በኦሮሚያ ክልል የህዝብን እና የመንግሰትን ንብረት አባክነዋል ተብለው የተጠረጠሩ 56 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፡፡ የኦሮሚያ ፀረ- ሙስና ኮሚሽን በህዝብ እና በመንግስት ንበረት ላይ ብክነት ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ሲያካሒድ የነበረውን ምርመራ በማጠናቀቅ 56 ግለሰቦችን በህግ ጥላ ስር ማዋሉን ገልጧል፡፡ በቀጣይም ተጠርጣሪዎችን በህግ ጥላ ስር የማዋል ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስታውቃል ፡፡ በሌላ በኩል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ የክልሉን ሰላም የሚያደፈርሱ ሃይሎችን እንደማይታገስ አስታውቋል ።
በምዕራብ ኦሮሚያ በተፈጠሩ ግጭቶች የንህፁሃን ዜጎችና የጽጥታ ሀይሎች ህይወት ማለፉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል አለማየሁ እጅጉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በምዕራብ ኦሮሚያ የተፈጠሩ ችግሮችን በውይይትና በሰከነ መንገድ በሰላመዊ ሁኔታ ለመፍታት ላለፉት ስድስት ወራት ጥረት ሲደረግ ቢቆይም የከፋ ዋጋ ማስከፈሉን ገልጸዋል።
ባለፉት አራት ወራት ብቻ በክልሉ በተፈጠሩ ችግሮች 29 ንጹሃን ዜጎች ህዎት መጥፋቱን የገለጹት ከሚሽነሩ የዜጎችን ደህንነት የሚያስጠብቁ 2 የዞን መምሪያ ሃላፊዎችን ጨምሮ 12 የፖሊስ አባላት ህይወት ማለፉንም ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም 77 የፖሊስ አባላት እና 40 ሚሊሻዎች መቁስላቸውን ኮሚሽነሩ አስርድተዋል።
በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ በቄለም ወለጋ እንዲሁም በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች አካባቢዎች አንዳንድ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት እንዲያቆሙ መደረጉንም ነው ኮሚሸነሩ የተናገሩት።
በቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ 2 ሺህ 72 ክላሽእንኮቭ መሳሪያዎች ከፖሊስ ተዘርፈዋል ያሉት ኮምሽነር አለማየሁ እጅጉ፤ በምዕራብ ወለጋ ከመንግስት ካዝና ከ3 ሚሊየን ብር በላይ መዘረፉንም አብራርተዋል።
ከላይ የተዘረዘሩት የተዘረፉ ንብረቶች የግለሰብ ንብረቶች የማይጨምሩ ሲሆን፥ በርካታ የግለሰብ ንብረቶች መዘረፋቸውም ኮሚሽነር ጄኔራሉ አስረድተዋል።
የአካባቢው ህብረተሰብ አሁንም ከፀጥታ ሃይሎች ጋር አብሮ እየሰራ ሲሆን፥ በቦኖ በደሌና ግንጪ መንገዶችና ሱቆችን ለመዝጋት የተደረገውን ጥረት መክሹፉን ለአብነት ጠቅሰዋል።
ከዚህ በኋላ መሰል ድርጊቶችን መንግስት እንደማይታገስ የተናገሩት ኮሚሽነር አለማሁ፥ ለሁሉም ዞኖች ጥብቅ መመሪያ መተላለፉን ነው የገለጹት።
ለሁሉም ዜጋ ሰላምን በማስቀደም ፖሊስ ህገ ወጦችን የመከታተል ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ ሀላፊነቱን በአግባቡ የማይወጣ የፀጥታ ሃይል ላይም አስፈላጊውን አርምጃ እንሚወሰድበት አመላክተዋል ።
Obn
Comments are closed.