Take a fresh look at your lifestyle.

ተጨማሪ አዳዲስ ዜናዎች ከ konjoethiopia.com

202

የትግራይ ክልል በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ ሰወችን አሳልፎ እንዲሰጥ ከመንግስት የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ ተፈላጊ ግለሰቦችን በሙሉ እንደሚያስረክብ በገለፀው መሰረት ተፈላጊ ግለሰቦችን የሚያመጣ ቡድን ወደ መቐለ ጉዞ ጀመረ የፀጥታና የደህንነት ቡድኖችንና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትን ይዞ ዛሬ ማምሻውን ወደ መቐለ የተንቀሳቀሰው ይህ ቡድን የቀድሞውን የስኳር ኮርፖሬሽን ሃላፊ አቶ አባይ ፀሃዬንና ሌሎች 11 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ይዞ ነገ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስ  ለ konjoEthiopia.com የደረሰው መረጃ ያመለክታል ።

በተያያዘ ዜና በትግራይ ክልል እየተወሰደ ያለው በወንጀል የተጠረጠሩ ሰወችን የማደን እርምጃ በቀጣይ በኦሮሚያ ክልል መወሰድ እንደሚጀመር የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። ከኦሮሚያው ኦፕሬሽን በመቀጠል ደግሞ በማንኛውም መልኩ በወንጀል የተጠረጠሩ ሰወችን ከሌሎች ክልሎች የማደን ኦፕሬሽን እንደሚቀጥል ታውቋል ።
( wasihune tesfaye )

 

Comments are closed.