(ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ በሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ በሌሎች የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፈቀደ።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት፥ በተጠረጠሩበት የማፈናቀል፣ የአካል ጉዳትና ህይዎት ማለፍ ወንጀል ለፖሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀን ፈቅዷል።
መርማሪ ፖሊስ ቀሪ ስራዎችን ለማከናወን ተጨማሪ የ10 ቀን የጠየቀ ሲሆን፥ ተጠርጣሪዎቹ ተቃውሞ አቅርበዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ፖሊስ በተደጋጋሚ ጊዜ ለተመሳሳይ ምርመራ በየጊዜው ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ አይደለም ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።
ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ለፖሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀን በመፍቀድ ለጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Comments are closed.