ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት
ሕገ መንግስቱን ማሻሻል የሚቻልበት አሰራር በራሱ በሕገ መንግስቱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ የማይሻሻልበት ምክንያት የለም፡፡ ምክንያቱም ሕገመንግስት ዘላለማዊና ቋሚ አይደለም፡፡
ሕዝባችንን መጠየቅ የምፈልገው ሰፊ ትእግስትና መረጋጋት እንዲኖረው ነው፡ ፡የፍትሕ ጉዳይ በአንድ ጀምበር መልስ የሚገኝለት አይደለም፡፡ሪፎርሙ ተጀምሯል፡፡መንግስት መልካም ሀሳብ አለው፡፡ሕዝቡ በቅን ልቦና እንዲረዳው ትእግስት እንዲያደርግ ያስፈልጋል፡፡
ትክክለኛና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ፍትሕ እንደሚሰጥ ሌላው ወገን በፍርድ ቤት ላይ ሙሉ እምነት እንዲኖረው መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡
የሚዲያ ሰዎች እንዲከታተሉት፣እንዲያውቁት፣ሕዝቡንም እንዲያሳውቁት የምፈልገው የሐሰተኛ ማስረጃ ሰነድን ጉዳይ ነው፡፡ በሐሰተኛ ሰነድ ሰው ንብረቱን እያጣ ነው ፡፡
የዳኝት ነጻነትን ለማረጋገጥ ዳኞች ራሳቸው ለራሳቸው መቆም አለባቸው፡፡ ሲታዘዙ አቤት ከማለት ወጥተው የዳኝነት ነጻነትን ማስከበር አለባቸው፡፡