ህወሓት ከፌደራል ተሸንፎ ነው የመጣው፤ በጣም ችግር ላይ ነው ያለው ፡፡ ( አምዶም ገ/ስላሴ )

• ህወሓት ከፌደራል ተሸንፎ ነው የመጣው፤ በጣም ችግር ላይ ነው ያለው፡፡ የቆየው በጠመንጃ፣ በደህንንት፣ በፖሊስ እና በገንዘብ ኃይል ሲሆን፤ የትግራይን ሕዝብ ፍላጎት የማያሟላና ለማስተዳደር የማይበቃ ድርጅት ነው፡፡

• ኤፈርትን በሃላፊነት ያገለገሉት አቶ ስብሀት ነጋ መድረኩ ላይ ስለነበሩ ባያቋርጡኝ ድርጅቱን በተመለከተ ለመናገር ነበር ያሰብኩት፡፡ ከኤፈርት ጋር በተያያዘ የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ እንደሆነ ተደርጎ ይወራል፡፡ ህወሓት ድርጅቱን ለራሱ ነው መጠቀሚያ ያደረገው፡፡

• በአማራው ክልል አዴፓ እና በህወሓት መካከል ያለው የስልጣን ሽኩቻ የሁለቱን ክልሎች ሕዝቦች ያጋጫል፤ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ብለን እንገምታለን፡፡

• የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ምንም አይነት ጥያቄ የሚነሳበትና የሚያነሳም ሕዝብ አይደለም፤ ሀገሩን ትቶ ወደየትም አይሄድም፡፡

• የትግራይ ተወላጆች በአማራ፣ በኦሮሚያና በሌሎችም ክልሎች ጥቃት እየደረሰባቸው ነውና ይሄን ጉዳይ በጽኑ ነው የምንቃወመው፡፡ ህወሓት ግን ይህን ይፈልገዋል፡፡ ምክንያቱም እኔ ከሌለሁ ያጠፉሀል የሚል ፕሮፓጋንዳ በመስራት ይጠቀምበታል፡፡

የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉአላዊነት (አረና) ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ካደረገው ቃለምልልስ የተወሰደ ሙሉ ቃለምልልሱን በነገው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይጠብቁ ።