a%ab-%e1%88%9c-%e1%88%98%e1%88%ac%e1%89%b5-%e1%88%88%e1%89%a3%e1%88%88%e1%88%83%e1%89%a5%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%88%8b%e1%88%88%e1%8d%88%e1%8b%8d-%e1%8a%83%e1%88%8b/ Mon, 24 Dec 2018 15:14:04 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1216 በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አጃንባ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የመሬት አስተዳደር የሰነድ አልባ ዴስክ ኃላፊ የሆነው ግለሰብ ከሶስት የክፍሉ ባለሞያዎች ጋር በመተባበር መሬት ባንክ በኮድ ቁጥር 79 ገቢ የተደረገን ባዶ ቦታ የድርጅት በማድረግ እና መረጃ በማዛባት ለግለሰቦች ካርታ አዘጋጅቶ በመስጠት የህዝብን ውስን ሃብት ለግል ጥቅም በማዋል መንግስት ሊያገኘው የሚገባውን 12.1 ሚሊየን ብር አሳጥቷል፡፡ የመሬት […]]]>

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አጃንባ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የመሬት አስተዳደር የሰነድ አልባ ዴስክ ኃላፊ የሆነው ግለሰብ ከሶስት የክፍሉ ባለሞያዎች ጋር በመተባበር መሬት ባንክ በኮድ ቁጥር 79 ገቢ የተደረገን ባዶ ቦታ የድርጅት በማድረግ እና መረጃ በማዛባት ለግለሰቦች ካርታ አዘጋጅቶ በመስጠት የህዝብን ውስን ሃብት ለግል ጥቅም በማዋል መንግስት ሊያገኘው የሚገባውን 12.1 ሚሊየን ብር አሳጥቷል፡፡

የመሬት አስተዳደር የሰነድ አልባ ዴስክ ኃላፊ የሆነው ግለሰብ ከተጠቀሱት ባለሃብቶች ጋር በግል በፈጠረው ያልተገባ ቁርኝት አንደኛውን ባለሃብት 600,000 እና ሁለተኛውን 400,000 ብር የሊዝ ዋጋ በማስከፈል በድርጅት ስም የመሬት ባንክ ንብረት የሆነውን 4583 ካሬ ሜትር አጥር የሌለው ቦታ አስተላልፏል፡፡

ይህን የታዘቡት የአከባቢው ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ በዘረጋው የጥቆማ መስጫ ቁጥር በመጠቀም ለከንቲባ ፅ/ቤት ጥቆማ አድርሰዋል፡፡

የከንቲባ ፅ/ቤት ጥቆማው እንደደረሰው አጣሪ ግብረሃይሉን በቀጥታ ወደ ተጠቀሰው ክፍለከተማ በመላክ ከመሬት ማኔጅመንት ቢሮ ጋር በመተባበር ባደረገው የማጣራት ስራ መሬቱ ያለ አግባብ መሠጠቱን እና በሰነድ አልባ ዴስክ ኃላፊው የተፈረመው ካርታም ትክክለኛ አለመሆኑን ካረጋገጠ በኃላ ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር አውሎ ጉዳያቸውን በማጣራት ላይ ይገኛል።
ሰሞኑን በተመሳሳይ ለከንቲባ ፅ/ቤት በደረሰ ጥቆማ ለካርታ አገልግሎት 90,000 ብር ጉቦ የጠየቀው የየካ ክፍለከተማ ሰራተኛ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
የከተማችን ነዋሪዎች አሁንም የከተማ አስተዳደሩ የጀመረውን ህግ የማስከበር ተግባር በመደገፍ ለውጡን ለማደናቀፍ የሚሯሯጡ አመራሮችን ፥ ባለሞያዎችን እና ግለሰቦችን በመጠቆም ለውጡን እንዲደግፉ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

