Take a fresh look at your lifestyle.

ከአሲድ ጥቃት የሚከላከል “ሜክአፕ’’ ተሰራ

236

ከአሲድ ጥቃት የሚከላከል “ሜክአፕ’’ ተሰራ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2011 (ኤፍቢሲ) በብሪታንያ የ32 ዓመቷ ዶክተር ከአሲድ ጥቃት የሚከላከል መዋቢያ “ሜክአፕ” መስራቷን አስታወቀች፡፡

ወጣቷ ዶክተር አልማስ አህመድ ትባላለች፤ ሜክአፑን ለመስራት ያሰበችው ገና የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለች በአንዲት ሞዴል ላይ የደረሰውን የአሲድ ጥቃት ከተመለከተች በኋላ እንደነበር ገልጻለች፡፡

ይህንንም ተከትሎ በመላው ዓለም እየሰፋ የመጣውን ጥቃት በሌሎች ላይ እንዳይደገም እና የግፉ ሰለባ እንዳይሆኑ መላ ለመፈለግ መወሰኗን አስታውሳለች፡፡

ዶክተር አልማስ የዩኒቨርስቲ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላም በምን መልኩ የአሲድ ጥቃትን መከላከል እንደሚቻል ጥረት ማድረጓን ቀጠለች፡፡

ከበርካታ ጥረት በኋላ እንደማንኛውም መዋቢያ የሚያገለግል ሌሎቹ ሜክአፖች የሚሰጡትን አገልግሎት የሚያሟላ ምርምሯን ለማበርከት በቅታለች፡፡

የዩኒቨርስቲ ህልሟንም እውን ለማድረግ ከራሷ ኪስ 60 ሺህ ፓውንድ ማውጣቷንም ገልጻለች፡፡

ዶክተር አልማስ ያበረከተችው መዋቢያ ፊት ላይ ከተቀባ በኋላ አሲድን ከመከላከል በተጨማሪ ውሃ ወደ ውስጥ እንዳይገባ የሚከላከል ሲሆን፥ እሳት የመቋቋም አቅም እንዳለውም ገልጻለች፡፡

ይህ ምርምር አራት ዓመታትን መፍጀቱን የጠቀሰችው ዶክተር አልማስ ባለፈው ወር የባለቤትነት መብት ማግኘቷን ይፋ አድርጋለች፡፡

በቅርብ ዓመታት ውስጥ በዓለም ዙሪያ የሚደረጉ የአሲድ ጥቃቶች እየጨመሩ ሲሆን፥ በ2016 በብሪታንያ መዲና ለንደን 450 የአሲድ ጥቃቶች መፈጸማቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

 

 

Comments are closed.