Take a fresh look at your lifestyle.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞስኮ በረራ ጀመረ

706

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሩሲያ መዲና ሞስኮ አዲስ በረራ ጀመረ።

አምባሳደሮች፣ የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች የአየር መንገዱ ማኔጅመንት ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በረራውን አስጀምረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ባደረጉት ንግግር በረራ መጀመሩ በቀጣይ በሁለቱ አህጉሮች መካከል ያለውን የንግድ፣ የቱሪዝም እና የኢቨስትመንት ግንኙነት እንደሚያሳድገው አስረድተዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ አዲሱ በረራ የኢትዮ-ሩሲያን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን ከ 120 ዓመት በፊት የጀመሩ ሲሆን፣ግንኙነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰባ ዓመት የአገልግሎት ዕድሜው በአህጉሪቱ ተመራጭ አየር መንገድ እንዲሆን አስችሎታል።

Comments are closed.