]]>
1216
በኦሮሚያ ክልል የህዝብንና የመንግሰትን ንብረት አባክነዋል ተብለው የተጠረጠሩ 56 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ ። http://konjoethiopia.com/2018/12/24/%e1%89%a0%e1%8a%a6%e1%88%ae%e1%88%9a%e1%8b%ab-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8b%9d%e1%89%a5%e1%8a%95%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%b0%e1%89%b5%e1%8a%95/ Mon, 24 Dec 2018 14:08:10 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1210 በኦሮሚያ ክልል የህዝብን እና የመንግሰትን ንብረት አባክነዋል ተብለው የተጠረጠሩ 56 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፡፡ የኦሮሚያ ፀረ- ሙስና ኮሚሽን በህዝብ እና በመንግስት ንበረት ላይ ብክነት ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ሲያካሒድ የነበረውን ምርመራ በማጠናቀቅ 56 ግለሰቦችን በህግ ጥላ ስር ማዋሉን ገልጧል፡፡ በቀጣይም ተጠርጣሪዎችን በህግ ጥላ ስር የማዋል ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስታውቃል ፡፡ በሌላ በኩል […]]]>

በኦሮሚያ ክልል የህዝብን እና የመንግሰትን ንብረት አባክነዋል ተብለው የተጠረጠሩ 56 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፡፡ የኦሮሚያ ፀረ- ሙስና ኮሚሽን በህዝብ እና በመንግስት ንበረት ላይ ብክነት ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ሲያካሒድ የነበረውን ምርመራ በማጠናቀቅ 56 ግለሰቦችን በህግ ጥላ ስር ማዋሉን ገልጧል፡፡ በቀጣይም ተጠርጣሪዎችን በህግ ጥላ ስር የማዋል ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስታውቃል ፡፡ በሌላ በኩል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ የክልሉን ሰላም የሚያደፈርሱ ሃይሎችን እንደማይታገስ አስታውቋል ።
በምዕራብ ኦሮሚያ በተፈጠሩ ግጭቶች የንህፁሃን ዜጎችና የጽጥታ ሀይሎች ህይወት ማለፉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል አለማየሁ እጅጉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በምዕራብ ኦሮሚያ የተፈጠሩ ችግሮችን በውይይትና በሰከነ መንገድ በሰላመዊ ሁኔታ ለመፍታት ላለፉት ስድስት ወራት ጥረት ሲደረግ ቢቆይም የከፋ ዋጋ ማስከፈሉን ገልጸዋል።
ባለፉት አራት ወራት ብቻ በክልሉ በተፈጠሩ ችግሮች 29 ንጹሃን ዜጎች ህዎት መጥፋቱን የገለጹት ከሚሽነሩ የዜጎችን ደህንነት የሚያስጠብቁ 2 የዞን መምሪያ ሃላፊዎችን ጨምሮ 12 የፖሊስ አባላት ህይወት ማለፉንም ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም 77 የፖሊስ አባላት እና 40 ሚሊሻዎች መቁስላቸውን ኮሚሽነሩ አስርድተዋል።
በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ በቄለም ወለጋ እንዲሁም በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች አካባቢዎች አንዳንድ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት እንዲያቆሙ መደረጉንም ነው ኮሚሸነሩ የተናገሩት።
በቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ 2 ሺህ 72 ክላሽእንኮቭ መሳሪያዎች ከፖሊስ ተዘርፈዋል ያሉት ኮምሽነር አለማየሁ እጅጉ፤ በምዕራብ ወለጋ ከመንግስት ካዝና ከ3 ሚሊየን ብር በላይ መዘረፉንም አብራርተዋል።
ከላይ የተዘረዘሩት የተዘረፉ ንብረቶች የግለሰብ ንብረቶች የማይጨምሩ ሲሆን፥ በርካታ የግለሰብ ንብረቶች መዘረፋቸውም ኮሚሽነር ጄኔራሉ አስረድተዋል።
የአካባቢው ህብረተሰብ አሁንም ከፀጥታ ሃይሎች ጋር አብሮ እየሰራ ሲሆን፥ በቦኖ በደሌና ግንጪ መንገዶችና ሱቆችን ለመዝጋት የተደረገውን ጥረት መክሹፉን ለአብነት ጠቅሰዋል።
ከዚህ በኋላ መሰል ድርጊቶችን መንግስት እንደማይታገስ የተናገሩት ኮሚሽነር አለማሁ፥ ለሁሉም ዞኖች ጥብቅ መመሪያ መተላለፉን ነው የገለጹት።
ለሁሉም ዜጋ ሰላምን በማስቀደም ፖሊስ ህገ ወጦችን የመከታተል ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ ሀላፊነቱን በአግባቡ የማይወጣ የፀጥታ ሃይል ላይም አስፈላጊውን አርምጃ እንሚወሰድበት አመላክተዋል ።
Obn

