የትግራይ ክልል በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ ሰወችን አሳልፎ እንዲሰጥ ከመንግስት የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ ተፈላጊ ግለሰቦችን በሙሉ እንደሚያስረክብ በገለፀው መሰረት ተፈላጊ ግለሰቦችን የሚያመጣ ቡድን ወደ መቐለ ጉዞ ጀመረ የፀጥታና የደህንነት ቡድኖችንና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትን ይዞ ዛሬ ማምሻውን ወደ መቐለ የተንቀሳቀሰው ይህ ቡድን የቀድሞውን የስኳር ኮርፖሬሽን ሃላፊ አቶ አባይ ፀሃዬንና ሌሎች 11 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ይዞ ነገ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስ ለ konjoEthiopia.com የደረሰው መረጃ ያመለክታል ።
በተያያዘ ዜና በትግራይ ክልል እየተወሰደ ያለው በወንጀል የተጠረጠሩ ሰወችን የማደን እርምጃ በቀጣይ በኦሮሚያ ክልል መወሰድ እንደሚጀመር የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። ከኦሮሚያው ኦፕሬሽን በመቀጠል ደግሞ በማንኛውም መልኩ በወንጀል የተጠረጠሩ ሰወችን ከሌሎች ክልሎች የማደን ኦፕሬሽን እንደሚቀጥል ታውቋል ።
( wasihune tesfaye )
Comments are closed.