Take a fresh look at your lifestyle.

የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (የደምሂት) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስገዶም በቁጥጥር ስር ዋለ

576

የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(የደምሂት) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስገዶም በአሶሳ ከተማ ከቤኒን የተቃዋሚ ሀይሎች ጋር ሽብር ሊፈጥር ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ።

ምንጮች እንዳረጋገጡልን አቶ ሞላ አስገዶም በአሶሳ ከተማ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

አቶ ሞላ አስገዶም ከ800 በላይ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ታጣቂዎችን በመያዝ መስከረም 1 2008 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ይታወሳል።

በወቅቱም በሞላ አስገዶም የሚመራው ሀይል በመተማና ሁመራ አድርጎ ወደ ሀገሩ የተመለሰው።

የታጣቂ ሃይሉ መሪ ሞላ አስገዶም ከኢትዮጵያ የደህንነት ተቋም ጋር ለ1 ዓመት ምስጢራዊ ግንኙነት በማድረግ ከነሙሉ ትጥቁ እና ሎጀስቲክ መሳሪያው አገሩ መግባቱም ይታወሳል ሲል Oromia Standard ዘግቧል ። በ konjoethiopia.com በኩል ደግሞ የዜናውን እውነተኝነት ለማረጋገጥ የደወልናቸው አንድ የክልሉ ባለስልጣን በሳቸው በኩል ጉዳዩን እንደማያውቁ ነግረውናል ።

Comments are closed.