]]>
1210
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታራሚዎች ረብሻ ፈጠሩ ። http://konjoethiopia.com/2018/12/23/%e1%89%a0%e1%89%83%e1%88%8a%e1%89%b2-%e1%88%9b%e1%88%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%89%b3%e1%88%ab%e1%88%9a%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%88%a8%e1%89%a5%e1%88%bb-%e1%8d%88%e1%8c%a0%e1%88%a9/ Sun, 23 Dec 2018 14:20:00 +0000 http://konjoethiopia.com/?p=1201 በቃሊቲ ማረሚያ ቤት “ይቅር ተደርጐልን መፈታት አለብን” የሚሉ እስረኞች ከትናንት በስቲያ ከሐሙስ ጀምሮ ረብሻ በማስነሳት የእርስ በርስ ግጭት መፈጠሩ ታውቋል፡፡ በማረሚያ ቤቱ ዞን ሁለት በተባለው ክፍል ከአዲስ አበባና ከፌደራል የፍትህ አካላት የተውጣጡ አስተዳዳሪዎች የታራሚዎችን አያያዝ በተመለከተ በአካል ተገኝተው ለመታዘብ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ረብሻው መቀስቀሱን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ታራሚዎቹ በዋናነት “የይቅርታ ማመልከቻ አስገብተን፣ እንዴት እስካሁን ሳንፈታ ቆየን፤ […]]]>

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት “ይቅር ተደርጐልን መፈታት አለብን” የሚሉ እስረኞች ከትናንት በስቲያ ከሐሙስ ጀምሮ ረብሻ በማስነሳት የእርስ በርስ ግጭት መፈጠሩ ታውቋል፡፡ 
በማረሚያ ቤቱ ዞን ሁለት በተባለው ክፍል ከአዲስ አበባና ከፌደራል የፍትህ አካላት የተውጣጡ አስተዳዳሪዎች የታራሚዎችን አያያዝ በተመለከተ በአካል ተገኝተው ለመታዘብ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ረብሻው መቀስቀሱን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ 
ታራሚዎቹ በዋናነት “የይቅርታ ማመልከቻ አስገብተን፣ እንዴት እስካሁን ሳንፈታ ቆየን፤ ልንፈታ ይገባል” በሚል ተቃውሞ መጀመራቸውን የገለፁት ምንጮች፤ ይኸም ወደ እርስ በእርስ ግጭት አምርቶ በድንጋይና በተለያዩ ቁሳቁሶች በመታገዝ፤ በርካቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል፡፡ 
ረብሻው መፈጠሩን ለአዲስ አድማስ ያረጋገጡት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ገረመው አያሌው፤ ግጭቱና ረብሻው ብዙም ሳይስፋፋ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ 
ታራሚዎቹ ዞን ሁለትን ከዞን ሶስት የሚለየውን አጥር በማፍረስ ሁለቱን ዞኖች የቀላቀሉ ሲሆን ወደ ሴቶች ማረፊያ ለመግባትም ሙከራ ማድረጋቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ 

Source ፡አዲስ አድማስ

]]>
1201